የኘሮጀክቱ ሥም፡    የውኃ መባከን ቁጥጥር ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- ገቢ የማይሰበሰብበትን ውሃ መጠን በሂደት በመቀነስ ብክነትን መቆጣጠር፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- በባለስልጣኑ የአሰራር እና አገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና እና ውጤታማነት ለማምጣት፣ የሚባክነውን የውሃ መጠን ስትራቴጂክ በሆነ መንገድ ለመቀነስ እንዲሁም የሀብት እና ንብረት አያያዝ ስርአትን ለማሻሻል የሚያስችል ሥርዓት በመዘርጋት የውኃ ብክነትን መከላከል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • አዲስ የቢሊንግና አካውንቲን ሲስተም ማስጠናት
  • አዲሱን ቢሊንግና አካውንቲንግ ሲስተም መተግበር፣
  • የብክነት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ግዥ
  • ለአገልግሎት ቅጥያ መስመሮች (Service connection) የቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ፣

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2002 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 144,997,983 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

ይህ ፕሮጀክት ገቢ የማይሰበሰብበት ውሃ በአረጁ መስመሮች ምክንያት የሚባክን ውሃን፣ በህገወጥ ቅጥያ ምክንያት እና በተለያዩ ምክንያቶች ክፍያቸው የማይሰበሰብ የውሃ አቅርቦትን መጠን መቀነስን ትኩረት ያደረገ ሲሆን በተለይም በአረጁ መስመሮች ምክንያት የሚባክን ውሃና ወደ መስመር በመቀነስ የውሃ አቅርቦቱን መጨመር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

የሥራው አስፈላጊነት

ብነትን መቆጣጠር ከፈተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባና እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ድሀ ሀገሮች ደግሞ ያለውን ውስን ሀብት በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ ሲሆን፣ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ ሆኖበት የተጣራ ውሃና ካለምንም ጥቅም በመሬት ውስጥ መፍሰስ የሚያስከትለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀት ያስቀራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ገቢ ከማይሰበሰብባቸው የውሃ አገልግሎቶች ገቢ በመሰብሰብ የድርጅቱን ገቢ ማሣደግ ያስችላል፡፡

የሥራው ዓላማ

ገቢ የማይሰበሰብበትን ውሃ መጠን በሂደት በመቀነስ ብክነትን መቆጣጠር፡፡

የሥራው ግብ

በመረጃ መረብ የተደገፈ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ፣ የቆጣሪ ንባብ እንዲሁም የገንዘብ አሰባሰብ እና የአካውንቲንግ ምዝገባ ስርአት በመዘርጋት ቀልጣፋ እና ውጤታማ አሰራር እና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ይደረጋል፡፡

ያረጁ መስመሮችን መቀየርና ገንዘብ የማይሰበሰብበትን ውኃን ለመቀነስ የሚያስችሉ መሳሪያዎችን በስራ ላይ በማዋል የውኃ ብክነትን መከላከል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ይሄ ኘሮጀክት የድርጅቱን የብክነት ቁጥጥር አቅም የሚያሳድግ ሲሆን ለድርጅቱ ሆነ ተቋማዊ የብክነት መከላከል አቅም ያሳድጋል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • የአሴት/ ማቴሪያል ማኔጅመንት ጂ አይ ኤስ እና የሰው ሀይል አስተዳደር ሲስተም ግንባታ እና ትግበራ ማጠናቀቅ
  • ኦፕሬሽናል ድጋፍ ማድረግ

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የአረጁ መስመሮችን መቀየር፣
  • የአካባቢ የውሃ ፍሰትን መለካት፣
  • ክፍያ የማይሰበሰብበትን ቅጥያ መለየት፣
  • ዘመናዊ የመረጃ አሰባሰብና አደረጃጀት ሥርዓት መዘርጋት 

ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

  • የብክነት መመርመሪያ ማሣሪያዎች ግዥ፣
  • የቢሊንግና አካውንቲንግ ሲስተም ለመተግበር ያስችል ዘንድ ራሱን የቻለ ኮሚቴ፣

የአካባቢና የማሕበራዊ ትንታኔ

  • በመረጃ መረብ የተደገፈ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ፣ የቆጣሪ ንባብ እንዲሁም የገንዘብ አሰባሰብ እና የአካውንቲንግ ምዝገባ ስርአት በመዘርጋት ቀልጣፋ እና ውጤታማ አሰራር እና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
  • በተለያዩ የግንባታ ወቅት ከመሬት ውስጥ በሚመነጭ ውሃ ምክንያት የሚያጋጥም የግንባታ መጓተትና ተጨማሪ ወጪ በማስቀረት በከተማዋ ውስጥ የሚካሄዱትን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እንዲቀላጠፉ ያግዛል፡፡

በጀት /ጠቅላላና ዝርዝር ወጪ/

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የማዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
46 የውኃ መባከን ቁጥጥር ፕሮጀክት   12,474,000 0 6,500,000 0 5,974,000
46.1 ለኦፕሬሽን ድጋፍ ክፍያ መፈጸም 6,974,000 5,974,000 5,974,000 በተገባው ውለታ መሠረት ለሚከፈል ቀሪ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፤
46.2 የመያዥያ ክፍያ (ለክፍል 2 እና 3 ትግበራ) 6,500,000 6,500,000 6,500,000 በተገባው ውለታ መሠረት ለሚከፈል የመያዥያ ክፍያ ከመንግስት በጀት ለመሸፈን የተያዘ በጀት ነው፡፡