ባለስልጣኑ ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በከተማዋ ኪስ ቦታዎች ያስገነባቸውን አራት የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች ዛሬ አስመርቋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡት አራት የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች በኮልፌ ቀራኒዮ እና ጉለሌ ክ/ከ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በጥቅሉ በቀን 9ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችሉ ናቸው ፡፡ የፕሮጀክቶቹ በተዘረጉ መስመሮች ለተጠቃሚው እንዲደርሱ የተደረገ ሲሆን በተሰሩበት አካባቢ ፈረቃ እንዲሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ...

የአዲስአበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአዲስአበባ ሴቶች ማኅበር የጥቃት ማገገሚያ ውስጥ ለሚገኙ 60 ሴቶች የቁርስ በጀት ድጋፍ አደረገ።

በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ እና የተለያዩ ጥቃቶች ተፈጽመውባቸው በማገገም ላይ ላሉ 60 ሴቶች 15 ሺህ ብር የሚያወጣ የሩዝና የፖስታ ድጋፍ ተደርጓል ። ድጋፉን ያስረከቡት በባለሥልጣኑ የቦርድና ስራ-አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት መሠረት አሰፋ በቀጣይም ሌሎች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረግና ከጎናችሁ ለመሆን ዝግጁ ነን ብለዋል። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዘንድሮ በዓለም ደረጃ ለ110ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ከ112 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃን ከብክነት ማዳን ችሏል፡፡

በባለሥልጣኑ ውሃውን ከብክነት ያዳነው፡- ያረጁ መለስተኛ እና ከፍተኛ የውሃ መስመሮችን በመቀየር፣ ተከታታይነት ያለው መደበኛ የውሃ ብክነት ምርመራ እና ቁጥጥር ስራ በተለያዩ መሳሪያዎች በማከናወን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እያንዳንዱ ቅርንጫፎች የሚገባውን እና የሚወጣውን የውሃ መጠን ለመቆጣጠር ከፍተኛ እና በመለስተኛ መስመር ላይ 53 የውሃ ቆጣሪዎችን በመትከል እንዲሁም ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ ቆጣሪዎች በመቀየር እና...