የስራ ዕድሉ የተፈጠረው በበጀት ዓመቱ ባለፍት ስምንት ወራት ውስጥ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁና በ76 ማህበራት ለታቀፉ 710 ስራ አጥ ዜጎች ነው፡፡

የስራ እድሉ የተፈጠረው በውሃ ቆጣሪ ንባብ፣ ይሃ መስመር ዝርጋታ፣ የፍሳሽ መስመር ቅጥያና ዝርጋታ፣ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ፣ የፍሳሽ እና የውሃ ማንሆል ግንባታ፣ የአጥር ስራ፣ የፓናል ቦርድና ፓምፕ ቤት ግንባታ እንዲሁም የጥበቃና መቆጣጠሪያ ቤት ግንባታ የስራ ዘርፎች ነው፡፡

ባለስልጣኑ ለስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር በከተማ ደረጃ ለተያዘው የድህነት ቅነሳ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት አቅዶ በመስራት ላይ መሆኑን የሦስተኛ ወገን ስራ ዕድል ፈጠራና መረጃ ማዕከል ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ዘውዴ ገልፀዋል፡፡

ባለስልጣኑ ተግባሩን እያከናወነ የሚገኘው ከከተማ አስተዳደሩ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ እና ከወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር የመግባቢያ ሠነድ በመፈራረም ነው፡፡