የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ መገኛ ተፋሰሶች እንዳይሸረሸሩና ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ በያዝነው ክረምት 46 ሺህ 500 ችግኞችን ተክሏል፡፡ችግኞቹ የተተከሉት በለገዳዲ፣ ገፈርሳና ድሬ ግድቦች ዙሪያ እንዲሁም በፍሳሽ ማጣሪ ጣቢያዎች ላይ ሲሆን በቀጣይም 800 የሎሚ ችግኞችን በለገዳዲ ግድብ ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በባለስልጣኑ የውሃ መገኛ ተፋሰሶች አስተዳደርና ጥበቃ ዲቪዥን የስራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ታዬ 43 ሺህ የደን ዛፎች እና 3 ሺ 500 የፍራፍሬ ችግኞች በዚህ ክረምት መተከላቸውን ገልፀው፡፡እየተሰራ ያለው የፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የግድቦቹን ደህንነት ከመጠበቅ ባለፈ የአፈር መሸርሸርን በማስቀረቱ ምርታማነትን በማሳደግ፣ ለአርሶ አደሩ ሠርቶ ማሳያ በመሆን እንዲሁም ከፍራፍሬ ሽያጭ ገቢያቸውን በመጨመር በተፋሰሱ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡