የኘሮጀክቱ ሥም፡     የደቡብ አቃቂ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ እና ፈሳሽ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ ክፍለ ከተሞች የሚያጠቃልል ሲሆን የፍሳሽ መስመሮቹ ጥናትና ዲዛይን የሚያከናወነው እ.ኤ.አ. በ2002 በተጠናው የፍሳሽ ማስተርፕላን የሚያካትታቸውን ቦታዎች ታሣቢ በማድረግ ይሆናል፡፡

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- በአቃቂ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙትን የፍሳሽ መስመር ያልተደረሰባቸውን ክፍለ ከተሞችና አካባቢዎች እንዲሁም የተገነቡትንና አዲስ የሚገነቡትን የኮንዶሚኒየም ቤቶች እና ሌሎች አካባቢዎች የፍሳሽ አገልግሎት በማዳረስ በተፋሰሱ ውስጥ የሚገኙትን ተጠቃሚ ማድረግ ይሆናል፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-60 ሺህ ሜ.ኩብ በቀን የማጣራት አቅም ያለውን የደቡብ አቃቂ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቅ የግንባታው ሥራው በቀጣይ 3 ዓመታት ውስጥ ማጠናቀቅ ነው፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ
  • የፍሳሽ ማጣሪያ ማሻሻያና ማጠናከሪያ ግንባታ ሥራ
  • የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2006 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2012 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 2,000,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እ.ኤ.አ በ2001—2002 ዓ.ም የአዲስ አበባን የፍሳሽ ማስተር ፕላን ክለሳ ኔድኮ (NEDECO) በተባለ አማካሪ አማካኝነት ማስጠናቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም ማስተር ፕላን ከተማ መሠረት የአቃቂ ፍሳሽ ተፋሰስ ፕሮጀክት ሁለት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

እነዚህም፡

ሀ/ የአቃቂ የፍሳሽ ተፋሰስ  መስመር ግንባታ’ ጥናትና ዲዛይን

ለ/ የአቃቂ አካባቢ የፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታ ናቸው

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት፡-

የአቃቂ ተፋሰስ አካባቢ በፈጣን እድገት በመልማት ላይ ያለ ሲሆን ከተወሠኑ ጥቂት አካባቢዎች በስተቀር በቂ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር የሌለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚገኘው የፍሳሽ ማጣሪያ አቅም አሁን ካለው የተፋሰሱ እድገት ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡

በአቃቂ ፍሳሽ ተፋሰስ ብዛት ያላቸው ኮንደሚኒየም ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ የተገነቡትም ተገቢ የሆነ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች የላቸውም፡፡ በተጨማሪም እንዱስትሪዎች እና ሌሎች የልማት ድርጅቶች ሥራዎች በማፋጠን ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህም መሠረት ከፍተኛ የሆነ የፍሳሽ ማስወገጃ ፍላጉቶች ከሕብረተሰቡ ቀርበዋል፡፡ ስለዚህ የዚህ ፕሮጀክት ተግባራዊ መሆንም እ.ኢ.አ ከ2020—2025 ያለውን የፍሳሽ የማስወገድ ፍላጎት በተገቢ ሁኔታ ምላሽ ይሰጣል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ፡-

አቃቂ ፍሳሽ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ ፍሳሽ መስመር ያልተደረሰባቸውን አካባቢዎች የተገነቡትንና አዲስ በመገንባት ላይ ያሉትን የኮንደሚኒየም ቤቶች ፋብሪካዎች ልማት ድርጅቶች ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር በማቀናጀት ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር በማቀናጀት የፍሳሽ ማሰባሰቢያ መስመሮችንና የፍሳሽ ማጣሪያ ፕላንት እንዲገነባ በማድረግ የህብረተሰቡን ፍላጎት እና ጤንነት በመጠበቅ ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ፡-

60 ሺህ ሜ.ኩብ በቀን የማጣራት አቅም ያለውን የደቡብ አቃቂ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቅ የግንባታው ሥራው በቀጣይ 3 ዓመታት ውስጥ ማጠናቀቅ ነው፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች፡-

ሥራውን ተግባራዊ በማድረግ በአካባቢው የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች የኮንዶሚኒየም ቤቶች ድርጅቶች እና ፋብሪካዎች የዘመናዊ ፍሳሽ መስመር አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

በዚህም ፡-

  • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
  • የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡
  • የአካባቢ ብክነትን ማስወገድና የተሟላ ጤና እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
  • የፀዳች አዲስ አበባ ብሎም ለቱሪዝም እንዱስትሪ እድገት የተመቻቸ ከተማ እንድትኖረን ያደርጋል፡፡
  • ተጨማሪ የመስኖ ሥራዎችን ለመስራት የተጣራውን ፍሳሽ ለአካባቢው ግብርና እንዲውል ማድረግ ይቻላል፡፡
  • የተጣራውን የፍሳሽ ለከርሰምድር ማሟያ (Ground Water recharge) እንዲውል ማድረግ ይቻላል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የአማሪ ቅጥር በመፈጸም የደቡብ አቃቂ ማጣሪያ ጣቢያ እና የመስመር ጥናትና ዲዛይን ክለሳ ስራ ማከናወን

የአካባቢ እና ነባራዊ ሁኔታዎች

በአማካሪ ድርጅት ከሚቀርቡ ጥናቶች አንዱና ዋነኛው ፕሮጀክቱ ሊያስከትለው የሚችለው አካባቢያዊ ተጽዕኖ ግምገማና ፕሮጀክቱን ተከትሎ የሚመጡ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዩች በጎና አሉታዊ ተጽእኖዎች የሚጠኑበት የጥናቱ ክፍል ነው፡፡

በጥናቱ መሠረት አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለማስቀረትና በጎ ጎኖችን ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ ያሰራል፡

የክትትልና ግምገማ ሥርዓት፡- 

በአማካሪው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ጥናቱን በሚገመግሙ ባለሙያዎች እየታዩ መዳበር የሚገባቸው ነጥቦች እንዲዳብሩ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የክትትል መመዘኛ ነጥቦችን በጨረታና በስምምነት ሰነዶች ላይ እንዲኖር ያደርጋል፡፡

የ2008 በጀት ፍላጎት

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
14 የደቡብ አቃቂ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ እና ፈሳሽ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት   24,563,928 0 23,956,127 0 0
14.1 ዝርዝር የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን 70,400,000 10,560,000 10,560,000 ጥናቱ የ1 ዓመት ሲሆን በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት ለኢንሰምሽን ሪፖርት የሚከፈል በጀት ነው፡፡
14.2 የካሳ ክፍያ መፈጸም 14,611,729 14,003,928 13,396,127 ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡