ከ25,000 በላይ አዳዲስ አባ እና እማወራዎች የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ለ25,478 አበወራዎች የፍሳሽ መስመር ቅጥያ በማከናወን ዘመናዊ የፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማረጋገጡ ተገለፀ፣ በመንፈቅ-ዓመቱ ለ14,385 አባወራዎች የፍሳሽ መስመር ለመቀጠል ታቅዶ ለ25,478 አባወራዎች ቅጥያ በማከናወን የፍሳሽ መስመር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በ2017 የመጀመርያው ግማሽ ዓመት የተከናወነው የፍሳሽ መስመር ቅጥያ ከዓምናው...

ባለስልጣኑ ባለፉት 9 ወራት 140.3 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ አምርቶ አሰራጭቷል፡፡

ባለስልጣኑ ከገፀ ምድር እና ከርሰ ምድር የውሃ መገኛዎች አለም አቀፍ ጥራቱን የጠበቀ 140.3 ሚሊዮን ሜ. ኪ ውሃ አምርቶ ማስራጨት መቻሉ ተገልጿል ። ከገጸ ምድር የውሃ መገኛዎች 55.75 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ እንዲሁም ከከርሰ ምድር የውሃ መገኛዎች 84.58 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ በማምረት ለነዋሪዎች ተደራሽ ለማድረግ ተችሏል ፡፡ ይህም ከእቅዱ 85 % ያህል ሲሆን የእቅዱን ያክል ማሳካት ያልተቻለው በኤሌክትሮ ሜካኒካል...

ባለለስልጣኑ የሲቢሉ የውሃ ግድብ ፕሮጀክት ፋይናንስ እንዲያደርግ የአለም ባንክን ጠየቀ፡፡

በአለም ባንክ የውሃ ሲንየር ግሎባል ዳይሬክተር ሳሮጅ ኩማር ጃህ የተመራው ልኡክ ዛሬ የድሬ እና ለገዳዲ ግድብ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የሲቢሉ ግድብ ፕሮጀክት የፋይናንስ ጉዳይ እና በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራውን የግድቡ ውሃ ማስተንፈሻ በሮች ጥገና ስራ ላይ ያተኮረ ውይይትም ተደርጓል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዘሪሁን አባተ የአለም ባንክ ግሩፕ ለባለስልጣኑ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፤...

በዓለም ባንክ ግሩፕ የምስራቅ ፣መካከለኛ እና ደቡብ አፍሪካ ወተር ፕራክቲስ ማናጀር ሶማ ጎሽ ሙሊክ እና ልዑካቸው የባለስልጣኑን መሠረተ ልማቶች ጎበኙ።

ማናጀሯ እና ልኡካቸው የለገዳዲ ግድብ ፣ በግድቦቹ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የተፋሰስ ልማት ስራ ፣ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት እና ማሰልጠኛ ተቋምን ነው የጎበኙት ::ጉብኝቱም በዋናነት አለም ባንክ ድጋፍ የሚያደረትግባቸውን ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ ማጤን እና ተጨማሪ ድጋፍ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡በቅርቡም በዓለም ባንክ ድጋፍ የለገዳዲና ድሬ ግድብ እድሳትና ማሻሻያ ለማከናወን ከዊ ቢውልድ (ሳሊኒ) ከተባለ የጣሊያኑ...

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምእራፍ ሁለት የውሀ ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት በይፋ መርቀዋል።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አስጀምሮ ላስጨረሰን ፈጣሪ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል፡፡ዛሬ የተቀዳጀነው ድል ትርጉሙ ብዙ ነው ያሉት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በአንድ በኩል በመጠጥ ውሃ ችግር ሲሰቃይ የነበረውን የአዲስ አበባ ነዋሪ ችግር የሚያቃልል በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ፕሮጀክቱ የሚለማበት አካባቢ ነዋሪዎችን የጋራ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑ...