የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ለ76 ማህበራት ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የስራ ዕድል ፈጠረ ፡፡

የስራ ዕድሉ የተፈጠረው በበጀት ዓመቱ ባለፍት ስምንት ወራት ውስጥ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁና በ76 ማህበራት ለታቀፉ 710 ስራ አጥ ዜጎች ነው፡፡ የስራ እድሉ የተፈጠረው በውሃ ቆጣሪ ንባብ፣ ይሃ መስመር ዝርጋታ፣ የፍሳሽ መስመር ቅጥያና ዝርጋታ፣ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ፣ የፍሳሽ እና የውሃ ማንሆል ግንባታ፣ የአጥር ስራ፣ የፓናል ቦርድና ፓምፕ ቤት ግንባታ እንዲሁም የጥበቃና መቆጣጠሪያ ቤት ግንባታ የስራ ዘርፎች...

ጥፋት ወይስ ልማት !

የህዝበ ሀብት በሆነው የፍሳሽ መሰረተ ልማት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ዛሬም ቀጥሏል ፡፡ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ፣ መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ እስከ ቆሬ ድልድይ ፣ከቆሬ ድልድይ ወደ አላርት ሆስፒታል የሚወስዱ እንዲሁም ከብሄረጽጌ ላፍቶ ድልድይ እስከ አረቄ ፋብሪካ ለፍሳሽ መሰረተ ልማቱ ተብሎም የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን በከፍተኛ ወጪ ያሰራቸው የመዳረሻ መንገዶችም የአፈር መድፊያ ሆነዋል፡፡ አፈሩን...

የፍሳሽ መሰረተ ልማቶቻችን ላይ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጧል ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በአለም ባንክ ብድር ያሰራው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ በሙሉ አቅሙ እንዲያጣራ 80 ኪሎ ሜትር መስመር ተዘርግቶ የቤት ለቤት ቅጥያ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ፡፡ በተፋሰሱ ስር የሚገኙ ነዋሪዎችን የዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘረጋ 80 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ ማሰባሰቢያ መስመር ላይ ከ550 በላይ ማንሆል ተሰርቶ የብረት ክዳን...

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በመኖሪያ ቤት የውሃ ቆጣሪ ወስደው በንግድ ስራ የተሰማሩ 15 ደንበኞች በፍተሻ ማግኘቱን ይፋ አደረገ፡፡

ደንበኞቹ በየካ ፣በአራዳ እና በጉለሌ ክ/ከተማ ስር የሚገኙ 15 ንግድ ቤት ሆነው በመኖሪያ ቤት ታሪፍ ሲከፍሉ የነበሩ ናቸው፡፡ ለዚህም ተግባራቸው ቅ/ጽ/ቤቱ የንግድ ፈቃዳቸውን በማየት አገልግሎት መስጠት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ኋላ በማስላት 47, 511, ብር እንዲከፍሉ ማድረጉን በቅ/ጽ/ቤቱ የውሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት መሪ አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ ተናግረዋል፡፡ አቶ ሙሉጌታ አክለዉም ደንበኛች በመኖሪያ...

ውሃን በቁጠባ ለመጠቀም ሆነ ወጪ ለመቀነስ የመልሶ መጠቀም አሰራር መዘርጋቱ በእጅጉ ጠቅሞናል አሉ በማህበር ተደራጅተው በተሸከርካሪ እጥበት የተሰማሩ አንድ አንድ ማበራት ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በስሩ ካሉ እና ህጋዊ ከሆኑ ሰባት ማህበራ ጋር በመነጋገር በቀላሉ ውሃን መልሶ በመጠቀም እንዲገለገሉ ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ስራ ገብቷል ፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ሶስቱ ሙሉ በሙሉ መጠቀም የጀመሩ ሲሆን አራቱ ማህበራት ደግሞ በሂደት ላይ ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከል በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ አራት የሚገኝ ሚካኤልና ጓደኞቹ የተሸከርካሪ እጥበት ማህበር አንዱ ነው፤የማህበሩ...