ማሳሰቢያ

ማስታወቂያ

ለአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሠራተኞች በሙሉ

ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ፈተና (ሲ.ኦ.ሲ.) ያቀረበ ሠራተኛና አመራር ራሱን በማጋለጥ ከተጠያቂነት ነፃ እንዲሆን እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ የጊዜ ገደብ ተሰጥቶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሆኖም የከተማ አስተዳደሩ የጊዜ ገደቡን እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ያረዘመ ስለሆነ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ፈተና  (ሲ.ኦ.ሲ.) ያቀረበ ማንኛውም ሠራተኛና አመራር በጊዜ ገደቡ ተጠቅሞ ራሱን በማጋለጥ ከተጠያቂነት ነፃ እንዲሆን እያሳሰብን፤ በዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የሚፈልግ ማንኛውም ፈፃሚም ሆነ አመራር ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት በዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 143 በመቅረብ ራሳችሁን እንድታጋልጡ እናሳስባለን፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን

 

ለአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ደንበኞች

በባለሥልጣኑ በተርሚናል የውሃ ግፊት መስጫ ላይ ረቡዕ ታህሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. የጥገና ሥራ ያከናውናል፡፡

በመሆኑም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6፣ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7፣ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 5፣ 6፣ 7፣ 8 እና 9፣ አካባቢዎች በከፊል የውሃ ስርጭት ስለሚቋረጥ ከወዲሁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን