የኘሮጀክቱ ሥም፡    የግድቦች አካባቢ ተፋሰስ እንክብካቤ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በለገዳዲ፣ ገፈርሳ እና ድሬ ግድቦች

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- ግድቦቹ ለታቀደላቸው የሥራ ዘመን ያህል የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረግ፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- በግድቦች አካባቢ የተፋሰስ እንክብካቤ ሥራዎች በማከናወን ግድቦችን ከአካባቢ መራቆት መግታትና ወደ ግድቦቹ የሚገባውን የደለል መጠን መቀነስ፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የግድቦች አካባቢ ተፋሰስ እንክብካቤ /Master Plan Review) ጥናት ማከናወን፣
  • የተፋሰስ እንክብካቤ ግንባታ ሥራ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2002 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 90,747,500 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

 

መግቢያ

ለከተማዋ የውሃ ምንጭ ሆነው የሚያገለግሉትን 3 የገፀ ምድር ውሃ ምንጭ የሆኑትን ግድቦች ከአካባቢ መራቆትና በደለል ከመሞላት እንዲሁም ከእንስሳትና ከሰው ጣልቃገብነት ለመከላከልና ለመንከባከብ የሚያስችል ሥራ ለመስራት የተጠናውን ማስተር ኘላን ተፈጻሚ በማድረግ ግድቦቹ በታቀደላቸው የሥራ ዘመን ውስጥ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻልን መሠረት ያደረገ ስራ ነው፡፡

የሥራው አስፈላጊነት

ይህ ኘሮጀክት ተፈጻሚ ሲሆን ግድቦቹን በደለል ከመሞላትና ሰዎችና እንስሳት ወደ አካባቢው ውሃ ፍለጋ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ማስቀረት ያስችላል፡፡

የሥራው ዓላማ

ግድቦቹ ለታቀደላቸው የሥራ ዘመን ያህል የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረግ፡፡

የሥራው ግብ

በግድቦች አካባቢ የተፋሰስ እንክብካቤ ሥራዎች በማከናወን ግድቦችን ከአካባቢ መራቆት መግታትና ወደ ግድቦቹ የሚገባውን የደለል መጠን መቀነስ የሚያስችል የግንባታ ሥራ ይጠናቀቃል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

በግንባታው ወቅት በአካባቢው ለሚኖሩ ነዋሪዎች ጊዜያዊ እና ቋሚ የሆነ የሥራ እድልን ይፈጥራል፡፡ ከግንባታው መጠናቀቅም በኋላ፡-

  • የግድቦቹ የመያዝ አቅም በደለል ምክንያት እንዳይቀንስ ያደርጋል፣
  • ተጨማሪ ውሃ መያዝ የሚችሉ ግድቦችን Cheek dames? በመገንባት ተጨማሪ ውሃ ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል፣
  • ግድቦቹ ያላቸውን ወቅታዊ የመያዝ አቅም ትክክለኛ መረጃ ይሰጣል በዚህም ለቀጣይ ሥራዎች ወሳኝ የሆነ ግብአትን ይፈጥራል፣
  • ለአካባቢው ነዋሪዎች የንፁሕ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን እንዲገነቡ ያስችላል፣
  • የአካባቢው ሕብረተሰብ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ያገኛል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • በተፋሰስ አካባቢ ከሚቆፈሩ 9 መለስተኛ ጉድጓዶች ውስጥ የቀሪ 6 ጉድጓዶች ቁፋሮ ስራ ማጠናቀቅ፣
  • የዕቃ አቅራቢ ቅጥር በመፈጸም የ9 ፓምፕ ዕቃ አቅርቦትና ተከላ ሥራ ማከናወን፣
  • በራስ ኃይል የውኃ መስመር እና ሪዘርቫየር ጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን፣
  • በተጠናው ጥናት መሠረት በራስ ኃይል የውኃ መስመር ዝርጋታ እና ሪዘርቫየር ግንባታ ሥራ ማከናወን፣
  • የወሰን ማስከበር ሥራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የግንባታ ሥራውን መከታተል፤

የአካባቢና የማሕበራዊ ትንታኔ

በአካባቢው የተለያዩ ዘርፈ ብዙ የማህበራዊ ሥራወች የሚሰሩ በመሆናቸውና የሥራውም ይዘት አሉታዊ የአካባቢ ተጽዕኖን መቀነስ በመሆኑ ለአካባቢው ነዋሪዎችም ሆነ ለስነምህዳሩ አወንታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡

በጀት /ጠቅላላና ዝርዝር ወጪ/

ይህንን ሥራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የማዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
10 የግድቦች አካባቢ ተፋሰስ እንክብካቤ ፕሮጀክት   43,050,000 43,050,000 0 0 0
10.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ9 መለስተኛ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ማከናወን 71,670,243 30,000,000 30,000,000 በተገባው ውል ስምምነት መሠረት ለ9 ጉድጓዶች ለሚከፈል ቀሪ ክፍያ በጀቱ ተይዟል፡፡
10.2 የ9 ፓምፕ ግዥ ማከናወን 5,400,000 5,400,000 5,400,000 ከዕቃ አቅርቦቱ ጋር በተያያዘ በ2008 በጀት ዓመት ለሚከፈል ክፍያ የተጠቀሰው ብር ተይዟል፡፡
10.3 ለተቆፈሩ የውኃ ጉድጓዶች የኤሌክትሪክ ኃይል ማስገባት 7,650,000 7,650,000 7,650,000 ከዚህ ቀደም ለ70ሺህ ውኃ አቅርቦት ለጉድጓድ ትራነስፎርመር አቅርቦት የተያዘውን በጀት መነሻ በማድረግ እነዚህ ጉድጓዶች የሚፈልጉት ትራንሰፎርመር አቅም አነስተኛ እንደሚሆን ግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ ፕሮጀክት ለተቆፈሩ 9 ጉድጓዶች ትራንሰፎርመር አቅርቦት በጀቱ ተይዟል፡፡