ከፍተኛ የውሃ ተጠቃሚዎች የባለስልጣኑን ውሃ ለመቆጠብ በሚያስችላቸው አማራጭ ዙሪያ ውይይት አደረጉ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በደሊቨሪ ዩኒት የታቀዱ ተግባራትን ከማሳካት አንፃር በውሃ አቅርቦት ዙሪያ እያጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶች ላይ በወር በአማካኝ ከ500 ሜትር ኪዩብ በላይ የባለስልጣኑን ውሃ ከሚጠቀሙ 150 ድርጅቶች ጋር ቅዳሜ ህዳር 30/2010ዓ.ም በጊዮን ሆቴል ውይይት አድርጓል፡፡ የውሃ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መጨረሻ የከተማውን የውሃ አቅርቦት በቀን...