ራዕይ ሠንቀናል! ለላቀ ድል ተነስተናል” በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ ታስቦ የሚውለውን የሠንደቅ ዓላማ ቀንን በማስመልከት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በዓሉን በፓናል ውይይት አከበረ፡፡ በዕለቱ የኢትዮጵያ የህዝብ መዝሙርም በመዘመር የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በእለቱ በቀረበው ሰነድ ላይ የአንድነት፣ የሉዓላዊነት እና የህብረ ብሔራዊ እኩልነት መገለጫ የሆነው የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ከትውልድ ትውልድ በቅብብሎሽ እዚህ የደረሰው ባለፉት አባቶቻችን ተጋድሎ መሆኑ ተዘክሯል፡፡ በተያያዘም በሠንደቅ ዓላማ ምንነት፣ ትርጓሜ እና አጠቃቀም ዙሪያ ህገ መንግስቱን መሠረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቧል፡፡

ሰነዱ የረጅም ታሪክ ባለቤት፣ የበርካታ ኃይማኖቶች፣ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መገኛ የሆነችው ሃገራችን ኢትዮጵያን

ከባለፈው ጨቋኝ የአገዛዝ ስርዓት ነፃ ለማውጣት የተደረገውን መራራ ትግል የሚያብራራ ሲሆን፣ በትጥቅ ትግሉ የተገኘውን ድል ተከትሎም የኢህአዴግ መንግስት ስልጣን ከያዘበት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸው ተጠብቆ፣ የኃይማኖቶች እኩልነት ተረጋግጦ፣ ሰላም መረጋጋትና ዴሞክራሲ ሰፍኖ በኢኮኖሚ የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ መቻሉ ተገልጿል፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ በ26 ዓመታት ውስጥ ልማታዊ እንቅስቃሴዎች የታዩበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተገኘው የድል ፍሬዎች ከኢኮኖሚ አንፃር የራስን አቅም ከማጎልበት ባለፈ ለሌሎች ሀገራትም ምርቶቻችንን ወደ ውጭ የላክንበት መሆኑ ተወስቷል፡፡

በመጨረሻም በቀረበው የመወያያ ሠነድ ላይ ከቤቱ ለቀረበው