ባለስልጣኑ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ለከተማዋ ነዋሪዎች ከማቅረቡ ባሻገር ማህበራዊ ሀላፊነቱ እየተወጣ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ በአይነት ድጋፍ ያደረገው 2000 ፓስታ ፣633 ካርቶን ሀይል ሰጪ ብስኩቶች( አንዱ ካርቶን 80 እሽግ ብስኩት የያዘ) ፣400 ባለ ሰባ ግራም የቲማቲም ድልህ እና 36 የገበታ ጨው ሲሆን አጠቃላይ ድምራቸው 290 ሺህ ብር በላይ ግምት አላቸው ፡፡
የድጋፍ ረክክቡ ላይ የተገኙት የማዕከሉ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን አምቢሳ ባለስልጣኑ በተለያዩ ጊዚያት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመው በተለይ በዚህ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብዙ ረጂ ተቋማት ደጋፍቸውን በቀነሱበት ወቅት ይህንን የመሰለ ድጋፍ ማበርከቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡
ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በ1998 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ቁጣራቸው 450 የሚሆኑ ወገን ዘመድ የሌላቸው የአዕምሮ ህሙማንና በተለያዩ ደዌ ታመው የሚሰቃዩ ምግብ ፣መጠለያ እንዲሁም ህከምና በመሰጠት እንክብካቤ በማድረግ ላይ የሚገኝ ማዕከል ነው፡፡