የረጅም ጊዜ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ችግሩ ሙሉ ለሙሉ ተፈቷል፡፡

ጣፎ አደባባይ አካባቢ የሚገኝ የየካ አባዶ ሳይት የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመር ባልተገባ አጠቃቀም ምክኒያት ተዘግቶ ፍሳሹ እየገነፈለ ለነዋሪዉ ፈተና ፤ለአላፊ አግዳሚው ለመጥፎ ጠረን ዳርጎ ሰነባብቷል፡፡ፍሳሹም በማንሆል ገንፍሎ መንገድ ላይ በመፍሰሱ ምክኒንያት ነዋሪዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ከስፍራው የፍሳሽ ቆሻሻ ሰብስቦ ወደ ኮተቤ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የሚያጓጉዘው ከፍተኛ የፍሳሽ መስመር መዘጋትን ተከትሎ ችግሩን...
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የ490 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የ490 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ባለስልጣኑ የተፈራረመው ከጃፓን ዓለም አቀፍ ድርጅት (JICA) ጋር ሲሆን ስምምነቱም በውሃ ብክነትን መቀነስ እና ስርጭቱን ማስተካከል ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ከ51ሺኅ በላይ ደንበኞችን ያቀፈ ሲሆን በንፋስ ስልክ እና መካኒሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ላይ የሚተገበር ነው ፡፡በአሁኑ ሰዓትም ከተጠቀሱት አካቢዎች መረጃ በመሰብሰብ እና የተመረጡት ቅርንጫፎች ወቅታዊ የሆነ መሰረተ ልማቶችን ካርታ ላይ የማስፈር ስራ በመስራት ላይ...

ባለስልጣኑ ከ741.9 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሠበሰበ።

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት 5 ወራት 776 ሚሊየን 350 ሺህ 677 ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 741 ሚሊየን 987 ሺህ ብር በላይ በመሰብሰብ የዕቅዱን 96 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡ገቢው የተሰበሰበው በውሃ አገልግሎት ዘርፍ ከሚሠጡ የውሃ ሽያጭ፣ የቆጣሪ ግብር፣ ከውሃ መስመር ቅጥያ ሲሆን በፍሳሽ አገልግሎት ዘርፍ ከፍሳሽ ማንሳት አገልግሎት፣ ከአዲስ ደንበኞች የፍሳሽ መስመር ቅጥያ፣...