የኘሮጀክቱ ሥም፡        የአዳዲስ ቅብብሎሽ ጣቢያ ግንባታና ነባር ጣቢያዎችን ማሻሻያ ፕሮጀክት፤

አስፈፃሚው አካል፡       የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን የውሃና ሳኒቴሽን ልማትና መልሶ ግንባታ ኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ : በአዲስ አበባ ከተማ፣

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ

የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ዓላማ ከዚህ በፊት መኪኖች ከሴፕቲንክ ታንክ የሚያመጡትን ፍሳሽ ቃሊቲ ድረስ በማጓጓዝ የሚያደርጉትን ምልልስና የሃብትና የጊዜ ብክነት የሚያስቀይር መሆኑ፣

የኘሮጀክቱ ግብ

ከሴፕቲንክ ታንክ በመኪና የሚወጣውን ፍሳሽ በተመረጡ ቦታዎች በማከማቸትና የቅብብሎሽ ጣቢያ በመክፈት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት፣               

በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

  • የጥናትና ዲዛይን ስራ ማከናወን
  • በጥናቱ ውጤት መሰረት አዲስ የቅብብሎሽ ጣቢያዎች ግንባታ እና ነባር የቅብብሎሽ ጣቢያዎችን የማሻሻል ስራ መስራት

ከኘሮጀክቱ የሚጠበቅ ውጤት

ነባር የቅብብሎሽ ጣቢያዎችን የማሻሻል እና በጥናቱ መሰረት በሚመረጡ ቦታዎች አዲስ የቅብብሎሽ ጣቢያዎች ተሰርተው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ እንዲሁም የፍሳሽ መኪኖች የቀን የጉዞ ምልልስ እንዲጨምር በማድረግ ፍሳሽ በተሸርካሪ የማንሳት አቅም አንዲያድግ ይደረጋል፡፡

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2005 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2009 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት

  • በጥናቱ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

መግቢያ

እንደሚታወቀው የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በተለያዩ የከተማዋ ርቀት አካባቢዎች የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች አሉት፡፡ ወደነዚህ ማጣሪያ ጣቢያዎች ከከተማዋ መስፋፋትና ከመኪናዎች መብዛት ጋር በተያያዘ የሚደረገው ምልልስ ረዥም ጊዜ የሚፈጅ በመሆኑ በከተማዋ በተሸከርካሪ የሚነሳው ፍሳሽ ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅህኖ አሳድሯል፡፡ በመሆኑም በተመረጡ የፍሳሽ መስመር በሚያልፍባቸው የከተማዋ አካባቢዎች ፍሳሽ ኢንጄክት በማድረግና የፍሳሽ መኪኖችን ምልልስ በመጨመር በከተማዋ ፍሳሽ በፊጥነት እንዲነሳ ለማስቻል ይረዳ ዘንድ ይህ ፕሮጀክት ተቀርጿል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

ይህ ኘሮጀክት ተፈጻሚ ሲሆን የፍሳሽ መኪኖች ወደ ማጣሪያ ጣቢያ የሚያደርጉት ምልልስ በመቀነስ ከከተማዋ ፍሳሽ በፍጥነት እንዲነሳ የሚያስችል ይሆናል፡፡

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ

የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ዓላማ ከዚህ በፊት መኪኖች ከሴፕቲንክ ታንክ የሚያመጡትን ፍሳሽ ቃሊቲ ድረስ በማጓጓዝ የሚያደርጉትን ምልልስና የሃብትና የጊዜ ብክነት የሚያስቀይር መሆኑ፣

የኘሮጀክቱ ግብ

ከሴፕቲንክ ታንክ በመኪና የሚወጣውን ፍሳሽ በተመረጡ ቦታዎች በማከማቸትና የቅብብሎሽ ጣቢያ በመክፈት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት፣

ከኘሮጀክቱ የሚጠበቅ ውጤት

ነባር የቅብብሎሽ ጣቢያዎችን የማሻሻል እና በጥናቱ መሰረት በሚመረጡ ቦታዎች አዲስ የቅብብሎሽ ጣቢያዎች ተሰርተው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ እንዲሁም የፍሳሽ መኪኖች የቀን የጉዞ ምልልስ እንዲጨምር በማድረግ ፍሳሽ በተሸርካሪ የማንሳት አቅም አንዲያድግ ይደረጋል፡፡

በ2008 በጀት አመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

  • ቀሪ የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማጠናቀቅ
  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ3 ነባር ቅብብሎሽ ጣቢያ ማሻሻያና የ9 አዳዲስ ቅብብሎሽ ጣቢያ ግንባታ ሥራ 50 በመቶ ማከናወን
  • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም ለነባርና አዳዲስ ቅብብሎሽ ጣቢያ ግንባታ ሥራ የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን
  • የወሰን ማስከበር ሥራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

አማካሪ መምረጥና አማካሪው ጥናቱን እንደያከናውን ማድረግ እንዲሁም ለግንባታ ሥራው አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግ ይደረጋል፡፡

ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግበአቶች

  • ዝርዝር ጥናቱን የሚያጠና አማካሪ የሚቀጠር ሲሆን አስፈላጊ ባለሙያዎችን በሙሉ አማካሪ ድርጅቱ ያቀርባል፡፡ በተጨማሪም ለግንባታ ስራውም የፕሮጀክት ተቆጣጣሪ መሀንዲስ የሚመደብ ይሆናል፡፡

የአካባቢና የማሕበራዊ ትንታኔ

  • በአካባቢው የተለያዩ ዘርፈ ብዙ የማህበራዊ ሥራወች የሚሰሩ በመሆናቸውና የሥራውም ይዘት አሉታዊ የአካባቢ ተጽዕኖን መቀነስ በመሆኑ ለአካባቢው ነዋሪዎችም አወንታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡

የክትትልና ግምገማ ስርዓት

  • የኘሮጀክቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ጥራቱን የጠበቀና ስርዓቱን የተከተለ እንዲሆን የተለያዩ የክትትልና የግምገማ ሥርዓት የተዘረጋ ሲሆን ከዚህም አንዱ ለራሱ የሆነ አማካሪ በመቅጠር የሱፐርቪዥን ሥራው በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥጥር እየተደረገበት ይገኛል

ለ2008 የተጠየቀ አጠቃላይ እና ዝርዝር የበጀት ፍላጎት መግለጫ

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
19 የአዳዲስ ቅብብሎሽ ጣቢያ ግንባታ እና ነበር ጣቢያዎችን ማሻሻያ ፕሮጀክት   13,157,205 13,157,205 0 0 0
19.1 የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን 2,000,000 2,000,000 2,000,000 በጀቱ ከዚህ በፊት ለአማካሪው ላልተከፈለው ሥራ የሚውል ነው፡፡
19.2 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ3 ነባር ቅብብሎሽ ጣቢያ ማሻሻያና የ9 አዳዲስ ቅብብሎሽ ጣቢያ ግንባታ ሥራ ማከናወን 20,000,000 10,000,000 10,000,000 በበጀት ዓመቱ በሚገባው ውለታ መሠረት የቅድመ ክፍያ 20 በመቶ እና ሥራው 58 በመቶ የሚሰራ በመሆኑ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ክፍያ  የተያዘ በጀት ነው፡፡ ( ስራው ለ6 ወራት እንደሚከናወን ታሳቢ ተደርጓል፡፡)
19.3 የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን 1,200,000 800,000 800,000 በውል ስምምነቱ መሠረት በየወሩ ለሚያካሄደው የሱፐርቪዥን ሥራ በየወሩ 200,000 ብር የሚከፍል ሲሆን በዚህ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለ4 ወር ክፍያ ለመፈጸም የተያዘ በጀት ነው፡፡
19.4 የካሳ ክፍያ 357,205 357,205 357,205 ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡