ዜና

ባለሥልጣኑ ባለፉት 10 ወራት 625 272 ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃ ከብክነት ማዳን ችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ብክነቱን በመስመር ሂደት የሚባክን (physical loss) እና ከውሃ ቆጣሪ ጋር የተያያዘ ብክነት (commercial loss) በመለየት የቁጥጥር ስራ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡የሚባክነውን ውሃ ማዳን የተቻለውም በመሣሪያ በመታገዝ ተከታታይነት ያለው የውሃ ብክነት ምርመራ እና ቁጥጥር (Active leak detection) ስራ በ305 ኪሎ ሜትር መለስተኛ የውሃ መስመር ላይ በመስራት...

ባለስልጣኑ በቀጣይ 3 ወራት የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ከአመራሮች ጋር እየተወያየ ነው ።

ቀጣይ ሶስት ወራት የሚሰሩ እቅዶች በፍጥነት ፣በጥራት እና ችግር ፈቺ በሆነ መንገድ ለመተግበር ይቻል ዘንድ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ተብሏል ።በተለይ ደግሞ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዪ ችግሮችን መፍታት በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ነው የተመላከተው ።በውይይቱ ላይ የየዘርፉ እቅድ የቀረበ ሲሆን በታቀደው ልክ ጊዜ የለኝም በሚል መንፈስ መፈጸም የሁሉም ሀላፊነት መሆን እንደሚገባ...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የእግር ኳስ ቡድን ከኤርፖርት ጉምሩክ የእግር ኳስ ክለብ ጋር አቻ ወጥቷል።

በየካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ሜዳ ዛሬ የተጫወቱት ሁለቱ ክለቦች አቻ ወጥተዋል።የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ባዘጋጀው በዚህ ወድድር የባለሥልጣኑ የእግር ኳስ ክለብ እስካሁን በአምስት ጨዋታ አራቱን በማሸነፍ እና የዛሬውን አቻ በመውጣት 13 ነጥቦችን መሰብሰብ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አመራርና እና አባላት የባለስልጣኑን ስራዎች ጎበኙ።

ቋሚ ኮሚቴው የለገዳዲ ክፍል ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክት ፣ የቦሌ አራብሳ ፣ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤት ፣ የቦሌ ቡልቡላ እና ሪፌንቴ አካባቢ እየታሰሩ ያሉ የውሃ እና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ምልከታ አድርገዋል።የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢው የተከበሩ ወ/ሮ ልእልቲ ግደይ ባለስልጣኑ በተለይ የህዝብ ቅሬታ የሚነሳባቸውን ቦታዎች በመለየት አፋጣኝ መፍትሄ ማበጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።በተለይ መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው የጋራ...

ከቱሉ ዲምቱ እስከ ቃሊቲ አደባባይ ሲሰራ የነበረው የውሃ መስመር የማዛወር ስራ ተጠናቀቀ ::

በመንገድ ሥራ ምክንያት ከአቃቂ ክፍል 1 ወደ ከተማ ውሃ ይዞ የሚመጣውና 18.94 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ከፍተኛ የውሃ መስመር ማዛወር ስራ ተጠናቆ ለመንገድ ስራው ክፍት ተደርጓል፡፡የመስመር ማዛወር ስራው በ48 ሚሊየን 876 ሺህ 163.72 ብር እና በ7 ሚሊየን 245 ሺህ 883.4 የአሜሪካን ዶላር ወጪ በአሰር ኮንስትክሽን ኃ.ግ.ድ እና በIFH ኮንስትክሽን አማከኝነት ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡የከፍተኛ የውሃ መስመር ማዛወር...

በባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ38 ሺኅ በላይ አባወራዎችን የፍሳሽ በመስመር አገልግሎት ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማዋን የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ለማዘመን በከተማው ባስገነባቸው ከ40 በላይ የተማከሉ እና ያልተማከሉ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ነዋሪውን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡በዚሁ መሰረት በስድስት ወራት ውስጥ የፍሳሽ መሰረተ ልማት በተዘረጋባቸው አካባቢዎች ለ31,755 አባወራ የፍሳሽ መስመር ቅጥያ ለማከናወን ታቅዶ ለ38,114 አባወራዎች መስመር በማገናኘት...

የረጅም ጊዜ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ችግሩ ሙሉ ለሙሉ ተፈቷል፡፡

ጣፎ አደባባይ አካባቢ የሚገኝ የየካ አባዶ ሳይት የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመር ባልተገባ አጠቃቀም ምክኒያት ተዘግቶ ፍሳሹ እየገነፈለ ለነዋሪዉ ፈተና ፤ለአላፊ አግዳሚው ለመጥፎ ጠረን ዳርጎ ሰነባብቷል፡፡ፍሳሹም በማንሆል ገንፍሎ መንገድ ላይ በመፍሰሱ ምክኒንያት ነዋሪዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ከስፍራው የፍሳሽ ቆሻሻ ሰብስቦ ወደ ኮተቤ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የሚያጓጉዘው ከፍተኛ የፍሳሽ መስመር መዘጋትን ተከትሎ ችግሩን...

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የ490 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ባለስልጣኑ የተፈራረመው ከጃፓን ዓለም አቀፍ ድርጅት (JICA) ጋር ሲሆን ስምምነቱም በውሃ ብክነትን መቀነስ እና ስርጭቱን ማስተካከል ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ከ51ሺኅ በላይ ደንበኞችን ያቀፈ ሲሆን በንፋስ ስልክ እና መካኒሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ላይ የሚተገበር ነው ፡፡በአሁኑ ሰዓትም ከተጠቀሱት አካቢዎች መረጃ በመሰብሰብ እና የተመረጡት ቅርንጫፎች ወቅታዊ የሆነ መሰረተ ልማቶችን ካርታ ላይ የማስፈር ስራ በመስራት ላይ...

ባለስልጣኑ ከ741.9 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሠበሰበ።

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት 5 ወራት 776 ሚሊየን 350 ሺህ 677 ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 741 ሚሊየን 987 ሺህ ብር በላይ በመሰብሰብ የዕቅዱን 96 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡ገቢው የተሰበሰበው በውሃ አገልግሎት ዘርፍ ከሚሠጡ የውሃ ሽያጭ፣ የቆጣሪ ግብር፣ ከውሃ መስመር ቅጥያ ሲሆን በፍሳሽ አገልግሎት ዘርፍ ከፍሳሽ ማንሳት አገልግሎት፣ ከአዲስ ደንበኞች የፍሳሽ መስመር ቅጥያ፣...