ባለስልጣኑ ከኩባንያው ጋር ስምምነቱን የተፈራረመው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪ ጣቢያ ሙሉ የኦፕርሽን ስራ ( ማጣሪያ ጣቢያው ደረጃውን የጠበቀ ፍሳሽ የማጣራት እና የማወገድ) እንዲሁም ጥገና እና የአቅም ግንባታ ስራን ያካትታል፡፡

የውል ስምምነቱ ለሶስት አመት ከመንፈቅ የሚቆይ ሲሆን ፕሮጀክቱም በአለም ባንክ የሚደገፍ ነው፡፡

የባለስልጣኑ ስራስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ በስምምነቱ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ማጣሪያ ጣቢያ መሆኑን አስታሰው፤ኩባያው ማጣሪያ ጣቢያውን ሲረከብ የአካቢውን ስነ ምህዳር ማእከል ያደረገ እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ ፍሳሽ አጣርቶ ማስወገድ እንደሚገባው አሳስበዋል።

የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪ ጣቢያ በቀን 100ሺህ ሜ.ኪዩብ ፍሳሽ ቆሻሻ የማጣራት አቅም እንዳለው የሚታወቅ ነው።