የአስተዳደር ቅርጽ

አብይ የሥራ ሂደቶች

 • የውሃ አቅርቦት ስ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ
 • የሀብት አስ/አጠ/ክ/ዘ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ
 • የፍ/ቆ/ማ/ማ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ
 • የውሃና ሳኒቴሽን ልማትና ማስፋፊያ ጽ/ቤት

ደጋፊ የሥራ ሂደቶች

 • የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደ/የሥራ ሂደት
 • የጥናት፣ዕቅድና በጀት ደ/የሥራ ሂደት
 • ውጤትን መሠረት ያደረገ ክ/ደ/የሥራ ሂደት
 • ሕግና ኢንሹራንስ ደ/የሥራ ሂደት
 • ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ደ/የሥራ ሂደት
 • ግዥ ደ/የሥራ ሂደት
 • ፋይናንስ ደ/የሥራ ሂደት
 • የውስጥ ኦዲት ደ/የሥራ ሂደት
 • የሰው ኃይል አስ/ደ/የሥራ ሂደት
 • የንብረት አስተዳደር ደ/የሥራ ሂደት
 • የማሰልጠኛ ተቋም

ቅ/ጽ/ቤቶች

 • ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት
 • አራዳ ቅ/ጽ/ቤት
 • ነፋስ ስልክ ቅ/ጽ/ቤት
 • መካኒሣ ቅ/ጽ/ቤት
 • አዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት
 • መገናኛ ቅ/ጽ/ቤት
 • ጉርድ ሾላ ቅ/ጽ/ቤት
 • አቃቂ ቅ/ጽ/ቤት

ተቋማዊ አደረጃጀት

 

ተቋሙ በስራ ላይ ባለው አደረጃጀት በማዕከል አንድ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ ሶስት ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ፣ ዘጠኝ ደጋፊ ስራ ሂደቶች ሲኖሩት በስሩ በሚገኙ  ስምንት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስምንት የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ እና በፕሮጀክት ጽ/ቤት አንድ ስራ አስኪያጅና ሁለት ምክትል ስራ አስኪያጅ ያሉት ሲሆን በዘርፍ፣በፕሮጀክትና በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደረጃ ያለውን አደረጃጀት ደግሞ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

                 ውሃ ዘርፍ

የውሃ ዘርፍ በማዕከል በአንድ ዋና፣ በሶስት ንዑስ ስራ ሂደት (የውኃማጣ/ማም/ማሠ//ቁንዑስ የስራ ሂደት፣የውሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የሥራ ሂደት እና የኮንደሚንየም ቤቶችና ሌሎች መሰረተ-ልማት የውሃመስመር አቅርቦትና አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት) እና በሰባት ኬዝ ቲሞች ተደራጅቶ የውሃ ማምረትና ማሰራጨት  ስራን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በቅርንጫፍ ደረጃ ከውሃ ደንበኞችጋር የተያያዙ በርካታ አገልግሎቶችን ለመስጠት በአንድ ን/ስራ ሂደትና በሶስት ኬዝ ቲም ተደራጅቶ ይገኛል፡፡

                    የፍሳሽ ዘርፍ

የፍሳሽ ዘርፍ በማዕከል በአንድ ዋና ስራ ሂደት ፣ በሶስት ንዑስ ስራ ሂደት (የፍሳሽ ማጣራት፣ መልሶ መጠቀምና ማስወገድ ንዑስ የስራሂደት፣ የፍሳሽ ማንሳት ንዑስ የሥራ ሂደት እና የኮንደሚንየም ቤቶችና ሌሎች መሰረተ ልማት የፍሳሽ መስመር አቅርቦትና አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት) እና በአምስት ኬዝ ቲሞች ተደራጅቶ የፍሳሽ ቆሻሻን የማንሳት፣ የማጣራትና የማስወገድ ስራን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በቅርንጫፍ ደረጃ ከፍሳሽ ደንበኞች ጋር የተያያዙ በርካታ አገልግሎቶችን ለመስጠት በአንድ ን/ስራ ሂደት ተደራጅቶ ይገኛል፡፡

              የሃብት አስተዳደር ዘርፍ

የሃብት አስተዳደር ዘርፍ በማዕከል በአንድ ዋና፣ በአምስት ደጋፊ ስራ ሂደት (ፋይናንስ፣ ግዥ፣ የሰው ሃይል አስተዳደር፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት እና የተሸከርካሪዎች እና መሳሪያዎች ጥገና ደጋፊ የስራ ሂደት) እና በአስር ቡድኖች ተደራጅቶ የሃብት አጠቃቀም፣ አስተደደርና ክትትል  ስራን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በቅርንጫፍ ደረጃ በአራት ቡድኖች ተደራጅቶ ለአብይ ስራ ሂደቶቹ የመደገፍ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

         ለተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ ተጠሪ የሆኑ ሌሎች ደጋፊ ስራ ሂደቶች

በስራ ላይ ባለው መዋቅር ተጠሪነታቸው ለተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆነ 8 ደጋፊ ስራ ሂደቶች እና 2 ዴስክ ያሉ ሲሆን በዝርዝር ሲታዩ ህግና ኢንሹራንስ፣ የውስጥ ኦዲት፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የጥናት ዕቅድና በጀት፣ ውጤትን መሰረት ያደረገ ክትትልና ድጋፍ፣ የውሃና ሳኒቴሽን ማሰልጠኛ ተቋም፣ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ ስራ ሂደት፣ የስምግባር መከታተያ ዴስክ፣ የሴቶች ጉዳይ ዴስክ ናቸው፡፡

        ፕሮጀክት ጽ/ቤት

የከተማውን የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የፍሳሽ ቆሻሻ አገልግሎት ሽፋን ከከተማው ዕድገትና ከከተማው ህብረተሰብ ፍላጎት ጋር ጎን ለጎን እንዲሄድ የውሃ መገኛና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ በማጥናት የመጠጥ ውሃ ልማትና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ለመዘርጋት ሲባል የባለስልጣን መ/ቤቱ ስር የፕሮጀክት ጽ/ቤት እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ስር አንድ ስራ አስኪያጅ፣ ሁለት ምክትል ስራ አስኪያጅ፣ ሁለት ንዑስ ስራ ሂደት፣ ስድስት የዋና ስራ ሂደቶች ኬዝ ቲም፣ አምስት ደጋፍ ስራ ሂደትና በደጋፊ ስራ ሂደት ስር ያሉ ሶስት ቡድኖች ይዞ የተደራጀ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ ስኪያጅ ነው፡፡

 

 

ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ

ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ዋና ስራ አስኪያጅ

Team Member 1

Team Member 1

የውሃ አቅርቦት ስ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ

Team Member 2

Team Member 2

የሀብት አስ/አጠ/ክ/ዘ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ

Team Member 3

Team Member 3

የፍ/ቆ/ማ/ማ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ

Team Member 4

Team Member 4

የውሃና ሳኒቴሽን ልማትና ማስፋፊያ ጽ/ቤት