ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታና ቅጥያ ስራዎች በህብረተሰብ ተወካዮች ተጎበኙ፡፡

ባለስልጣኑ የመዲናዋን የፍሳሽ አወጋገድ ዘመናዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ሲሆን የጉብኝቱ አላማም ፍሳሽ በመስመር ወደ ማጣሪያ ጣቢያ እንዲገባ የተዘረጉ መስመሮችን መሰረት በማድረግ ነዋሪው ከቤቱ ቅጥያ እንዲያሰራ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ፡፡ በባለስልጣኑ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር ባሉ ሁሉም ወረዳች በተሰራ የመስመር ዝርጋታ እና ቤት ለቤት ቅጥያው ላይም 12 ተቋራጮች እና በ47 ጥቃቅን አነሰተኛ ማህበራት ተሳትፈዋል...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ባለፉት 8 ወራት ከ27 ኪሎ ሜትር በላይ ያረጁ መለስተኛ የውሃ መስመሮችን ቀየረ፡፡

የመስመር ቅየራ የተደረገው በባለስልጣኑ 8 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አማካኝነት ሲሆን ባለፉት ስምንት ወራት 28 ኪ.ሜ መለስተኛ መስመር ለመቀየር ታስቦ የዕቅዱን 94.41% ማከናወን ተችሏል፡፡ ከዚህ በፊት ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩና ያረጁ የብረት መስመሮች በፕላስቲክ የውሃ መስመሮች መቀየራቸው ባለስልጣኑ አምርቶ የሚያሰራጨውን ንፁህ ውሃ ከብክነት እና ብክለት በማዳን በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ሠራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ

ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ሙሉ ጤነኛ የሆነ ማንኛውም ዜጋ በየ 3 ወሩ ደም ቢለግስ የአዕምሮ እርካታ ከማግኘቱ በተጨማሪ በወሊድ ምክንያት ደም አጥተው የሚሞቱ እናቶቻችን እና በተለያየ ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ግለሰቦችን ህይወት መታደግ ይቻላል፡፡ “እኛ ጤናማ ሆነን ደም ካልሰጠን የታመሙትን ማዳን አንችልም…!” ያሉት የባለስልጣኑ ሠራተኞች በደም እጦት ምክንያት ህይታቸውን ማትረፍ ለማይችሉ ዜጎች እንዲውል በበጎ...