የተቋቋመው ኮሚቴም የውሃ እና ፍሳሽ ስራውን የሚቆጣጠር እና የሚከታተል እንዲሁም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ደህንነት ላይ የግንዛቤ እና የጥንቃቄ ስራ የሚያከናውን ነው፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራስኪያጅ ኢንጅነር ዘሪሁን አባተ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ባለስልጣኑ ባሁኑ ሰዓት የአለም ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ ፤

በኳራንቲን የተለዩ የጤና ተቋማት እና በመዲናዋ የሚገኙ ትልልቅ ሆስፒታሎች በየቀኑ ግንኙነት በማድረግ በውሃ አቅርቦት እና ፍሳሽ ማንሳት ላይ ልዩ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጅት አጠናቋል ብለዋል፡፡

ውሃ በፈረቃ የሚታደልባቸው አካባቢዎች ደግሞ ተወካይ ደንበኞች ጋር በቂ እና ተከታታይ ክትትል በማድረግ እንዲሁም ከወረዳ አመራች ጋር በቅርበት በመስራት ደንበኞች በፈረቃቸው እያገኙ መሆናቸውን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል ፡፡

በተለያዩ ምክኒያቶች በፈረቃቸው ካላገኙ እንኳ በቦቴ እስከ ምሽት 6 ሰዓት ለዚሁ አላማ በተዘጋጁ 28 የውሃ ቦቴ ተሸከርካሪዎች ለማዳረስ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

ህዝብ በብዛት የሚንቀሳቀስባቸው አካቢዎች ( ቃሊቲ፣አስኮ፣ መርካቶ፣ዘነበ ወርቅ እና ላምበረት) በሚገኙ አውቶቢስ ተራ ከፊታችን ሀሙስ ጀምሮ የእጅ መታጠብ መረሀ ግብር ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

እንዲሁም ከዚህ ቀደም በባለስልጣኑ ስር የነበሩ እና አሁን በሌላ ተቋም የሚተዳደሩ ህዝብ በሚበዛቸው አካባቢ የሚገኙ ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶች በተለይ(በመገናኛ፣አያት፣ ካሳንቺስ፣ አራት ኪሎ፣ ስድስት ኪሎ፣ፒያሳ፣ መርካቶ ልደታ ሜክሲኮ ፣ሳር ቤት፣ አየር ጤና እና ጀሞ ህዝቡ እጁን እንዲታጠብ ለመጋቢት ወር ውሃ በነጻ የሚያቀርብ መሆኑን በመረዳት ህብረተሰቡ መጠቀም የሚችል መሆኑን ባስልጣኑ ያሳቃል፡፡

የውሃ ምርት ስራ ለ24 ሰዓት እንዲሰራ የውሃ ስርጭት ሰራተኞች ደግሞ በፈረቃ እስከ ምሽት 6ሰዓት እንዲሰሩ ከማድረግ ባሻገር ይህንን ችግር ሀገሪቱ በድል እስክትሻገር ሁሉም የባለስልጣኑ ሰራተኞች የተለየ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ለአንድ ወር ያክል ምንም አይነት ፍቃድ ሳይወስዱ ህዝቡን በቅንነት እንዲያገለግሉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የተቋቋመው ኮሚቴም እነዚህን ተግባራት በየእለቱ በቦታው ተገኝተው በመፈተሽ የክትትል እና ድጋራ ስራ የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡