የአዲስአበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአዲስአበባ ሴቶች ማኅበር የጥቃት ማገገሚያ ውስጥ ለሚገኙ 60 ሴቶች የቁርስ በጀት ድጋፍ አደረገ።
በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ እና የተለያዩ ጥቃቶች ተፈጽመውባቸው በማገገም ላይ ላሉ 60 ሴቶች 15 ሺህ ብር የሚያወጣ የሩዝና የፖስታ ድጋፍ ተደርጓል ። ድጋፉን ያስረከቡት በባለሥልጣኑ የቦርድና ስራ-አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት መሠረት አሰፋ በቀጣይም ሌሎች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረግና ከጎናችሁ ለመሆን ዝግጁ ነን ብለዋል። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዘንድሮ በዓለም ደረጃ ለ110ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ...የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ከ112 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃን ከብክነት ማዳን ችሏል፡፡
በባለሥልጣኑ ውሃውን ከብክነት ያዳነው፡- ያረጁ መለስተኛ እና ከፍተኛ የውሃ መስመሮችን በመቀየር፣ ተከታታይነት ያለው መደበኛ የውሃ ብክነት ምርመራ እና ቁጥጥር ስራ በተለያዩ መሳሪያዎች በማከናወን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እያንዳንዱ ቅርንጫፎች የሚገባውን እና የሚወጣውን የውሃ መጠን ለመቆጣጠር ከፍተኛ እና በመለስተኛ መስመር ላይ 53 የውሃ ቆጣሪዎችን በመትከል እንዲሁም ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ ቆጣሪዎች በመቀየር እና...የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ባለፉት 6 ወራት 622 ሚሊዮን ብር ገቢ ሰብስቧል፡፡
ገቢው የተሰበሰበው ከውሃ የአገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ልዩ ልዩ የገቢ ርዕሶች ነው፡፡ በባለሥልጣኑ ጥናት ዕቅድና በጀት ሃላፊ አቶ በዓለምላይ ባህሩ ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ 6ወራት 798 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የዕቅዱን 78 በመቶ ማሳካት ችሏል ብለዋል ፡፡ አፈጻጸሙ ከእቅዱ አንጻር ዝቅ ቢልም ከሀምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ13 ሚሊዩን ብር ብልጫ አሳይቷል ብለዋል ፡፡ በባለስልጣኑ በስድስት ወራት...
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች