እንኳን ደህና መጣችሁ!!!

የድሬ ግድብ

ግንባታው በ1991 ተጠናቀቀ

21 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

የገፈርሣ ግድብና ማጣሪያ ጣቢያ

ግንባታው በ1948 ተጠናቀቀ

በ2001 በጀት ዓመት የጥገና ሥራ ከተካሔደለት ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅሙ ወደ 9.5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ያደገ ሲሆን ውሃ የማምረት አቅሙም በቀን 30ሺ ሜትር ኪዩብ ነው

ለገዳዲ ግድብ

በ1963 ተመሠረተ

47 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

በ1977 ማስፋፊያ ከተደረገለት በኋላና በ1990ዎቹ አጋማሽ የኬሚካል አጠቃቀሙን ማሻሻል እና የሥርጭት መሥመሩን መቀየር ያስቻለ የዕድሳት ሥራ ከተከናወነለት በኋላ ዕለታዊ ውሃ የማማረት አቅሙ በቀን 165ሺ ሜትር ኪዩብ ደርሶ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም በ2007 ዓ.ም. የድሬ ግድብን ውሃ የመያዝ አቅም መጨመርና የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያን ውሃ የማምረት አቅም በ30ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማሳደግ ያስቻለ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተካሒዷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከግድብ በየዕለቱ 195ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ይመረታል፡፡

የከርሠ ምድር ውሃ

ከ1987 ዓ.ም. ወዲህ በከተማዋ ከ100 በላይ ጥልቅና መካከለኛ ጉድጓዶች ተቆፍረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በቀን ከሚመረተው 608ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ውስጥ 413ሺ ሜትር ኪዩብ (67.9%) ያህሉ ከከርሠ ምድር ውሃ መገኛዎች የሚመረት ነው፡፡

የፍሳሽ ማስወገጃ መኪኖች

ያለቦትን የውሃ ክፍያ በቀላሉ ይመልከቱ!

R||divi||400

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም. ተቋማችን በሚሰጠው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች የከተማዋ ህብረተሰብ ረክቶ ማየት እና በዘርፉ የአፍሪካ ከተሞች የልዕቀት ማዕከል ሆኖ መገኘት፡፡
R||divi||400

ተልዕኮ

የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ በማድረግ የውሃ መገኛዎችን በማልማት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓትን በመዘርጋት ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ዕድገት ጋር የሚመጣጠን የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ በበቂና አስተማማኝ ሁኔታ መስጠት፡፡
R||divi||400

እሴቶች

1. አገልጋይነት
2. ቅንነት
3. በጋራ መስራት
4. እውቅና መስጠት
5. ልዕቀት
6. ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ትኩረት የሚሰጥ
7. ፍትሃዊነት
8. እምነት የሚጣልበት

ከ25,000 በላይ አዳዲስ አባ እና እማወራዎች የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ለ25,478 አበወራዎች የፍሳሽ መስመር ቅጥያ በማከናወን ዘመናዊ የፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማረጋገጡ ተገለፀ፣ በመንፈቅ-ዓመቱ ለ14,385 አባወራዎች የፍሳሽ መስመር ለመቀጠል ታቅዶ ለ25,478 አባወራዎች ቅጥያ በማከናወን የፍሳሽ መስመር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በ2017 የመጀመርያው ግማሽ ዓመት የተከናወነው የፍሳሽ መስመር ቅጥያ ከዓምናው...

read more

በሰዎች አስተሳሰብ ላይ መስራት ለሁለንተናዊ ለውጥ ትልቅ ድርሻ አለው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፡፡

ዋና ስራ አስኪያጁ ይህንን ያሉት ዛሬ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የገዳዲ ማሰልጠኛ ተቋም ስልጠና የወሰዱ ሰልጣኞች ባስመረቁበት ወቅት ነው፡፡የሰዎች አስተሳሰብ ላይ ካልተሰራ የህንጻም ሆነ የቴክኖሎጂ ጋጋታ ትርጉም የለውም ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ እንደ ከተማ አስተዳደር ተቋማት በሰው ሃይል መገንባት አለባቸው ተብሎ እየተሰራ ያለውን ስራ የሚያግዝ እና ተስፋ የሚሰጥ ስራ በባለስልጣኑ እየተሰራ መሆኑን ከሰልጣኞች...

read more

ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ዋና ስራ አስኪያጅ

የተቋሙ ተገልጋዮች

||divi||400

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፤

||divi||400

በከተማዋ የሚገኙ የሀገር ውስጥና አለም አቀፋዊ ተቋማት፤

||divi||400

በውሃ መገኛዎች አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች፤

በላይ ደንበኞች

በላይ ሰራተኞች

ቅርንጫፎች

ግድቦች