ህብረት ስምምነቱ የተፈረመው በውሃና ፍሳሽ በባለስልጣን ማኔጅመንት እና በመሠረታዊ የሠራተኞች ማህበር መካከል ነው፡፡
ህብረት ስምምነቱ ከዚህ በፊት ለ14 ዓመታት በተግባር ላይ የቆየውን 9ኛውን ስምምነት በመተካት በቀጣይ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ሠራተኞች በሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ልክ ተጠቃሚ በማድረግ ባለስልጣኑን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ ህበረት ስምምነቱን በማዳበር ተቋሙን እና ሠራተኛውን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሰነድ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
የሠራተኛ ማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ወርቁ አንዱለም በበኩላቸው ህብረት ስምምነቱ የጋራ ተቀባይነት ያለው ሰነድ እንዲሆን እንደተደከመበት ገልፀው በዝግጅት ሂደቱም ከተቋሙ ማኔጅመንት እና ከሠራተኛ ማህበሩ አስተዋፅ ላበረከቱ አመራር እና ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ስምምነቱን የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ እና የባለስልጣኑ መሠረታዊ የሠራተኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ ወርቁ አንዷለም ፈርመዋል፡፡