ዜና

ሰብል የተሰበሰበላቸው አዛውንት በእጅጉ መደሰታውን ገለጹ።

አርሶ አደር ሀይሌ ጸጋዬ በመዲናዋ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ 11 ቱሉ ጉዶ አካባቢ ነዋሪ ናቸው፡፡ በደካማ አቅማቸው ያመረቱት ምርት ከጎተራቸው ይገባ ዘንድ ጉዳት ሳይደርስበት መሰብሰብ አለበት ! እርሳቸው ግን ለዚህ የሚሆን አቅም አልነበራቸውም፡፡ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የመካኒሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እንደ ሀገር የተላፈውን ጥሪ በመቀበል ሠራተኞቹን ፣ አመራሮችን ፣የቆፋሪ እና አንባቢ ማህበራትን እንዲሁም የውሃ...

10ኛው የህብረት ስምምነት ሰነድ የፊርማ ሥነ ስርዓት ተደረገ::

ህብረት ስምምነቱ የተፈረመው በውሃና ፍሳሽ በባለስልጣን ማኔጅመንት እና በመሠረታዊ የሠራተኞች ማህበር መካከል ነው፡፡ ህብረት ስምምነቱ ከዚህ በፊት ለ14 ዓመታት በተግባር ላይ የቆየውን 9ኛውን ስምምነት በመተካት በቀጣይ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ሠራተኞች በሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ልክ ተጠቃሚ በማድረግ ባለስልጣኑን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ ረዘም...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የፉሪ ሀና የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮጀክት ዋና የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ በራስ ሀይል እያከናወነ ነው ።

የባለስልጣኑ የፍሳሽ ዘርፍ ም/ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢ/ር አለማየሁ መንግስቱ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታን ለማፋጠን በ4 ቡድን የተደራጀ የራስ ሀይል በማስገባት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል...

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ሰራተኞች እና አመራሮች ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መረሀ ግብሩን አጠናረው ቀጥሏል ፡፡

ዛሬም በባለስልጣኑ ዋናው መስሪያ ቤት "ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን " በሚል መሪ ቃል ደም ለግሰዋል፡፡ በመረሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ወርቁ አንዱዓለም የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ዓላማ የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ሀገር አፍራሾችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ለሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ሰራተኛው የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው ብለዋል። ሊቀመንበሩ...

ከኬንያ የመጡና 11 የስራ ኃላፊዎች ዛሬ የባለስልጣኑን የውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማቶች ጎበኙ ፡፡

ሀላፊዎቹ ከኬኒያ ናኩሩ የመጡና በየውሃና ፍሳሽ ላይ ከሚሠሩ ሦስት ድርጅቶች የተውጣጡ ሲሆን ዛሬ የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን፣ መካኒሳ ቆጣሪ ያልተማከለ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን እና የለገዳዲ ግድብና ማጣሪያ ጣቢያን...

ባለስልጣኑ ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በከተማዋ ኪስ ቦታዎች ያስገነባቸውን አራት የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች ዛሬ አስመርቋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡት አራት የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች በኮልፌ ቀራኒዮ እና ጉለሌ ክ/ከ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በጥቅሉ በቀን 9ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችሉ ናቸው ፡፡ የፕሮጀክቶቹ በተዘረጉ መስመሮች ለተጠቃሚው እንዲደርሱ የተደረገ ሲሆን በተሰሩበት አካባቢ ፈረቃ እንዲሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ...

የአዲስአበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአዲስአበባ ሴቶች ማኅበር የጥቃት ማገገሚያ ውስጥ ለሚገኙ 60 ሴቶች የቁርስ በጀት ድጋፍ አደረገ።

በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ እና የተለያዩ ጥቃቶች ተፈጽመውባቸው በማገገም ላይ ላሉ 60 ሴቶች 15 ሺህ ብር የሚያወጣ የሩዝና የፖስታ ድጋፍ ተደርጓል ። ድጋፉን ያስረከቡት በባለሥልጣኑ የቦርድና ስራ-አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት መሠረት አሰፋ በቀጣይም ሌሎች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረግና ከጎናችሁ ለመሆን ዝግጁ ነን ብለዋል። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዘንድሮ በዓለም ደረጃ ለ110ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ "የሴቶችን...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ከ112 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃን ከብክነት ማዳን ችሏል፡፡

በባለሥልጣኑ ውሃውን ከብክነት ያዳነው፡- ያረጁ መለስተኛ እና ከፍተኛ የውሃ መስመሮችን በመቀየር፣ ተከታታይነት ያለው መደበኛ የውሃ ብክነት ምርመራ እና ቁጥጥር ስራ በተለያዩ መሳሪያዎች በማከናወን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እያንዳንዱ ቅርንጫፎች የሚገባውን እና የሚወጣውን የውሃ መጠን ለመቆጣጠር ከፍተኛ እና በመለስተኛ መስመር ላይ 53 የውሃ ቆጣሪዎችን በመትከል እንዲሁም ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ ቆጣሪዎች በመቀየር እና...

ባለስልጣን መ/ቤቱ በአቃቂ ቅ/ፅ/ቤት የህፃናት ማቆያ አገልግሎት መስጫ ማዕከል አቋቋመ::

የህፃናት ማቆያ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የአሰራር መተዳደሪያ ደንብ ባለስልጣን መ/ቤቱ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 89/7 እንደተረጋገጠው መንግስት በአገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት የሚሳተፉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ሃላፊነት አለበት የሚለውን ለመተግበር የሚያስችሉ ስራዎችን በእቅዱ አካቶ የሚሠራ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንዱ የእዝብ ተሳትፎን ማረጋገጥና ዘርፈ ብዙ ተግባራትን...