እንኳን ደህና መጣችሁ!!!

የድሬ ግድብ

ግንባታው በ1991 ተጠናቀቀ

21 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

የገፈርሣ ግድብና ማጣሪያ ጣቢያ

ግንባታው በ1948 ተጠናቀቀ

በ2001 በጀት ዓመት የጥገና ሥራ ከተካሔደለት ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅሙ ወደ 9.5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ያደገ ሲሆን ውሃ የማምረት አቅሙም በቀን 30ሺ ሜትር ኪዩብ ነው

ለገዳዲ ግድብ

በ1963 ተመሠረተ

47 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

በ1977 ማስፋፊያ ከተደረገለት በኋላና በ1990ዎቹ አጋማሽ የኬሚካል አጠቃቀሙን ማሻሻል እና የሥርጭት መሥመሩን መቀየር ያስቻለ የዕድሳት ሥራ ከተከናወነለት በኋላ ዕለታዊ ውሃ የማማረት አቅሙ በቀን 165ሺ ሜትር ኪዩብ ደርሶ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም በ2007 ዓ.ም. የድሬ ግድብን ውሃ የመያዝ አቅም መጨመርና የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያን ውሃ የማምረት አቅም በ30ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማሳደግ ያስቻለ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተካሒዷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከግድብ በየዕለቱ 195ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ይመረታል፡፡

የከርሠ ምድር ውሃ

ከ1987 ዓ.ም. ወዲህ በከተማዋ ከ100 በላይ ጥልቅና መካከለኛ ጉድጓዶች ተቆፍረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በቀን ከሚመረተው 608ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ውስጥ 413ሺ ሜትር ኪዩብ (67.9%) ያህሉ ከከርሠ ምድር ውሃ መገኛዎች የሚመረት ነው፡፡

የፍሳሽ ማስወገጃ መኪኖች

R

ራዕይ

በ2012 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማን የንፁህ ውሃ አቅቦትና
የዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ደረጃ በአፍሪካ ካሉት
ቀዳሚ አምስት ከተሞች ተርታ ማሰለፍ፡፡

R

ተልዕኮ

የውሃ መገኛዎችን በመጠቀም እና የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓትን
በመዘርጋት፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት
ከአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ዕድገት ጋር የሚመጣጠን የንፁህ
ውሃ አቅርቦት እና የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት
ለከተማዋ ነዋሪ በበቂና አስተማማኝ ሁኔታ መስጠት፡፡

R

እሴቶች

ንፁህ ውሃ ለሁሉም የከተማዋ ነዋሪ እናቀርባለን!
ከፍሳሽ ቆሻሻ የፀዳ ከተማ እንፈጥራለን!
በማያቋርጥ ለውጥ እና መሻሻል እናምናለን!
በዕውቀትና በእምነት እንመራለን!
ፈጣን ምላሽ መስጠት የዕለት ተዕለት ተግባራችን ነው!
ግልፅነትና ተጠያቂነት የአገልግሎታችን መገለጫዎች ናቸው!
ቅንጅታዊ አሰራር ለተልዕኮአችን መሠረት ነው!

ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታና ቅጥያ ስራዎች በህብረተሰብ ተወካዮች ተጎበኙ፡፡

ባለስልጣኑ የመዲናዋን የፍሳሽ አወጋገድ ዘመናዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ሲሆን የጉብኝቱ አላማም ፍሳሽ በመስመር ወደ ማጣሪያ ጣቢያ እንዲገባ የተዘረጉ መስመሮችን መሰረት በማድረግ ነዋሪው ከቤቱ ቅጥያ እንዲያሰራ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ፡፡ በባለስልጣኑ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር ባሉ ሁሉም ወረዳች በተሰራ የመስመር ዝርጋታ እና ቤት ለቤት ቅጥያው ላይም 12 ተቋራጮች እና በ47 ጥቃቅን አነሰተኛ ማህበራት ተሳትፈዋል...

read more

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ባለፉት 8 ወራት ከ27 ኪሎ ሜትር በላይ ያረጁ መለስተኛ የውሃ መስመሮችን ቀየረ፡፡

የመስመር ቅየራ የተደረገው በባለስልጣኑ 8 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አማካኝነት ሲሆን ባለፉት ስምንት ወራት 28 ኪ.ሜ መለስተኛ መስመር ለመቀየር ታስቦ የዕቅዱን 94.41% ማከናወን ተችሏል፡፡ ከዚህ በፊት ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩና ያረጁ የብረት መስመሮች በፕላስቲክ የውሃ መስመሮች መቀየራቸው ባለስልጣኑ አምርቶ የሚያሰራጨውን ንፁህ ውሃ ከብክነት እና ብክለት በማዳን በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡...

read more

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ሠራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ

ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ሙሉ ጤነኛ የሆነ ማንኛውም ዜጋ በየ 3 ወሩ ደም ቢለግስ የአዕምሮ እርካታ ከማግኘቱ በተጨማሪ በወሊድ ምክንያት ደም አጥተው የሚሞቱ እናቶቻችን እና በተለያየ ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ግለሰቦችን ህይወት መታደግ ይቻላል፡፡ “እኛ ጤናማ ሆነን ደም ካልሰጠን የታመሙትን ማዳን አንችልም…!” ያሉት የባለስልጣኑ ሠራተኞች በደም እጦት ምክንያት ህይታቸውን ማትረፍ ለማይችሉ ዜጎች እንዲውል በበጎ...

read more

ወቅታዊ…

የስራ ማስታወቂያ

ያለቦትን የውሃ ክፍያ በቀላሉ ይመልከቱ!

የቢል መረጃ

ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ዋና ስራ አስኪያጅ

መልእክት

የተቋሙ ተገልጋዮች

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፤

በከተማዋ የሚገኙ የሀገር ውስጥና አለም አቀፋዊ ተቋማት፤

በውሃ መገኛዎች አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች፤

በላይ ደንበኞች

በላይ ሰራተኞች

ቅርንጫፎች

ግድቦች