የኘሮጀክቱ ሥም፡    የገርቢ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- የሦስተኛው መጠጥ ውኃ አካል የሆነውን የገርቢ ግድብ ግንባታ እስከ 2012 በጀት ዓመት ድረስ በማጠናቀቅ እና በቀን ከ73ሺህ ሜ.ኩብ. በላይ ውኃ በማምረት ለከተማዋ ህብረተሰብ ማሰራጨት ነው፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የሦስተኛው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ታሳቢ ያደረጋቸውን የዲዛይን ፓራሜትሮች መገምገምና እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ማድረግ፣
  • ነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት አጠቃላይ የከተማውን ተጨማሪ የውሃ ፍላጎት መጠን ማስላት፣
  • የሚፈለገውን ተጨማሪ ውሃ ለማግኘት በሚያስችል መልኩ የሦስተኛው መጠጥ ውሃፕሮጀክት ለመተግበር የሚቻልባቸውን አማራጮች ማቅረብ፣
  • ጥናቱ አሁን ካለው የአዲስ አበባና አካባቢው ከተሞች መስፋፋት አንጻር መተግበር የሚያስችሉ ሁኔታዎች መኖራቸውን መገምገም፣
  • የገርቢ ግድብ ግንባታ ሥራ ማከናወን
  • የገርቢ ማጣሪያ ግንባታ ሥራ ማከናወን
  • የውኃ መስመር ዝርጋታ እና ተያያዥ ሥራዎች ማከናወን

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2004 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2012 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 3,000,000,000 ብር ይፈጃል ተብሎ ይገመታል 

መግቢያ

የከተማዋን የወደፊት የውኃ አቅርቦት ፍላጎት መሠረት ያደረገ ጥናት ከዚህ በፊት የተጠና ሲሆን በጥናቱ መሠረትም ይህ ፕሮጀክት ቢተገበር እስከ 20 ዓመታት ድረስ ያለምንም ችግር የከተማዋ የውኃ ፍላጎት መሟላት እንደሚችል ያሳያል፡፡ ሆኖም በተለያዩ ምክያቶች የተነሳ ጥናቱ እስካሁን ድረስ ሳይተገብር ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ጥናቱን በመከለስ የሚተገበርበትን አማራጭ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ለዚህም ያስችል ዘንድ ይህን ፕሮጀክት ተቀርጿል፡፡

የሥራው አስፈላጊነት

ይህ ኘሮጀክት ተፈጻሚ ሲሆን የገርቢ ግድብ ግንባታ ሥራ ተግባራዊ የሚሆንበትን ዝርዝር ጥናት በማስቀመጥ የግድብ ሥራው ተግባራዊ እንዲሆን ሚያስችል ይሆናል፡

የሥራው ዓላማ

የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ

የሥራው ግብ

የሦስተኛው መጠጥ ውኃ አካል የሆነውን የገርቢ ግድብ ግንባታ እስከ 2012 በጀት ዓመት ድረስ በማጠናቀቅ እና በቀን ከ70ሺህ ሜ.ኩብ. በላይ ውኃ በማምረት ለከተማዋ ህብረተሰብ ማሰራጨት ነው፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  • የተጠናቀቀ የገርቢ ግድብ፣ ማጣሪያ ጣቢያ እና የውኃ መስመር ዝርጋታ
  • የከተማዋ ሕብረተሰብ ተጨማሪ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ያገኛል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም 15 በመቶ የገርቢ ግድብ ግንባታ ሥራ ማከናወን
  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም 15 በመቶ የገርቢ ማጣሪያ ግንባታ ሥራ ማከናወን
  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም 11 በመቶ የውኃ መስመር ዝርጋታ እና ተያያዥ ሥራዎች ማከናወን
  • የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን
  • የወሰን ማስከበር ሥራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የዝርዝር ጥናት ዲዛይን ሥራ የሚያከናውን አማካሪ መቅጠርና የጥናት ሥራውን መከታተል፣
  • ለግንባታ ሥራው የግንባታ ተቆጣጣሪ አማካሪ ድርጀት በመቅጠር ሥራው በጊዜው እና በጥራት እንዲጠናቀቅ በቂ ክትትል ማድረግ

ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

  • ግንባታውን የሚቆጣጠር አማካሪ የሚቀጠር ሲሆን አስፈላጊ ባለሙያዎችን በሙሉ አማካሪ ድርጅቱ ያቀርባል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርአት

  • የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ለመከታተል ሳምንታዊና ወርሃዊ ሪፖርቶችን መከታተል፡፡
  • የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ በመገምገም እቅዱን መከለስ

በጀት /ጠቅላላና ዝርዝር ወጪ/

ይህንን ሥራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የማዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
6 የገርቢ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት   70,000,000 70,000,000 0 0 0
6.1 የተቋራጭቅጥርበመፈጸም የገርቢ ግድብ ግንባታሥራ ማከናወን 495,000,000 10,000,000 10,000,000 በሚገባው ውለታ መሠረት ለ2008 ለሚሰሩ ሥራዎች የተያዘ በጀትነው፡፡
6.2 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የገርቢ ማጣሪያ ግንባታ ሥራ ማከናወን 1,551,000,000 10,000,000 10,000,000 በሚገባው ውለታ መሠረት ለ2008 ለሚሰሩ ሥራዎች የተያዘ በጀትነው፡፡
6.3 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የውኃ መስመር ዝርጋታ ሥራማከናወን 1,254,000,000 10,000,000 10,000,000 በሚገባው ውለታ መሠረት ለ2008 ለሚሰሩ ሥራዎች የተያዘ በጀትነው፡፡
6.4 የሱፐርቪዥን ክፍያ ሥራ 135,000,000 20,000,000 20,000,000 በተገባው ውለታ መሠረት ለአማካሪው የሚከፍል የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ክፍያ ነው፡፡
6.5 የካሳ ክፍያ መፈጸም 120,000,000 20,000,000 20,000,000 ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡