ዜና

ከውሃ መስመር ላይ የሚፈስ እና የሚባክን ውሃን ለመቀነስ ጥረት እየተደረገ ነው::

ከመጠጥ ውሃ ስርጭት መስመር ላይ በሚባክነው ውሃ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር የአለም አቀፍ ውሃ ብክነት ቀን ዛሬ ህዳር 25 ቀን በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀን 346 ቢሊየን ሊትር ውሃ ከውሃ ማሰራጫ መስመሮች ላይ ይባክናል፡፡ ይህን ብክነት በ30% መቀነስ ቢቻል በምድራችን 800 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል በዓለም አቀፍ ውሃ ማህበር የውሃ ብክነት ቡድን መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ...

ባለስልጣኑ መካኒሳ፣ ጉርድ ሾላ፣ አራዳ እና መገናኛ ቅ/ጽ/ቤቶች የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ዙር የደንበኞች ፎረም ጉባኤ አካሂደዋል፡፡

በጉባኤው ላይ ከመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ተቋሙ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የተወሰዱ እርምጃዎችን የተመለከተ የሩብ ዓመት ሪፖረት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውሃ ስርጭት ፣ በዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ እና በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በገቢ አሰባሰብ ላይ በርካታ ደንበኞች የመክፈል ባህል ዝቅተኛ በመሆኑ በቅስቀሳ ሲያልፍም እርምጃ በመውሰድ...

የአዲስአበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሰራተኞች እና አመራሮች ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለገሱ።

"ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን" በሚል መሪ ቃል የባለሥልጣኑ ሰራተኞች የሀገር መከላከያ ሰራዊታን ለመደገፍ የደም ልገሳ መርሐ ግብር በመካኒሳ ቅ/ጽ/ቤትና በዋናው መ/ቤት አከናውነዋል። በደም ልገሳ መርሐ ግብሩ ላይ አስተባባሪ የሆኑት የባለሥልጣኑ የሴቶች ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ኤጀርሳ የደም ልገሳ መርሐ ግብሩ ዓላማ የባለሥልጣኑ ሰራተኞች ህግ በማስከበር ተግባር ላይ ለተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት የበኩላችንን...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ሠራተኞች ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ከ14.4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

የባለስልጣኑ ሠራተኞች ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን 14 ሚሊየን 463 ሺህ 815 ብር ለግሰዋል፡፡ ድጋፉን ያደረጉት በዋናው መስሪያ ቤት እና በስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኙ ቋሚ እና ኮንትራት ሠራተኞች መሆናቸውን በባለስልጣኑ የፋይናንስ ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ ወ/ሮ ላቀች አግደው አስታውቀዋል፡፡ ከተጠቀሰው ድጋፍ በተጨማሪም በባለስልጣኑ ስፖርት ኮሚቴ አማካኝነት ሠራተኛው ለስፖርታዊ...

ዛሬ የአለም የመጸዳጃ ቤቶች ቀን ታስቦ ውሏል ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣንም ቀኑን በማስመልከት ፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ አጣርቶ የማስወገድ አገልግሎት ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ገልጸል፡፡ ባለሥልጣኑ አሁን ያለው ፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ የማጣራት አቅም በቀን 148 ሺህ ሜ.ኩብ ማድረስ ችሏል፡፡ በዘመናዊ መንገድ ፍሳሽ ሰብስቦ የማጣራት አቅሙ ከፍ ያደረጉት በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የቃሊቲ ፣ የኮተቤ ፣ ሚኪላንድ፣ ገላን እንዲሁም...

የአዲስ አበባ ውሃ ና ፍሳሽ ባለስልጣን ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ግምታቸው 290 ሺህ ብር በላይ የሆነ የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

ባለስልጣኑ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ለከተማዋ ነዋሪዎች ከማቅረቡ ባሻገር ማህበራዊ ሀላፊነቱ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ባለስልጣኑ በአይነት ድጋፍ ያደረገው 2000 ፓስታ ፣633 ካርቶን ሀይል ሰጪ ብስኩቶች( አንዱ ካርቶን 80 እሽግ ብስኩት የያዘ) ፣400 ባለ ሰባ ግራም የቲማቲም ድልህ እና 36 የገበታ ጨው ሲሆን አጠቃላይ ድምራቸው 290 ሺህ ብር በላይ ግምት አላቸው ፡፡ የድጋፍ ረክክቡ ላይ የተገኙት የማዕከሉ ምክትል ስራ...

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ሦስት የጥበቃ አባላት የተቋሙን ቁሳቁሶች ሲዘርፉ እጅ ከፍንጂ ተያዙ፡፡

የጥበቃ አባላቱ GBS ከተባለ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲ ጋር ውል በመፈጸም ወደ ስራ ገብተው የነበሩ ሲሆን በቀን 27/02/2013ዓ.ም የተለያዩ ቁጥር ያላቸው የቧንቧ መፍቻዎችን፣ ሁለት GPS እና የብረት መጋዝ መያዣ/ሰጌቶ ከዕቃ ከግምጃ ቤት ነው የሰረቁት፡፡ ተጠርጣሪዎቹም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ ሁለት በተለምዶ ስብሰባ ማዕከል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕቃዉን እንደተሸከሙ በአካባቢው ማህበረሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር...

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት የስራ ዕድል ሊፈጥር ዝግጅት አጠናቋል ፡፡

ባለስልጣኑ በ2013 በጀት ዓመት ከ781 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን በጀት በጥቃቅን እና አነስተኛ በ169 አዲስ እና ነባር ማህበራት ለተደራጁ ከ1700 በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ተዘጋጅቷል፡፡ ለስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር በከተማ ደረጃ ለተያዘው የድህነት ቅነሳ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከነባር ማህበራት በተጨማሪ በተያዘው በጀት ዓመት ከ64 በላይ ለሚሆኑ አዲስ ማህበራት የስራ ትስስር ለመፍጠር...

በባለስልጣኑ የንፋስ ስልክ ቅ/ ጽ/ቤትም የውሃ ስርጭት አገልግሎት እየተሻሻለ መምጣቱን ደንበኞች ፎረም ገለፁ ።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ 2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ከደንበኞች ፎረም አባላት ውይይት አካሄድ ። ቅርንጫፉ ውሃ በፈረቃ እያደረስ ቢሆንም ቀድሞ ፈረቃው ይዛባ እንደነበር ገልጸው በአሁኑ ጊዜ የተሻለ አግልግሎት መኖሩን የፎረም አባላት ገልፀዋል ። በሌላ በኩል በሩብ ዓመቱ ተቋሙ ወዝፍ ገቢ አሰባሰብ ላይ ክፈተቶች መኖራቸውን ገልፀው በቀጣይ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከፎረም አባለት እና ከየወረዳ አስተዳደሩ...