የውሃ ዘርፍ

ዝርዝር  አገልግሎቶች  የሚሰጡበት  ቦታ፣  የአገልግሎት  አሰጣጥ  ስታንዳርዶች  እና  ደንበኞች  ሊያማሏቸው  የሚገቡ  ቅድመ  ሁኔታዎች፡-

የውሃ መስመር ማሻሻያ

ጥራት 100% መጠን 12 ሜ
ጊዜ14/ሰዓት
  • የቤት ባለቤትነት ካርታ ወይም ደብተር ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ፣
  • የአገልግሎት ጠያቂው የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
  • ተወካይ ከሆኑ የውክልና ደብዳቤ፤
  • የወረዳ ወይም የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ከሆነ ከወረዳ ወይም ከኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ እና የመንግስታዊና ህዝባዊ ድርጅቶች ከሆነ ከተቋሙ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ፣
  • የመንግስት መስመር በሌለበት የሚቀርብ አዲስ የውሃ መስመር ቅጥያ ጥያቄ ውሃ ካስገባ ነባር ደንበኛ መስመር ላይ ለመቀጠል የባለመስመሩ ፍቃድ ስለሚያስፈልግ የነባሩ ደንበኛ የፍቃደኝነት ደብዳቤና የውሃ ቢል ኮፒ ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፣
  • ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

የውሃ መስመር ማዛወሪያ

ጥራት 100% መጠን 12 ሜ
ጊዜ14/ሰዓት
  • የቤት ባለቤትነት ካርታ ወይም ደብተር ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ፣
  • የአገልግሎት ጠያቂው የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና ፎቶኮፒ፣
  • ተወካይ ከሆኑ የውክልና ደብዳቤ፤
  • የወረዳ ወይም የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ከሆነ ከወረዳ ወይም ከኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ እና የመንግስታዊና ህዝባዊ ድርጅቶች ከሆነ ከተቋሙ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ፣
  • ደንበኞች የቤት ባለቤትነት ካርታ ወይም ደብተር ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ካልቻሉ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባዘጋጀው መተማመኛ ቅፅ ላይ በመፈረም አገልግሎቱን ያገኛሉ፣
  • ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

የደንበኛ የውሃ መስመር ጥገና

ጥራት 100% መጠን 3 ሜትር/ 1 በቁጥር/
ጊዜ4/ሰዓት
  • መስመር ይጠገንልኝ ጥያቄ፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

የደንበኛ ቆጣሪ በማንሳት መመርመር

ጥራት 100% መጠን በቁጥር 1
ጊዜ4/ሰዓት
  • የዉሃ ብክነት ጥቆማ፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

የውል ኮፒ ይሰጠኝ ጥያቄ

ጥራት 100% መጠን በቁጥር 1
ጊዜ30/ደቂቃ
  • ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ የውሃ ቢልና የወረዳ መታወቂያ ማቅረብ፣
  • ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

የአገልግሎት ሂሳባቸውን ያልከፈሉ ደንበኞችን አገልግሎት ማቋረጥ

ጥራት 100% መጠን በቁጥር 1
ጊዜ4/ሰዓት
  • የአገልግሎት ክፍያ በወቅቱ አለመከፈሉ ሲረጋገጥ፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

ደንበኞች እዳቸውን እንደከፈሉ ቆጣሪ መልሶ መቀጠል

ጥራት 100% መጠን በቁጥር 1
ጊዜ4/ሰዓት
  • የውሃ አገልግሎት የተከፈለበት ቢል፣
  • የመስመር ማስቀጠያ ክፍያ 56 ብር መፈጸም፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

ለምርመራ የተነሳውን ቆጣሪ መልሶ መቀጠል

ጥራት 100% መጠን በቁጥር 1
ጊዜ4/ሰዓት
  • የውሃ አገልግሎት መጨረሻ የተከፈለበት አንድ ቢል፣
  • የመስመር ማስቀጠያ ክፍያ 56 ብር መፈጸም፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

የመስመር መበከል እና የማስተካከያ ስራ መስራት የላቦራቶሪ ምርመራ /ባክትሮሎጂ እና ኬሚካል/

ጥራት 100% መጠን በቁጥር 1
ጊዜ3/ሰዓት
  • የዉሃ ብክነት መኖሩን መረጃ ማቅረብ፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

ውሃ በሮቶ ማደል ስራ ሳይቆራረጥ ማቅረብ

ጥራት 100% መጠን በቁጥር 1
ጊዜ8/ሰዓት
  • የአገልግሎት ክፍያ መክፈል፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

የቦኖ ውሃ መስመር ቅጥያ (12 ሜትር)

ጥራት 100% መጠን በቁጥር 1/በሜትር 12/
ጊዜ3/ሰዓት
  • ከሚኖሩበት ወረዳ ወይም ክ/ከተማ ከስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የትብብር ደብዳቤ እና የወረዳውን መታወቂያ ማቅረብ፣
  • ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
  • በመመሪያዉ መሰረት ከሌሎች ቦኖዎች ያለዉን ርቀት እና በአካባቢዉ ያለዉን የህዝብ ቁጥር ማሟላት፣
  • የተጠቃሚዎችን አባዎራዎች በዝርዝር ማቅረብ፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት

የመንግስት የውሃ መስመር ጥገና

ጥራት 100% መጠን 6 ሜትር/ 1 በቁጥር/
ጊዜ5/ሰዓት
  • መስመር ይጠገንልኝ ጥያቄ፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- ከ4ኢንች በታች በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት ከ4ኢንች በላይ በማዕከል በከፍተኛ መስመር ዝርጋታና ጥገና ኬዝቲም

የመንግስት መስመር ዝርጋታ

ጥራት 100% መጠን በቁጥር 1 (1 ኪ.ሜ)
ጊዜ3/ቀን
  • የአገልግሎት ጥያቄ ማቅረብ፣
  • በአካባቢው የተዘረጋው መስመር በዕቅድ የተያዘ መሆን አለበት፣
  • አገልግሎቱ የሚሰጥበት የስራ ሂደት:- ከ4ኢንች በታች በቅርንጫፍ የዉሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት ከ4ኢንች በላይ በማዕከል በከፍተኛ መስመር ዝርጋታና ጥገና ኬዝቲም

የተጠቃሚዎች መብት እና ግዴታ

  • ማንኛውም ደንበኛ ተቋሙ የሚጠይቃቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ንፁህ የመጠጥ ውሃ የማግኘት መብት ኣላቸው፤
  • ማንኛውም ተገልጋይ ከሥራ ሂደቱ አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ በማናቸውም ጉዳይ ላይ የተሰማውን ቅሬታ ወይም አቤቱታ የማቅረብ እና ምላሽ የማግኘት መብት አለው፤
  • ስለ አገልግሎቱ በቂ መረጃ እና የምክር አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፤
  • ለአገልግሎት የሚጠየቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ፍትሃዊና አድሎ የሌለው አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፤
ተገልጋዮች አገልግሎት የማግኘት መብት

  • ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና የፍሳሽ ማስወገድ ስርዓት ለህብረተሰቡ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተደራሽ ማድረግ፤
  • የባለስልጣን መ/ቤቱን የስትራቴጂክ ዘመኑን ዕቅድ፣ አመታዊ ዕቀድ ዝግጅት እና የአፈጻጸም ግምገማ ላይ የህዝብ አደረጃጀት ፎረሞችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ማሳተፍ፤
  • ባለስልጣን መ/ቤቱ በውሃ እና በፍሳሽ ዘርፍ ለሚሰጣቸው አገልግሎት በቂ ግብዓት የማቅረብ፤
  • በተቀመጡ ስታንዳርድ መሰረት አገልግሎት መስጠት፤
  • ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በባለስልጣን መ/ቤቱ ስለሚሰጡ አግልግሎቶች ሙሉ መረጃ ግልጽ በሆነ መልኩ ማቅረብ እና ማሳወቅ፤
  • በተገልጋዩ ህብረተሰብ ለሚፈጠሩ ቅሬታዎች በባለስልጣን መ/ቤቱ ለቅሬታ አፈታት በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ምላሽ መስጠት፤
  • ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ፍትሃዊ፣ አድሎ የሌለበት አገልግሎት የመስጠት እና በእኩልነት የማገልገል፤
  • በየጊዜው የህብረተሰቡ እርካታ ያለበትን ደረጃ መለካት፤
  • ዜጎች በተቋሙ አፈጻጸም ምዘና ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ፤
  • የባለስልጣን መ/ቤቱን ህግና ስርዓት ለደንበኞች ማሳወቅ፤
የባለስልጣን መ/ቤቱ ግዴታዎች

  • በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እና ማቅረብ፤
  • በተቋሙ የሚቀርቡ አገልግሎቶች እና ንብረቶች (ውሃ፣ የውሃ ቆጣሪ እና የውሃ መስመሮች ወ.ዘ.ተ)እና የውሃ ብክነትን ለመቀነስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በአግባቡ መጠቀምና የሚፈስ ውሃ ሲኖር መጠቆም፤
  • የባለስልጣን መ/ቤቱን ህግና ስርዓት ማክበር፤
የተገልጋዮች ግዴታ

ደንበኞች በማንኛውም ሁኔታ በአገልግሎት አሰጣጡ ቅሬታ ካጋጠማቸው ቅሬታቸውን ሊያቀርቡበት የሚችሉበት ስርዓት በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽባለሥልጣን ዋናው መሥሪያ ቤት እና በስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተዘረጋ ሲሆን ተገልጋዮችም በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ የሚያጋጥሟቸውን ቅሬታዎችበየደረጃው ላሉ ፈፃሚዎች፣ የቅርብ ሃላፊዎች፣ ለበላይ አመራሮች በማንኛውም ሰዓት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ላቀረቡት ቅሬታ በቂ ምላሽ ካላገኙዋናው መሥሪያ ቤት እና በየቅርንጫፎቹለተቋቋሙ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በማቅረብ ቅሬታቸው በገለልተኝነት እንዲታይላቸው ማድረግ ይችላሉ፡፡ ተገልጋዮችበባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ደረጃ በደረጃ ቅሬታቸው ካልተፈታ ወደ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ፍርድ ቤቶች እና መገናኛ ብዙሃንበመሄድ ቅሬታቸው እንዲፈታላቸው ማድረግ ይችላሉ፡፡

  • ማንኛውም ተገልጋይ ከሥራ ሂደቱ አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ ያለመርካት ባስከተለበት በማናቸውም ጉዳይ ላይ የተሰማውን ቅሬታ ወይም አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፤
  • የተገልጋይ አለመርካት ቅሬታ ወይም አቤቱታ ለማቅረብ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮች፡-
    • አገልግሎት ለማግኘት ካለው ህጋዊ መብት፣
    • ከአገልግሎት አሠጣጥ ሠርዓቶእ እና የአሰራር ሂደቶች
    • ከአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ማለትም ከጥራት፣ ከሚወስደው ጊዜ፣ ምልልስ እና ውጤታማነት አንጻር፣
    • አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ቦታዎች
    • ከአገልግሎት ክፍያ እና ከፈጻሚ ሠራተኞች ሠነ-ምግባር ጋር በተያያዘ፣
  • በተገልጋዩ የሚቀርቡ ቅሬታንም ሆነ አቤቱታ የማስተናገድ እና ፈጣን ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት፤
  • ቅሬታ እና አቤቱታ ሊቀርብባቸው የሚችሉ ጉዳዮችን እና የሚቀርቡበትን ደረጃ ለተገልጋዮች ማሳወቅ አለበት፤
  • በአገልግሎት አሰጣጥ ላልረካና ቅር ለተሰኘ ተገልጋይ በመስሪያ ቤቱ የመረጃ ዴስክ ሠራተኛ አማካኝነት የቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት ሥራዓጥን ለተገልጋዩ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፤
  • ቅሬታ በተገልጋዩ ወይም በወኪሉ በጽሁፍ፣ በቃል፣ በፋክስ፣ በኢ.ሜይል ወይም በስልክ አገልግሎት ሰጪ /ፈፃሚ/ ለሚገኝበት የሥራ ሂደት መሪ ወይም አስተባባሪ ሊቀርብ ይችላል፤
  • ማንኛውም አቤቱታ በተገልጋዩ ወይም በወኪሉ በጽሑፍ ወይም ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ፎርም እየተሞላ ለቅሬታ እና አቤቱታ ሰሚ አካ ሊቀርብ ይችላል፡፡
  • የተገልጋዩን ሙሉ ስም እና አድራሻ፣
  • ቅሬታው ወይም አቤቱታው የቀረበበትን ዋና ጉዳይ፣
  • መንስኤ የሆነውን ድርጊት በአጭሩ፣ የተፈጸመበት ቀን እና ቦታ፤
  • ጉዳዩ የሚመለከተውን የስራ ሂደት እና አገልግሎት ሰጪ/ፈፃሚ/፣
  • ደጋፊ ማስረጃዎች ካሉ በአባሪነት፣
  • ተገልጋዩ እንዲደረግለት የሚፈልገው መፍትሔ፣

 

አስተያየት መስጫ  ዘዴዎችን  በተመለከተ

በተቋሙ በሚሰጡ አገልግሎቶች ዙሪያ ከተገልጋዮችም ሆነ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሰጡ አወንታዊም ሆኑአሉታዊ አስተያየቶች ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መሻሻል እንደ ግብዓት የሚያገለግሉ መሆናቸውን በመገንዘብ በዋናው መ/ቤትም ሆነ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ህብረተሰቡ አስተያየት ሊሰጥ የሚችልባቸው ሀሳብ መስጫ ሳጥኖች፣ መዝገቦች እና ቅጾች እንዲሁም የነጻ አገልግሎት ስልኮች ተዘጋጅቷል፡፡ በእነዚህ ሀሳብ መስጫዎች የሚገኙ አስተያቶችን የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው በመሰብሰብ በፕሮሰስ ካውንስል እንዲታይ ከተደረገ በኃላ የፕሮሰስ ካውንስሉ ለቀረቡ አስተያየቶች ምላሾቻቸውንና የሚወሰዱ እርምጃዎችን እንዳስፈላጊነቱ በጽሁፍ ቦርድ ላይ በመለጠፍ ደንበኞች እንዲያውቁት ያደርጋል፡፡

የመረጃ  ማስተላለፊያ  አግባቦች

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሃሙስ ጠዋት ከ2፡30-6፡30፤ አርብ ከ2፡30-5፡30፤ ዘወትር ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሲሆን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሚሰጣቸው አገልገልግሎቶች (የውሃ እና የፍሳሽ መስመሮች ሲሰበሩ፣ በማንኛውም መንገድ የውሃ መቋረጥ ሲያጋጥም) እንዲሁም ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካልዎት የተዘረዘሩትን የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች በመጠቀም ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ድህረ ገጽ፡- www.aawsa.gov.et ኢሜይል፡-info@aawsa.gov.et ፖ.ሳ.ቁ.1505 አ.አ. ኢትዮጵያ ፋክስ፡-0116623924

. የስራ ኃላፊነት የኃላፊው ሥም ልዩ ቦታው ክፍለ ከተማ ወረዳ ቢሮ ቁጥር የአመራሩ ስልክ መረጃ ለመጠቅ ሆነ ለመስጠት ስልክ ቁጥር
1.   ዋናው መሥሪያ ቤት
1.1 የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ

 

ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ

መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ ቦሌ ክፍለ ከተማ 05 0116623902  

 

 

 

 

0116623927

1.2 የባለስልጣን መ/ቤቱ የፍሳሽ ም/ስ/አስኪያጅ አቶ ተስፋለም ባዩ መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ ቦሌ ክፍለ ከተማ 05 0116623781  

 

 

 

 

0116623921

1.3 የዋና ስራስኪያጅና ቦርድ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ እፀገነት ተስፋዬ መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ ቦሌ ክፍለ ከተማ 05
1.4 የባለስልጣን መ/ቤቱ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የስራ ሂደት ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ ቦሌ ክፍለ ከተማ 05 0116187643  

 

 

 

 

 

0116188638

1.5 ሀብት/አስ/ክ/ዘ/ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ደገፋ ቶሎሳ ዋናው መስሪያ ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ 05  0116674832  

 

 

 

0116187641/42/43 በነጻ ስልክ 906

1.6 ውሃ አቅ/ም/ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ዘለቀ ዋናው መስሪያ ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ 05 0116623782
. የስራ ኃላፊነት የኃላፊው ሥም ልዩ ቦታው ክፍለ ከተማ ወረዳ ቢሮ ቁጥር የአመራሩ ስልክ መረጃ ለመጠቅ ሆነ ለመስጠት ስልክ ቁጥር
2.     ፕሮጀክት /ቤት
2.1 የፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ

አቶ ስዩም ቶላ

ወረዳ 06 አስተዳደር ጽ/ቤት ፊት ለፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ 06 0118951478/79
3.     ቅርንጫፍ /ቤቶች
3.1 የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቶ አምባዬ አሰፋ 6 ኪሎ ከተፈሪ መኮንን ኮሌጅ አጠገብ ጉለሌ ክፍለ ከተማ 03 0111231652  

 

 

 

 

0111222931

3.2 የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቶ ወርቁ ገዳ የቀድሞ እስላም መቃብር ፊት ለፊት አዲስ ከተማ ክ/ከተማ 06 0112772799  

 

 

 

0112772711

3.3 የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቶ ደረጀ ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ጉለሌ ክፍለ ከተማ 05 0111113448  

 

 

 

0111114435

3.4 የመገናኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቶ አህመድ መሀመድ መገናኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አጠገብ ቦሌ ክፍለ ከተማ

 

 

 

 

05 0116188015  

 

 

 

 

0116511839

3.5 የጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቶ መሀመድ ካሣው ወረዳ 06 አስተዳደር ጽ/ቤት ፊት ለፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ 06 0116676524  

 

 

 

01166765427

3.6 የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቶ ሙሉጌታ አስፋው የጎተራ ማሳለጫ ምስራቅ ዱቄት ፋብሪካ አጠገብ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ 03 0114671589  

 

 

 

0114671366

3.7 የመካኒሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ወ/ሪት ሀዊ

ብስራተ ገብርኤል አካባቢ ከብሩከ ሆስፒታል ዝቅ ብሎ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 03 0113729735  

 

 

 

 

0113729728

3.8 የአቃቂ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቶ ሰለሞን ታፈሰ አቃቂ ሚሽን ት/ቤት ጀርባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 01  

 

 

 

0114343716