የኘሮጀክቱ ስም፡- ያልተማከለ የፍሳሽ አገልግሎት ፕሮጀክት/ለኮዬ ፍቼ የኮንደሚኒየም አካባቢዎች ያልተማከለ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት

አስፈጻሚው አካል በአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ  ፡- በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተመረጡ ክ/ከተሞች ( የኮንደሚንየም ቤቶች ግንባታ የሚከናወንባቸው) እንዲሁም ሌሎች ከቤቶች ልማት ኤጀንሲ ጋር በመነጋገር የሚወሰኑ ይሆናሉ፡፡

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ

ይህ ኘሮጀክት የተቀረፀበት ምክንያት የፍሣሽ ማስተር ኘላኑ ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ለተገነቡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ፍሣሻቸውን አካባቢን ሳይበክል በዘላቂነት ማስወገድ እንዲችሉ ጥናት ማካሄድ እና የግንባታ ሥራ ለማከናወን ነው፡፡ ኘሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን አገልግሎት የሚሰጠው ለኮንዶሚኒየም ቤቶች ብቻ ሣይሆን በአካባቢው ለሚገኙ የልማት ተቋማትና ቤቶችም ጭምር ይሆናል፡፡

የኘሮጀክቱ ግብ

ዘመናዊ የፍሳሽ አገልግሎት ያልተዳረሰባቸውንና በማስተር ፕላኑ ውስጥ ያልተካተቱትን አካባቢዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ

በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማካሄድ
  • ያልተማከለ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ማከናወን

የሚጠበቅ ውጤት፣

በተለያዩ ክ/ከተሞች የተገነቡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች እና በተጠናው የፍሳሽ ማስተር ፕላን ውስጥ ያልተካተቱ አካባቢዎች የፍሣሽ ማስወገጃ ችግር ያለባቸው በመሆኑ ይህን ኘሮጀክት ተግባራዊ በማድረግ መፍትሄ ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ኘሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን በኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚኖሩ ሰዎች እና በአካባቢው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ

  • በ2004 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ

  • በ2009 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት ግምት

  • በሚጠናው የኢንጂነሪንግ ግምት (Engineering Estimation) መሠረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

መግቢያ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን እ.አ.አ በ2ዐዐ2 ዓ.ም የአዲስ አበባን ፍሣሽ ማስተር ኘላን ክለሳ ማስጠናቱ ይታወቃል፡፡ ይህ የፍሣሽ ማስተር ኘላን ሁሉንም የአዲስ አበባ አካባቢዎች የማያዳርስ በመሆኑ የዚህ ጥናት አስፈላጊነት ጉልህ ሆኖ ታይቷል፡፡ ስለሆነም በዚህ ማስተር ኘላን ጥናት ውስጥ ላልተካተቱ የከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ከቤቶች ለሚለቀቁ ፍሣሾች የማስወገጃ መስመሮች እና አነስተኛ ማጣሪዎች አስፈላጊ ሆነው ስለተገኙ በ2ዐዐ4 የበጀት ዓመት የጥናትና ዲዛይን ሥራዎቻቸው ተጠናቀው ወደ ግንባታ የሚያስኬዱ ቅድመ ሁኔታዎች ይመቻቻሉ፡፡

የኘሮጀክቱ አስፈላጊነት

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት እያደረጋቸው ካሉ ጥረቶች ውስጥ አንዱና ዋናው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ነው፡፡

መስተዳድሩ በከተማዋ በሁሉም ክ/ከተሞች ግንባታውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ በጉለሌ፣ በአራዳና በሌሎችም ክ/ከተሞች የተገነቡ ቤቶች በአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣና ማስተር ኘላን ውስጥ ያልተካተቱ ስለሆነ ለነዋሪዉ የፍሣሽ ማስወገጃ መስመሮችን ለመዘርጋት በተጨማሪም ማጣሪያ ለመገንባት የዚህ ኘሮጀክት መቀረጽ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

የኘሮጀክቱ ዓላማ

በጉለሌ፣ በአራዳ፣ በኮልፌ ቀራኒዮና በጥናቱ መሠረት በሚገኙ ሌሎች ክ/ከተሞች የተገነቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች እና ሌሎች ድርጅቶች የፍሳሽ ማስወገጃ ችግር ያለባቸው በመሆኑ የፍሳሽ መሰብሰቢያ መስመሮችን እና የፍሳሽ ማጣሪያዎችን እንዲገነቡ በማድረግ በአካባቢና በጤና ላይ የሚከሰተውን ችግር ማስቀረት ብሎም የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን ማሳደግ ነው፡፡

የኘሮጀክቱ ግብ

የፍሳሽ መሰብሰቢያ መስመሮችና የማጣሪያ ኘላንት እንዲገነባ በማድረግ ፍሳሹ በአካባቢና በጤና ላይ የሚያስከትለውን ብክለት ማስወገድ ነው፡፡ በዚህም ኮንዶሚኒየም ቤቶች ድርጅቶች እና መኖሪያ ቤቶች የፍሣሽ መስመሮቻቸውን የሚያገናኙበት ዋና የፍሣሽ መስመር እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ኘሮጀክቱን ተግባራዊ ሲሆን በኮንደሚኒየም ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች እና በፍሳሽ ማስተር ፕላኑ ያልተካተቱ አካባቢዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ሚሆኑ ሲሆን በዚህም፡

  • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
  • የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም ለተመረጡ የኮንደሚኒየም አካባቢዎች ከ3 ያላነሱ ያልተማከለ ፍሳሽ ማስወገጃ ግንባታ ሥራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

ግንበታውን በበቂ ጊዜና የጥራት ደረጃ ለመፈጸም የሳይት ክትትል መሐንዲስ ጽ/ቤቱ በበቂ ሁኔታ ያሟላል፡፡

ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

ኘሮጀክቱን የሚያጠናና በግንባታም ወቅት ሥራውን የሚከታተል አማካሪ የሚመረጥ ሲሆን፣ አማካሪው የተጠየቀውን የሙያ አይነትና ባለሙያ በማቅረብ ጥናቱን  ያከናውናል፡፡ በተጨማሪም በግንባታ ወቅት ሥራውን የሚከታተሉ መሃንዲሶችን ያቀርባል፡፡ በባለቤቱ በኩልም እንዲሁ ሥራውን የሚከታተሉ መሃንዲሶች  ይመደባሉ፡፡

የአካባቢ እና ነባራዊ ሁኔታዎች

በአማካሪ ድርጅቱ ከሚቀርቡ ጥናቶች አንዱና ዋነኛው ኘሮጀክቱ ሊያስከትል የሚችለው አካባቢያዊ ተጽዕኖ ግምገማና ኘሮጀክቱን ተከትሎ የሚመጡ የኢኮኖሚና ሶሻል በጎና አሉታዊ ተጽእኖዎች የሚጠኑበት የጥናቱ ክፍል ነው፡

በጥናቱ መሠረት አሉታዊ ተጽኖዎችን ለማስቀረትና በጎ ጐኖችን ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ ያሰራል፡፡

የክትትልና ግምገማ ሥርዓት

ከአማካሪው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ጥናቱን በሚገመግሙ ባለሙያዎች እየታዩ መዳበር የሚገባቸው ነጥቦች እንዲዳብሩ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የክትትል መመዘኛ ነጥቦችን በጨረታና በስምምነት ሰነዶች ላይ እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡ የግንባታ ሥራውም በአማካሪው በሚያቀርበው የሥራ ክትትል ስልት መሠረት እና ባለቤቱ በሚመድባቸው መሃንዲሶች የሥራ ሂደት ክትትል ያደርጋል፡፡

ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች

ኘሮጀክቱን ተግባራው በማድረግ ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች እንደሚከተለው ይገለፃሉ፡፡

ሀ/ ሥጋቶች

  • በግንባታ ወቅት የወሰን ማስከበር ችግር፣

ለ/ ምቹ ሁኔታዎች

  • ኘሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድርግ የመንግስት ቁርጠኝነት፣
  • በአካከባቢው ያለው የኢንቨስትመንትና ልማት መስፋፋት፣
  • በአካባቢው የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት፤ ዘመናዊ የፍሳሽ መሰብሰቢያ እና ማጣሪያ ኘላንት የሚፈልጉ መሆናቸው፣

የ2008 በጀት ፍላጐት

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
16 ለኮዬ ፍቼ የኮንደሚኒየም አካባቢዎች ያልተማከለ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት   310,400,000 310,400,000 0 0 0
16.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈፀም ያልተማከለ ፍሳሽ ማስወገጃ ግንባታ ማከናወን 1,104,000,000 300,000,000 300,000,000 አጠቃላይ ሥራው የ1 ዓመት ሲሆን በሚገቡ ውለታዎች መሠረት የ1ዱ ስራ በሚቀጥለው የበጀት አመት 91 በመቶ የሚጠናቀቅ ሲሆን የቀሪ 2ቱ ደግሞ 59 በመቶ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የግንባታው አብዛኛው ክፍያ በ2008 በጀት ዓመት ለመፈፀም የተያዘ በጀት ነው፡፡ መያዥያ እና ቀሪ ክፍያዎች በድምሩ 10 በመቶ የሚደርስ ክፍያ ወደ 2009 በጀት ዓመት የሚሻገር ይሆናል፡፡
16.2 የሱፐርቪዥን ሥራ ማከናወን 12,000,000 10,400,000 10,400,000 በውል ስምምነቱ መሠረት በየወሩ ለሚያካሄደው የሱፐርቪዥን ሥራ በየወሩ የሚከፍል 1 ሚሊየን ብር ሲሆን በዚህ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለ12 ወር በየወሩ ክፍያ ለመፈጸም የተያዘ በጀት ነው፡፤