እንኳን ደህና መጣችሁ!!!

የድሬ ግድብ

ግንባታው በ1991 ተጠናቀቀ

21 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

የገፈርሣ ግድብና ማጣሪያ ጣቢያ

ግንባታው በ1948 ተጠናቀቀ

በ2001 በጀት ዓመት የጥገና ሥራ ከተካሔደለት ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅሙ ወደ 9.5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ያደገ ሲሆን ውሃ የማምረት አቅሙም በቀን 30ሺ ሜትር ኪዩብ ነው

ለገዳዲ ግድብ

በ1963 ተመሠረተ

47 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

በ1977 ማስፋፊያ ከተደረገለት በኋላና በ1990ዎቹ አጋማሽ የኬሚካል አጠቃቀሙን ማሻሻል እና የሥርጭት መሥመሩን መቀየር ያስቻለ የዕድሳት ሥራ ከተከናወነለት በኋላ ዕለታዊ ውሃ የማማረት አቅሙ በቀን 165ሺ ሜትር ኪዩብ ደርሶ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም በ2007 ዓ.ም. የድሬ ግድብን ውሃ የመያዝ አቅም መጨመርና የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያን ውሃ የማምረት አቅም በ30ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማሳደግ ያስቻለ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተካሒዷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከግድብ በየዕለቱ 195ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ይመረታል፡፡

የከርሠ ምድር ውሃ

ከ1987 ዓ.ም. ወዲህ በከተማዋ ከ100 በላይ ጥልቅና መካከለኛ ጉድጓዶች ተቆፍረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በቀን ከሚመረተው 608ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ውስጥ 413ሺ ሜትር ኪዩብ (67.9%) ያህሉ ከከርሠ ምድር ውሃ መገኛዎች የሚመረት ነው፡፡

የፍሳሽ ማስወገጃ መኪኖች

ያለቦትን የውሃ ክፍያ በቀላሉ ይመልከቱ!

N

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም. ተቋማችን በሚሰጠው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች የከተማዋ ህብረተሰብ ረክቶ ማየት እና በዘርፉ የአፍሪካ ከተሞች የልዕቀት ማዕከል ሆኖ መገኘት፡፡
N

ተልዕኮ

የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ በማድረግ የውሃ መገኛዎችን በማልማት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓትን በመዘርጋት ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ዕድገት ጋር የሚመጣጠን የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ በበቂና አስተማማኝ ሁኔታ መስጠት፡፡
N

እሴቶች

1. አገልጋይነት
2. ቅንነት
3. በጋራ መስራት
4. እውቅና መስጠት
5. ልዕቀት
6. ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ትኩረት የሚሰጥ
7. ፍትሃዊነት
8. እምነት የሚጣልበት

ባለስልጣኑ ከ182 ኪ.ሜ በላይ የከፍተኛ እና መለስተኛ ውሃ መስመር ዝርጋታ አከናውናለሁ ብሏል፡

አዲስ አበባ ውሃና ፍሰሽ ባለስልጣን የውሃ ምርትና ስርጭት ተግባራትን ለማቀላጠፍ እና የውሃ ተደራሽነትን ለማስፋት በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ከ12.53 ኪ.ሜ በላይ የከፍተኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወንና በተጓዳኝ 0.25 ኪ.ሜ የመስመር ማዘዋወር ስራዎችን ለመስራት በእቅድ ይዞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ በተጨማሪው ከእነዚህ ከፍተኛ መስመር ዝርጋታዎች ጎን ለጎን የውሃ አገልግሎትን ይበልጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ...

read more

ባለስልጣኑ ከ182 ኪ.ሜ በላይ የከፍተኛ እና መለስተኛ ውሃ መስመር ዝርጋታ አከናውናለሁ ብሏል፡

አዲስ አበባ ውሃና ፍሰሽ ባለስልጣን የውሃ ምርትና ስርጭት ተግባራትን ለማቀላጠፍ እና የውሃ ተደራሽነትን ለማስፋት በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ከ12.53 ኪ.ሜ በላይ የከፍተኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወንና በተጓዳኝ 0.25 ኪ.ሜ የመስመር ማዘዋወር ስራዎችን ለመስራት በእቅድ ይዞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ በተጨማሪው ከእነዚህ ከፍተኛ መስመር ዝርጋታዎች ጎን ለጎን የውሃ አገልግሎትን ይበልጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ...

read more

ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ዋና ስራ አስኪያጅ

የተቋሙ ተገልጋዮች

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፤

በከተማዋ የሚገኙ የሀገር ውስጥና አለም አቀፋዊ ተቋማት፤

በውሃ መገኛዎች አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች፤

በላይ ደንበኞች

በላይ ሰራተኞች

ቅርንጫፎች

ፕሮጀክት ጽ/ቤት

ግድቦች