እንኳን ደህና መጣችሁ!!!

የድሬ ግድብ

ግንባታው በ1991 ተጠናቀቀ

21 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

የገፈርሣ ግድብና ማጣሪያ ጣቢያ

ግንባታው በ1948 ተጠናቀቀ

በ2001 በጀት ዓመት የጥገና ሥራ ከተካሔደለት ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅሙ ወደ 9.5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ያደገ ሲሆን ውሃ የማምረት አቅሙም በቀን 30ሺ ሜትር ኪዩብ ነው

ለገዳዲ ግድብ

በ1963 ተመሠረተ

47 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

በ1977 ማስፋፊያ ከተደረገለት በኋላና በ1990ዎቹ አጋማሽ የኬሚካል አጠቃቀሙን ማሻሻል እና የሥርጭት መሥመሩን መቀየር ያስቻለ የዕድሳት ሥራ ከተከናወነለት በኋላ ዕለታዊ ውሃ የማማረት አቅሙ በቀን 165ሺ ሜትር ኪዩብ ደርሶ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም በ2007 ዓ.ም. የድሬ ግድብን ውሃ የመያዝ አቅም መጨመርና የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያን ውሃ የማምረት አቅም በ30ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማሳደግ ያስቻለ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተካሒዷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከግድብ በየዕለቱ 195ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ይመረታል፡፡

የከርሠ ምድር ውሃ

ከ1987 ዓ.ም. ወዲህ በከተማዋ ከ100 በላይ ጥልቅና መካከለኛ ጉድጓዶች ተቆፍረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በቀን ከሚመረተው 608ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ውስጥ 413ሺ ሜትር ኪዩብ (67.9%) ያህሉ ከከርሠ ምድር ውሃ መገኛዎች የሚመረት ነው፡፡

የፍሳሽ ማስወገጃ መኪኖች

ያለቦትን የውሃ ክፍያ በቀላሉ ይመልከቱ!

R

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም. ተቋማችን በሚሰጠው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች የከተማዋ ህብረተሰብ ረክቶ ማየት እና በዘርፉ የአፍሪካ ከተሞች የልዕቀት ማዕከል ሆኖ መገኘት፡፡
R

ተልዕኮ

የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ በማድረግ የውሃ መገኛዎችን በማልማት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓትን በመዘርጋት ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ዕድገት ጋር የሚመጣጠን የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ በበቂና አስተማማኝ ሁኔታ መስጠት፡፡
R

እሴቶች

1. አገልጋይነት
2. ቅንነት
3. በጋራ መስራት
4. እውቅና መስጠት
5. ልዕቀት
6. ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ትኩረት የሚሰጥ
7. ፍትሃዊነት
8. እምነት የሚጣልበት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አመራርና እና አባላት የባለስልጣኑን ስራዎች ጎበኙ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አመራርና እና አባላት የባለስልጣኑን ስራዎች ጎበኙ።

ቋሚ ኮሚቴው የለገዳዲ ክፍል ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክት ፣ የቦሌ አራብሳ ፣ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤት ፣ የቦሌ ቡልቡላ እና ሪፌንቴ አካባቢ እየታሰሩ ያሉ የውሃ እና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ምልከታ አድርገዋል።የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢው የተከበሩ ወ/ሮ ልእልቲ ግደይ ባለስልጣኑ በተለይ የህዝብ ቅሬታ የሚነሳባቸውን ቦታዎች በመለየት አፋጣኝ መፍትሄ ማበጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።በተለይ መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው የጋራ...

read more
ከቱሉ ዲምቱ እስከ ቃሊቲ አደባባይ ሲሰራ የነበረው የውሃ መስመር የማዛወር ስራ ተጠናቀቀ ::

ከቱሉ ዲምቱ እስከ ቃሊቲ አደባባይ ሲሰራ የነበረው የውሃ መስመር የማዛወር ስራ ተጠናቀቀ ::

በመንገድ ሥራ ምክንያት ከአቃቂ ክፍል 1 ወደ ከተማ ውሃ ይዞ የሚመጣውና 18.94 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ከፍተኛ የውሃ መስመር ማዛወር ስራ ተጠናቆ ለመንገድ ስራው ክፍት ተደርጓል፡፡የመስመር ማዛወር ስራው በ48 ሚሊየን 876 ሺህ 163.72 ብር እና በ7 ሚሊየን 245 ሺህ 883.4 የአሜሪካን ዶላር ወጪ በአሰር ኮንስትክሽን ኃ.ግ.ድ እና በIFH ኮንስትክሽን አማከኝነት ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡የከፍተኛ የውሃ መስመር ማዛወር...

read more
በባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ38 ሺኅ በላይ አባወራዎችን የፍሳሽ በመስመር አገልግሎት ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

በባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ38 ሺኅ በላይ አባወራዎችን የፍሳሽ በመስመር አገልግሎት ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማዋን የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ለማዘመን በከተማው ባስገነባቸው ከ40 በላይ የተማከሉ እና ያልተማከሉ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ነዋሪውን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡በዚሁ መሰረት በስድስት ወራት ውስጥ የፍሳሽ መሰረተ ልማት በተዘረጋባቸው አካባቢዎች ለ31,755 አባወራ የፍሳሽ መስመር ቅጥያ ለማከናወን ታቅዶ ለ38,114 አባወራዎች መስመር በማገናኘት...

read more

የስራ ማስታወቂያ

ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ዋና ስራ አስኪያጅ

የተቋሙ ተገልጋዮች

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፤

በከተማዋ የሚገኙ የሀገር ውስጥና አለም አቀፋዊ ተቋማት፤

በውሃ መገኛዎች አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች፤

በላይ ደንበኞች

በላይ ሰራተኞች

ቅርንጫፎች

ግድቦች