ዜና

የባለስልጣኑን አፈፃፀም ለማያሳደግ የመሪነት ስልጠና የሚወስዱ ሠራተኞች ወደ ህንድ ተሸኙ

ስልጠናው በዓለም ባንክ በሁለተኛው የከተሞች የውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት አማካኝነት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የአፈፃፀም አቅምን ለመገንባት በታቀደ ዕቅድ መሰረት የተዘጋጀ ነው፡፡ ከባለስልጣኑ የተውጣጡ ሃያ ባለሙዎች እና ሃላፊዎች ከሐምሌ 8–17 ቀን 2011 ዓ.ም ለአስር ተከታታይ ቀናት በህንድ ሃገር የአሰልጣኞች ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን ከተመለሱ ቡኃላ በቀጣይ ሁለት ዓመታት የባለስልጣኑን አጠቃላይ ሠራተኞች...

ባለስልጣኑ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስራ ሊጀመር ነው

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን  በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ  ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለጸ፡፡ ቴክኖሌጂውም ዳፍቴክ ሶሻል አይ.ሲ.ቲ. ከተባለ የግል ድርጅት  ጋር ከባለስልጣኑ ውል በመግባት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ የቆጣሪ ንባብ የሚካሄደው በስማርት ተንቀሳቃሽ ስልኮች ሲሆን ለስልኮቹ የቆጣሪ ማንበብያ አፕልኬሽን ሲሰተም የተጫነላቸው ሲሆን ለዚህም ስራ የሚረዱ 264 ስማርት ተንቀሳቃሽ ግዢ...

የመንገድ ዳር ማረፊያ እና ንፅህና መጠበቂያ በታቀደላቸው መሰረት ግንባታቸው እየተከናወነ መሆኑን ተለጸ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ዕንቅስቃሴ በሚበዛባቸው በተለያዩ የከተማዋ ቁልፍ ቦታዎች ያስገነባቸው የመንገድ ዳር ማርፊያ እና የንጽህና መጠበቂያዎች አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህን የመንገድ ዳር ማርፊያ እና የንጽህና መጠበቂያዎች ከጊዜ ጊዜ እንዲስፋፉ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በያዝነው በጀት ዓመትም ባለስልጣኑ ባወጣው ዕቅድ መሰረት የተለያዩ ተግባራት...

የኮሌራ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል ባለስልጣኑ ከወትሮ በተለየ እየሰራ ነው

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሌራ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል በውሃ ስርጭት እና በፍሳሽ አወጋገዱ ላይ ከወትሮ በተለየ መልኩ በጥንቃቄ እየሰራ ነው፡፡ በተለያዩ አከባቢዎች የተከሰተው የኮሌራ/አተት/ በሽታ በከተማችን ከውሃ ስርጭት ጋር በተገናኘ እንዳይከሰት ባለስልጣኑ በሚያሰራጨው ውሃ ላይ የክሎሪን መጠኑን ጨምሯል፡፡ ባለስልጣኑ በየዕለቱ የላቦራቶሪ ምርመራውን ለማካሄድ በከተማ ውስጥ ከየአካባቢው የሚወስደውን...

ባለስልጣኑ በሀገር አቀፍ የውሃ እና ኢነርጂ ሳምንት በኢግዚብሽን ተሳትፎ እያደረገ ነው

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኔ10-12 /2011 ዓ.ም በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተከበረ በሚገኘው የውሃ እና ኢነርጂ ሳምንት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በኢግዚብሽን በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ በስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ሲምፖዚየሙ እና ኢግዚብሽን  የኢፌድሪ ፕሬዝዳት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ከፍተውታል፡፡ በፕሮግራሙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት...

ፍሳሽ ቆሻሻን የማስወገድ አገልግሎት የግንዛቤ ማስጨበጫ የተዘጋጀ

በመዲናችን አዲስ አበባ ፍሳሽ ቆሻሻን የማስወገድ አገልግሎት የጀመረው በ1920ዎቹ መጨረሻ ገደማ ነው፡፡ ጅማሮው በ1920ዎቹ ይሁን እንጂ፣ ፍሳሽን በዘመናዊ መልኩ በመስመር የማስወገድ ሥራው ከቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ መጠናቀቅ ጋር ተያይዞ በ1974 ዓ.ም ተግባራዊ እንደተደረገ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመቀጠልም በ1993 በቀን 3,000 ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የመቀበል አቅም ያለው የኮተቤ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታው...

ባለስልጣኑ የውሃ ቢል ክፍያን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ለማድረግ ስምምነት አደረገ

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ደንበኞች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ክፍያ መፈጸም የሚያስችላቸውን ስምምነት  አደረገ፡፡ በስምምነቱ መሰረት ባንኩ በከተማዋ ለሚገኙ የውሃ ደንበኞች በአራት አይነት የአከፋፈል ስርዓት ማለትም በሞባይል ባንኪንግ፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ከተቀማጭ በሚቀነስ ሂሳብ እና በባንኩ ቅርንጫፎች አማካኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ደንበኞች በባንኩ መስኮት ለሚያገኙት አገልግሎት ብቻ 2 ብር...

በሁለተኛው ሀገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ አመራሮች እና ሰራተኞች የባለስልጣኑን ቅጥር ግቢ አፀዱ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ  እና የባለስልጣኑ ሰራተኞች በፅዳት ዘመቻው ላይ ተሳትፈዋል። የፅደት ዘመቻው ዘረኝነትን እጠየፋለሁ! አብሮነትን አከብራለሁ! ከተማዬንም አፀዳለሁ! እና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የሚደረገው የጽዳት ዘመቻ አካል ነው፡፡ የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዘርይሁን አባተ በጽዳት ዘመቻ ለተሳተፉ ሰራተኞች ምስጋና...

ለባለስልጣኑ የፍሳሽ መሰረተ ልማቶች ደህንነት ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደረግ ተጠየቀ

የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ከተገነቡበት ዓላማ ውጪ ወደ ፍሳሽ መስመሮች በሚገቡ ጠጣር ነገሮች፣ ቅባትነት ይዘት ያላቸው ነገሮች፣ ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቁ ዝቃጮች እና ወደ ማጣሪያ ጣቢያ የሚገባ ከፍተኛ የሆነ ጎርፍ የቀላቀለ ፍሳሽ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለፀ፡፡ ባለፈው ዓመት ወደ ስራ የገባውና በቀን 100 ሺህ ሜ.ኪብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ በ2011ዓ.ም በዘነበው የበልግ ዝናብ...