ይህን ያውቁ ኑሯል?

በብዙ ውጣ ወረድ እና ውስብስብ ሂደት ተመርቶ ወደ እያንዳንዳችን ቤት፣ተቋማት እና ድርጅቶች የሚሰራጨው የመዲናዋ የውሃ ጥራት የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መስፈርትን በማሟላት ነው፡፡ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ምንም እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት የሚያዘው  ከአዲስ አበባ ህዝብ ቁጥር አንጻር በቀን 18 ናሙናዎች እንዲወሰድ ቢሆንም በየእለቱ ከማጠራቀሚያ ፣መግፊያ ጣቢያዎች እና ግለሰቦች ቤት ሰላሳ(30) ናሙና...

ለዓለም የውሃ ቀን የተዘጋጀ ፕሬስ ሪሊዝ

የዓለም የውሃ ቀን በዓለም ለ27ኛ ጊዜ ‘Leaving no one behind’ በሃገራችን ደግሞ ለ26ኛ ጊዜ “ንፁህ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ”  በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ በዓሉ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በፈረንጆቹ 2030 ሁሉንም ህብረተሰብ የውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የተያዘውን አጀንዳ ታሳቢ በማድረግ ይከበራል፡፡  የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣንም በውሃ አቅርቦት ፣...

ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታና ቅጥያ ስራዎች በህብረተሰብ ተወካዮች ተጎበኙ፡፡

ባለስልጣኑ የመዲናዋን የፍሳሽ አወጋገድ ዘመናዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ሲሆን የጉብኝቱ አላማም ፍሳሽ በመስመር ወደ ማጣሪያ ጣቢያ እንዲገባ የተዘረጉ መስመሮችን መሰረት በማድረግ ነዋሪው ከቤቱ ቅጥያ እንዲያሰራ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ፡፡ በባለስልጣኑ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር ባሉ ሁሉም ወረዳች በተሰራ የመስመር ዝርጋታ እና ቤት ለቤት ቅጥያው ላይም 12 ተቋራጮች እና በ47 ጥቃቅን አነሰተኛ ማህበራት ተሳትፈዋል...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ባለፉት 8 ወራት ከ27 ኪሎ ሜትር በላይ ያረጁ መለስተኛ የውሃ መስመሮችን ቀየረ፡፡

የመስመር ቅየራ የተደረገው በባለስልጣኑ 8 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አማካኝነት ሲሆን ባለፉት ስምንት ወራት 28 ኪ.ሜ መለስተኛ መስመር ለመቀየር ታስቦ የዕቅዱን 94.41% ማከናወን ተችሏል፡፡ ከዚህ በፊት ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩና ያረጁ የብረት መስመሮች በፕላስቲክ የውሃ መስመሮች መቀየራቸው ባለስልጣኑ አምርቶ የሚያሰራጨውን ንፁህ ውሃ ከብክነት እና ብክለት በማዳን በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ሠራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ

ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ሙሉ ጤነኛ የሆነ ማንኛውም ዜጋ በየ 3 ወሩ ደም ቢለግስ የአዕምሮ እርካታ ከማግኘቱ በተጨማሪ በወሊድ ምክንያት ደም አጥተው የሚሞቱ እናቶቻችን እና በተለያየ ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ግለሰቦችን ህይወት መታደግ ይቻላል፡፡ “እኛ ጤናማ ሆነን ደም ካልሰጠን የታመሙትን ማዳን አንችልም…!” ያሉት የባለስልጣኑ ሠራተኞች በደም እጦት ምክንያት ህይታቸውን ማትረፍ ለማይችሉ ዜጎች እንዲውል በበጎ...