More customers
More employees
Branches
Dams
ተ.ቁ. | የስራው ዝርዝር | የተከለሰው ስታንዳርድ | ደንበኞች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች | አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት | |||
ከጊዜ | ጥራት | መጠን | |||||
1 | የአዲስ የውሃ መስመር ቅጥያ | 14 | ሰዓት | 100% | 12 ሜ | · የቤት ባለቤትነት ካርታ ወይም ደብተር ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ፣
· የአገልግሎት ጠያቂው የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣ · ተወካይ ከሆኑ የውክልና ደብዳቤ፤ የወረዳ ወይም የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ከሆነ ከወረዳ ወይም ከኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ እና የመንግስታዊና ህዝባዊ ድርጅቶች ከሆነ ከተቋሙ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ፣ · የመንግስት መስመር በሌለበት የሚቀርብ አዲስ የውሃ መስመር ቅጥያ ጥያቄ ውሃ ካስገባ ነባር ደንበኛ መስመር ላይ ለመቀጠል የባለመስመሩ ፍቃድ ስለሚያስፈልግ የነባሩ ደንበኛ የፍቃደኝነት ደብዳቤና የውሃ ቢል ኮፒ ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፣ · ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
2 | የውሃ መስመር ማሻሻያ | 14 | ሰዓት | 100% | 12 ሜ | · የቤትባለቤትነትካርታወይምደብተር ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ፣
· የአገልግሎትጠያቂው የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና ፎቶኮፒ፣ · ተወካይ ከሆኑ የውክልና ደብዳቤ፤ የወረዳ ወይም የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ከሆነ ከወረዳ ወይም ከኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ እና የመንግስታዊና ህዝባዊ ድርጅቶች ከሆነ ከተቋሙ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ፣ · ደንበኞች የቤት ባለቤትነት ካርታ ወይም ደብተር ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ካልቻሉ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባዘጋጀው መተማመኛ ቅፅ ላይ በመፈረም አገልግሎቱን ያገኛሉ፣ · ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
3 | የውሃ መስመር ማዛወሪያ | 14 | ሰዓት | 100% | 12 ሜ | · የቤት ባለቤትነት ካርታ ወይም ደብተር ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ፣
· የአገልግሎት ጠያቂው የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና ፎቶኮፒ፣ · ተወካይ ከሆኑ የውክልና ደብዳቤ፤ የወረዳ ወይም የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ከሆነ ከወረዳ ወይም ከኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ እና የመንግስታዊና ህዝባዊ ድርጅቶች ከሆነ ከተቋሙ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ፣ · ደንበኞች የቤት ባለቤትነት ካርታ ወይም ደብተር ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ካልቻሉ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባዘጋጀው መተማመኛ ቅፅ ላይ በመፈረም አገልግሎቱን ያገኛሉ፣ · ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
4 | የደንበኛ የውሃ መስመር ጥገና | 4 | ሰዓት | 100% | 3 ሜትር/ 1 በቁጥር/ | · መስመር ይጠገንልኝ ጥያቄ፣ | በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
5 | የደንበኛ ቆጣሪ በማንሳት መመርመር (NRW) | 4 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የዉሃ ብክነት ጥቆማ፣ | በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
6 | ለምርመራ የተነሳውን ቆጣሪ መልሶ መቀጠል(NRW) | 4 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የዉሃ ብክነት ጥቆማ፣ | በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
7 | የስም እና የአድራሻ ለውጥ ጥያቄ አገልግሎት | 15 | ደቂቃ | 100% | በቁጥር 1 | · የውርስ ከሆነ ከፍርድ ቤት የውርስ ማስረጃ፣
· የሽያጭ ከሆነ ከውልና ማስረጃ የተሰጠ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ፣ · የአገልግሎት ጠያቂው የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና ፎቶኮፒ፣ · ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ 12 ብር መፈጸም፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
8 | የውል ኮፒ ይሰጠኝ ጥያቄ | 30 | ደቂቃ | 100% | በቁጥር 1 | · ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ የውሃ ቢልና የወረዳ መታወቂያ ማቅረብ፣
· ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
9 | የአገልግሎት ሂሳባቸውን ያልከፈሉ ደንበኞችን አገልግሎት ማቋረጥ | 4 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የአገልግሎት ክፍያ በወቅቱ አለመከፈሉ ሲረጋገጥ፣ | በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
10 | ደንበኞች እዳቸውን እንደከፈሉ ቆጣሪ መልሶ መቀጠል | 4 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የውሃ አገልግሎት የተከፈለበት ቢል፣
· የመስመር ማስቀጠያ ክፍያ 56 ብር መፈጸም፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
11 | በሂሳብ በዛብኝ ቅሬታ የደንበኞች የውሃ ቆጣሪ በማንሳት የውሃ ብክነት ምርመራ ስራ መስራት (ቀን ቀን ውሃ ባለበት ሰዓት) | 4 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የውሃ ብክነት ምርመራ አገልግሎት ክፍያ መፈፀም፣
· የውሃ አገልግሎት የተከፈለበት አንድ ኮፒ ቢል፣ · የአገልግሎት ክፍያ እስከ ባለ አንድ ፎቅ ቤት ከሆነ 45 ብር ከሁለት ፎቅ በላይ ህንፃ 284 ብር መክፈል ይጠበቃል፡፡ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
12 | ለምርመራ የተነሳውን ቆጣሪ መልሶ መቀጠል | 4 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የውሃ አገልግሎት መጨረሻ የተከፈለበት አንድ ቢል፣
· የመስመር ማስቀጠያ ክፍያ 56 ብር መፈጸም፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
13 | ውል ማቋረጥ ቆጣሪ በማንሳት እና በማጣራት ሂሳብ መዝጋት | 4 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · ባለቤትነትን ሚያረጋግጥ የውሃ ቢልና መታወቂያ ማቅረብ፣
· ያለባቸውን ሂሳብ መዝጋት፣ · የውርስ ከሆነ ከፍርድ ቤት የውርስ ማስረጃ ማቅረብ፣ · የሽያጭ ከሆነ ከውልና ማስረጃ የተሰጠ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
14 | የመስመር መበከል እና የማስተካከያ ስራ መስራት የላቦራቶሪ ምርመራ /ባክትሮሎጂ እና ኬሚካል/ | 3 | ቀን | 100% | በቁጥር 1 | · የዉሃ ብክነት መኖሩን መረጃ ማቅረብ፣ | በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
15 | ውሃ በሮቶ ማደል ስራ ሳይቆራረጥ ማቅረብ | 8 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የአገልግሎት ክፍያ መክፈል፣ | በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
16 | የቦኖ ውሃ መስመር ቅጥያ (12 ሜትር) | 14 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1/በሜትር 12/ | · ከሚኖሩበት ወረዳ ወይም ክ/ከተማ ከስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የትብብር ደብዳቤ እና የወረዳውን መታወቂያ ማቅረብ፣
· ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣ · በመመሪያዉ መሰረት ከሌሎች ቦኖዎች ያለዉን ርቀት እና በአካባቢዉ ያለዉን የህዝብ ቁጥር ማሟላት፣ · የተጠቃሚዎችን አባዎራዎች በዝርዝር ማቅረብ፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
17 | የደንበኛ መረጃ ለውጥ (አዲስ ቅጥያ መረጃ፣የስም ለውጥ፣ የቆጣሪ ካታጎሪ፣ የቆጣሪ ለውጥ…) በማዘጋጀት ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ደ/የ/ሂደት መላክ | 15 | ደቂቃ | 100% | በቁጥር 1 | · የአገልግሎት ጥያቄ ማቅረብ፣
· የባለቤትነት ማረጋገጫ ቢል እና የቀበሌ መታወቂያ ማቅረብ፣ · ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣ |
በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
18 | የመንግስት የውሃ መስመር ጥገና | 5 | ሰዓት | 100% | 6 ሜትር/ 1 በቁጥር/ | · መስመር ይጠገንልኝ ጥያቄ፣ | ከ4ኢንች በታች በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት ከ4ኢንች በላይ በማዕከል በከፍተኛ መስመር ዝርጋታና ጥገና ኬዝቲም |
19 | የመንግስት መስመር ዝርጋታ | 3 | ቀን | 100% | በቁጥር 1 (1 ኪ.ሜ) | · የአገልግሎት ጥያቄ ማቅረብ፣
· በአካባቢው የተዘረጋው መስመር በዕቅድ የተያዘ መሆን አለበት፣ |
ከ4ኢንች በታች በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት ከ4ኢንች በላይ በማዕከል በከፍተኛ መስመር ዝርጋታና ጥገና ኬዝቲም |
ተ.ቁ. | የስራው ዝርዝር | የተከለሰው ስታንዳርድ | ደንበኞች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች | አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት | |||
ከጊዜ | ጥራት | መጠን | |||||
1 | የደንበኛ አዲስ የፍሳሽ መስመር ቅጥያ (ሶስት ሜትር) | 3 | ቀን | 100% | 3 ሜትር | · የወረዳ መታወቂያ፤ የውሃ ቢል፣
· መፀዳጃ ቤቱን በውሃ የሚሠራ ማድረግ፣ · ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም /ውል መዋዋል/፣ |
በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
2 | ፍሳሽ በተሸከርካሪ ማንሳት | 2 | ቀን | 100% | በቁጥር 1 | · መፀዳጃ ቤቱ መኪናው ከቆመበት ያለው ርቀት ከ30ሜትር መብለጥ የለበትም፣
· ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም(ለግለሰብ 176 ብር እና ለድርጅት 500 ብር)፣ |
በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
3 | የተሰበረ ፍሳሽ መስመር ጥገና | 12 | ሰዓት | 100% | በሜትር 3 | · ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም፤ | በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት እና በማዕከል በፍሳሽ ማንሳት ን/የስራ ሂደት |
4 | የተዘጋ ፍሳሽ መስመር መክፈት | 16 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የፍሳሸ መስመር ተጠቃሚ መሆን፣
· ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም፣ |
በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
5 | የፍሳሽ መስመር ማዛወር | 20 | ቀን | 100% | 1 ኪ.ሜ | · ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም፣ | በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
6 | የመለስተኛ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ | 20 | ቀን | 100% | 1 ኪ.ሜ | · ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም፣ | በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት |
7 | ህገ-ወጥ ቅጥያ ክትትል | 4 | ቀን | 100% | በቁጥር 1 | · ጥቆማ ማቅረብ፣ | በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት እና በማዕከል በፍሳሽ ማንሳት ን/የስራ ሂደት |
8 | ማንሆሎችን ማጽዳት ግሬስ ማድረግ እና መለያ መስጠት | 4 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የአገልግሎት ጥያቄ ማቅረብ፣ | በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት እና በማዕከል በፍሳሽ ማንሳት ን/የስራ ሂደት |
9 | የማንሆል ቶፕ ኤለመንት ማምረት | 4 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት እና በማዕከል በፍሳሽ ማንሳት ን/የስራ ሂደት | |
10 | የማንሆል ከፍታ ማስተካከል | 16 | ሰዓት | 100% | በቁጥር 1 | · የአገልግሎት ጥያቄ ማቅረብ፣ | በቅርንጫፍ የፍሳሽ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት እና በማዕከል በፍሳሽ ማንሳት ን/የስራ ሂደት |
የተጠቃሚዎች መብት እና ግዴታ
- ማንኛውም ደንበኛ ተቋሙ የሚጠይቃቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ንፁህ የመጠጥ ውሃ የማግኘት መብት ኣላቸው፤
- ማንኛውም ተገልጋይ ከሥራ ሂደቱ አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ በማናቸውም ጉዳይ ላይ የተሰማውን ቅሬታ ወይም አቤቱታ የማቅረብ እና ምላሽ የማግኘት መብት አለው፤
- ስለ አገልግሎቱ በቂ መረጃ እና የምክር አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፤
- ለአገልግሎት የሚጠየቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ፍትሃዊና አድሎ የሌለው አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፤
- ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና የፍሳሽ ማስወገድ ስርዓት ለህብረተሰቡ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተደራሽ ማድረግ፤
- የባለስልጣን መ/ቤቱን የስትራቴጂክ ዘመኑን ዕቅድ፣ አመታዊ ዕቀድ ዝግጅት እና የአፈጻጸም ግምገማ ላይ የህዝብ አደረጃጀት ፎረሞችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ማሳተፍ፤
- ባለስልጣን መ/ቤቱ በውሃ እና በፍሳሽ ዘርፍ ለሚሰጣቸው አገልግሎት በቂ ግብዓት የማቅረብ፤
- በተቀመጡ ስታንዳርድ መሰረት አገልግሎት መስጠት፤
- ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በባለስልጣን መ/ቤቱ ስለሚሰጡ አግልግሎቶች ሙሉ መረጃ ግልጽ በሆነ መልኩ ማቅረብ እና ማሳወቅ፤
- በተገልጋዩ ህብረተሰብ ለሚፈጠሩ ቅሬታዎች በባለስልጣን መ/ቤቱ ለቅሬታ አፈታት በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ምላሽ መስጠት፤
- ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ፍትሃዊ፣ አድሎ የሌለበት አገልግሎት የመስጠት እና በእኩልነት የማገልገል፤
- በየጊዜው የህብረተሰቡ እርካታ ያለበትን ደረጃ መለካት፤
- ዜጎች በተቋሙ አፈጻጸም ምዘና ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
- የባለስልጣን መ/ቤቱን ህግና ስርዓት ለደንበኞች ማሳወቅ፤
- በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እና ማቅረብ፤
- በተቋሙ የሚቀርቡ አገልግሎቶች እና ንብረቶች (ውሃ፣ የውሃ ቆጣሪ እና የውሃ መስመሮች ወ.ዘ.ተ)እና የውሃ ብክነትን ለመቀነስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በአግባቡ መጠቀምና የሚፈስ ውሃ ሲኖር መጠቆም፤
- የባለስልጣን መ/ቤቱን ህግና ስርዓት ማክበር፤
- የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት
- ቅሬታ ወይም አቤቱታ የማቅረብ መብት
- የመስሪያ ቤቱ ቅሬታ ወይም አቤቱታ የማስተናገድ ግዴታ
- የቅሬታ ወይም የአቤቱታ አቀራረብ
- የቅሬታ ወይም የአቤቱታ ይዘት
ደንበኞች በማንኛውም ሁኔታ በአገልግሎት አሰጣጡ ቅሬታ ካጋጠማቸው ቅሬታቸውን ሊያቀርቡበት የሚችሉበት ስርዓት በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽባለሥልጣን ዋናው መሥሪያ ቤት እና በስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተዘረጋ ሲሆን ተገልጋዮችም በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ የሚያጋጥሟቸውን ቅሬታዎችበየደረጃው ላሉ ፈፃሚዎች፣ የቅርብ ሃላፊዎች፣ ለበላይ አመራሮች በማንኛውም ሰዓት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ላቀረቡት ቅሬታ በቂ ምላሽ ካላገኙዋናው መሥሪያ ቤት እና በየቅርንጫፎቹለተቋቋሙ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በማቅረብ ቅሬታቸው በገለልተኝነት እንዲታይላቸው ማድረግ ይችላሉ፡፡ ተገልጋዮችበባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ደረጃ በደረጃ ቅሬታቸው ካልተፈታ ወደ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ፍርድ ቤቶች እና መገናኛ ብዙሃንበመሄድ ቅሬታቸው እንዲፈታላቸው ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተገልጋይ ከሥራ ሂደቱ አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ ያለመርካት ባስከተለበት በማናቸውም ጉዳይ ላይ የተሰማውን ቅሬታ ወይም አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፤
- የተገልጋይ አለመርካት ቅሬታ ወይም አቤቱታ ለማቅረብ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮች፡-
- አገልግሎት ለማግኘት ካለው ህጋዊ መብት፣
- ከአገልግሎት አሠጣጥ ሠርዓቶእ እና የአሰራር ሂደቶች
- ከአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ማለትም ከጥራት፣ ከሚወስደው ጊዜ፣ ምልልስ እና ውጤታማነት አንጻር፣
- አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ቦታዎች
- ከአገልግሎት ክፍያ እና ከፈጻሚ ሠራተኞች ሠነ-ምግባር ጋር በተያያዘ፣
- በተገልጋዩ የሚቀርቡ ቅሬታንም ሆነ አቤቱታ የማስተናገድ እና ፈጣን ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት፤
- ቅሬታ እና አቤቱታ ሊቀርብባቸው የሚችሉ ጉዳዮችን እና የሚቀርቡበትን ደረጃ ለተገልጋዮች ማሳወቅ አለበት፤
- በአገልግሎት አሰጣጥ ላልረካና ቅር ለተሰኘ ተገልጋይ በመስሪያ ቤቱ የመረጃ ዴስክ ሠራተኛ አማካኝነት የቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት ሥራዓጥን ለተገልጋዩ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፤
- ቅሬታ በተገልጋዩ ወይም በወኪሉ በጽሁፍ፣ በቃል፣ በፋክስ፣ በኢ.ሜይል ወይም በስልክ አገልግሎት ሰጪ /ፈፃሚ/ ለሚገኝበት የሥራ ሂደት መሪ ወይም አስተባባሪ ሊቀርብ ይችላል፤
- ማንኛውም አቤቱታ በተገልጋዩ ወይም በወኪሉ በጽሑፍ ወይም ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ፎርም እየተሞላ ለቅሬታ እና አቤቱታ ሰሚ አካ ሊቀርብ ይችላል፡፡
- የተገልጋዩን ሙሉ ስም እና አድራሻ፣
- ቅሬታው ወይም አቤቱታው የቀረበበትን ዋና ጉዳይ፣
- መንስኤ የሆነውን ድርጊት በአጭሩ፣ የተፈጸመበት ቀን እና ቦታ፤
- ጉዳዩ የሚመለከተውን የስራ ሂደት እና አገልግሎት ሰጪ/ፈፃሚ/፣
- ደጋፊ ማስረጃዎች ካሉ በአባሪነት፣
- ተገልጋዩ እንዲደረግለት የሚፈልገው መፍትሔ፣
አስተያየት መስጫ ዘዴዎችን በተመለከተ
በተቋሙ በሚሰጡ አገልግሎቶች ዙሪያ ከተገልጋዮችም ሆነ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሰጡ አወንታዊም ሆኑአሉታዊ አስተያየቶች ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መሻሻል እንደ ግብዓት የሚያገለግሉ መሆናቸውን በመገንዘብ በዋናው መ/ቤትም ሆነ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ህብረተሰቡ አስተያየት ሊሰጥ የሚችልባቸው ሀሳብ መስጫ ሳጥኖች፣ መዝገቦች እና ቅጾች እንዲሁም የነጻ አገልግሎት ስልኮች ተዘጋጅቷል፡፡ በእነዚህ ሀሳብ መስጫዎች የሚገኙ አስተያቶችን የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው በመሰብሰብ በፕሮሰስ ካውንስል እንዲታይ ከተደረገ በኃላ የፕሮሰስ ካውንስሉ ለቀረቡ አስተያየቶች ምላሾቻቸውንና የሚወሰዱ እርምጃዎችን እንዳስፈላጊነቱ በጽሁፍ ቦርድ ላይ በመለጠፍ ደንበኞች እንዲያውቁት ያደርጋል፡፡
የመረጃ ማስተላለፊያ አግባቦች
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሃሙስ ጠዋት ከ2፡30-6፡30፤ አርብ ከ2፡30-5፡30፤ ዘወትር ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሲሆን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሚሰጣቸው አገልገልግሎቶች (የውሃ እና የፍሳሽ መስመሮች ሲሰበሩ፣ በማንኛውም መንገድ የውሃ መቋረጥ ሲያጋጥም) እንዲሁም ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካልዎት የተዘረዘሩትን የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች በመጠቀም ማቅረብ ይችላሉ፡፡
ድህረ ገጽ፡- www.aawsa.gov.et ኢሜይል፡-info@aawsa.gov.et ፖ.ሳ.ቁ.1505 አ.አ. ኢትዮጵያ ፋክስ፡-0116623924
ተ.ቁ | የስራ ኃላፊነት | የኃላፊው ሥም | ልዩ ቦታው | ክፍለ ከተማ | ወረዳ | ቢሮቁጥር | የአመራሩ ስልክ | መረጃ ለመጠቅ ሆነለመስጠት ስልክ ቁጥር | |||||||
1. ዋናው መሥሪያ ቤት | |||||||||||||||
1.1 | የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ | አቶ አወቀ ኃ/ማርያም | መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ | ቦሌ ክፍለ ከተማ | 05 | 0116623902 |
0116623927 |
||||||||
1.2 | የባለስልጣን መ/ቤቱ የፍሳሽ ም/ስ/አስኪያጅ | አቶ ባህራይ በላይ | መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ | ቦሌ ክፍለ ከተማ | 05 | 0116623781 |
0116623921 |
||||||||
1.3 | የዋና ስራስኪያጅና ቦርድ ፅ/ቤት ሀላፊ | ወ/ሮ እፀገነት ተስፋዬ | መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ | ቦሌ ክፍለ ከተማ | 05 | ||||||||||
1.4 | የባለስልጣን መ/ቤቱ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የስራ ሂደት | አቶ እስጠፋኖስ ብስራት | መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ | ቦሌ ክፍለ ከተማ | 05 | 0116187643 |
0116188638 |
||||||||
1.5 | ሀብት/አስ/ክ/ዘ/ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ | ሞገስ አርጋው | ዋናው መስሪያ ቤት | ቦሌ ክፍለ ከተማ | 05 | 0116674832 |
0116187641/42/43 በነጻ ስልክ 906 |
||||||||
1.6 | ውሃ አቅ/ም/ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ | ፍቃዱ ዘለቀ | ዋናው መስሪያ ቤት | ቦሌ ክፍለ ከተማ | 05 | 0116623782 | |||||||||
ተ.ቁ | የስራ ኃላፊነት | የኃላፊው ሥም | ልዩ ቦታው | ክፍለከተማ | ወረዳ | ቢሮ ቁጥር | የአመራሩ ስልክ | መረጃ ለመጠቅ ሆነለመስጠት ስልክ ቁጥር | |||||||
2. ፕሮጀክት ጽ/ቤት | |||||||||||||||
2.1 | የፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ | አቶ ተስፋአለም ባዩ | ወረዳ 06 አስተዳደር ጽ/ቤት ፊት ለፊት | ቦሌ ክፍለ ከተማ | 06 | 0118951478/79 | |||||||||
3. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች | |||||||||||||||
3.1 | የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት | አቶ አምባዬ አሰፋ | 6 ኪሎ ከተፈሪ መኮንን ኮሌጅ አጠገብ | ጉለሌ ክፍለ ከተማ | 03 | 0111231652 |
0111222931 |
||||||||
3.2 | የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት | አቶ ወርቁ ገዳ | የቀድሞ እስላም መቃብር ፊት ለፊት | አዲስ ከተማ ክ/ከተማ | 06 | 0112772799 |
0112772711 |
||||||||
3.3 | የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት | አቶ ደረጀ | ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት | ጉለሌ ክፍለ ከተማ | 05 | 0111113448 |
0111114435 |
||||||||
3.4 | የመገናኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት | አቶ አህመድ መሀመድ | መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ | ቦሌ ክፍለ ከተማ
|
05 | 0116188015 |
0116511839 |
||||||||
3.5 | የጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት | አቶ መሀመድ ካሣው | ወረዳ 06 አስተዳደር ጽ/ቤት ፊት ለፊት | ቦሌ ክፍለ ከተማ | 06 | 0116676524 |
01166765427 |
||||||||
3.6 | የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት | አቶ ብርሀኑ ሸዋጎ | የጎተራ ማሳለጫ ምስራቅ ዱቄት ፋብሪካ አጠገብ | ቂርቆስ ክፍለ ከተማ | 03 | 0114671589 |
0114671366 |
||||||||
3.7 | የመካኒሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት | አቶ ሄኖክ ወርቁ | ብስራተ ገብርኤል አካባቢ ከብሩከ ሆስፒታል ዝቅ ብሎ | ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ | 03 | 0113729735 |
0113729728 |
||||||||
3.8 | የአቃቂ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት | አቶ ሰለሞን ታፈሰ | አቃቂ ሚሽን ት/ቤት ጀርባ | አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ | 01 |
0114343716 |