ባለስልጣኑ ከ4.7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የፍሳሽ መስመር ክዳን (ማንሆል) ተሰርቋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ2012 በጀት ዓመት በከፍተኛ እና መለስተኛ የፍሳሽ መስመሮች ላይ የገጠማቸውን 472 የፍሳሽ መስመር ክዳን (ማንሆል) ተሰርቋል፡፡ ከተሰረቁት ማንሆሎች 321 የሚሆኑት የብረት ክዳኖች ሲሆኑ 151ዱ ደግሞ የኮንክሪት ክዳኖች ናቸው፡፡ እነዚህ ክዳኖች በገንዘብ ሲተመኑም 4 ሚሊዮን 794 ሺህ ብር በላይ የወጣባቸው ናቸው፡፡ በማንሆል ስርቆት ምክንያት ወደ ፍሳሽ መስመር በሚገቡ ጠጣር እና...