የኘሮጀክቱ ሥም፡         ጦር- ኃይሎች መካኒሣ ቤረጽጌና ጎፋ አካባቢ የፍሳሽ አቃፊ ግንብ ግንባታ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡       በአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ   ጦር- ኃይሎች መካኒሣ ቤረጽጌ ጎፋ አካባቢ

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን አገልግሎት ማሻሻል፣

የኘሮጀክቱ ግብ በተጠቀሱት አካባቢዎች የፍሳሽ መስመር አቃፊ ግንባታ በማካሄድ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች አገልግሎት እንዲሻሻል ይደረጋል፡፡

በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን
  • ለአቃፊ ግንብ ሥራው የጨረታ ሰነድ በማዘጋጀት፣ጨረታ በማውጣት ከአሸናፊው ኮንተራክተር ጋር ውለታ መፈራረም፣
  • ግንባታ ማከናወን

የሚጠበቅ ውጤት

  • የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች አገልግሎት የተሻለ ይሆናል

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ

  • በ 2004

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ

  • በ 2007

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት ግምት

  • 12,000,000

መግቢያ

በአ.አ.ው.ፍ.ባ ከተማዋን የፍሳሽ ማስወገጃ መሥመር ለማዳረስ በጦር ኃይሎች መካኒሣ አካባቢ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ወጭ የሰራቸው የፍሳሽ ማስወገጃ መሥመሮች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ሆኖም ከግዜ ወደ ግዜ የወንዙ ጠርዝ እየተሸረሸረ’ እየተናደ የተገነቡትን የፍሳሽ መሥመሮች እና በወንዙ ዳርቻ ተሠርተው የተገኙ መኖሪያ አካባቢዎችን የመናድ አደጋ እንደሚያጋጥማቸውና አገልግሎት እንደሚያሳጣቸው ይታያል፡፡

በዚህም መሠረት ይህን ችግር የሚታይባቸውን ቦታዎች ከዚህ ችግር ለማስቆም እና የተሸለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የአቃፊ ግንብ ሥራ በመስራት አስፈላጊ ሆኖ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ አስፈላጊነት፡

  • የፍሳሽ መስመሮቹን ከመሸርሸር በመከላከል አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡

የፕሮጀክቱ አላማ፡

  • የአቃፍ ግንብ ግንባታ በማከናወን የፍሳሽ መስመሮች እና ማንሆሎች ከመሸርሸር መከላከል ነው፡

ፕሮጀክቱ ግብ፡

  • ተጠቂ የሆኑ የፍሳሽ መሥመሮች እና ማንሆሎች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተተቃሚዎች

  • ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብ እንዲኖር ያደርጋል፡
  • የአካባቢ ብክለትን ይከላከላል፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች

  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የፍሳሽ መስመር አቃፊ ግንብ ስራ ማከናወን

የአፈፃፀም ስልቶች

  • የፕሮጀክት ክትትል ለማያስፈልጋቸው ተግባራት የዕለት ተዕለት ቁጥጥር ማካሂድ

የአካባቢና ማህበራዊ ትንታኔ

የግንባታ ሥራው ለአገር መለሰስተኛ ተቋራጮች ጥሩ የሥራ ዕድል በመክፈት ማህበራዊ ጠቀሜታ ይሰጣል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርአት

  • የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ለመከታተል ሳምንታዊና ወርሃዊ ሪፖርቶችን መከታተል፡፡
  • የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ በመገምገም እቅዱን መከለስ

ሥጋትና ምቹ ሁሌታዎች

  • የግንባታ ግብአቶች በበቂ ሁኔታና በታሰበ ጊዜ አለመገኘት
  • የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ለፕሮጀክቶች ተግባራዊ በሙሉ አቅማቸው መትጋት

የፕሮጀክቶቹ አጠቃላይ በጀት 894,010 ብር ሲሆን ዝርዝሩ እንደሚከተለው ነው

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
47 ጦር-ኃይሎች መካኒሣ አካባቢ የፍሳሽ አቃፊ ግንብ ግንባታ ፕሮጀክት   894,010 0 894,010 0 0
47.1 የፍሳሽ መስመር አቃፊ ግንብ ስራ ማከናወን 12,715,796 317,895 317,895 የግንባታ ስራው ሙሉ በሙሉ የሚያልቅ በመሆኑ ለቀጣዩ የ2008 በጀት አመት ቀሪ የ2.5 በመቶ የመያዣ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡
47.2 የካሳ ክፍያ 576,115 576,115 576,115 ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡