እንኳን ደህና መጣችሁ!!!

የድሬ ግድብ

ግንባታው በ1991 ተጠናቀቀ

21 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

የገፈርሣ ግድብና ማጣሪያ ጣቢያ

ግንባታው በ1948 ተጠናቀቀ

በ2001 በጀት ዓመት የጥገና ሥራ ከተካሔደለት ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅሙ ወደ 9.5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ያደገ ሲሆን ውሃ የማምረት አቅሙም በቀን 30ሺ ሜትር ኪዩብ ነው

ለገዳዲ ግድብ

በ1963 ተመሠረተ

47 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም አለው

በ1977 ማስፋፊያ ከተደረገለት በኋላና በ1990ዎቹ አጋማሽ የኬሚካል አጠቃቀሙን ማሻሻል እና የሥርጭት መሥመሩን መቀየር ያስቻለ የዕድሳት ሥራ ከተከናወነለት በኋላ ዕለታዊ ውሃ የማማረት አቅሙ በቀን 165ሺ ሜትር ኪዩብ ደርሶ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም በ2007 ዓ.ም. የድሬ ግድብን ውሃ የመያዝ አቅም መጨመርና የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያን ውሃ የማምረት አቅም በ30ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማሳደግ ያስቻለ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተካሒዷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከግድብ በየዕለቱ 195ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ይመረታል፡፡

የከርሠ ምድር ውሃ

ከ1987 ዓ.ም. ወዲህ በከተማዋ ከ100 በላይ ጥልቅና መካከለኛ ጉድጓዶች ተቆፍረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በቀን ከሚመረተው 608ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ውስጥ 413ሺ ሜትር ኪዩብ (67.9%) ያህሉ ከከርሠ ምድር ውሃ መገኛዎች የሚመረት ነው፡፡

የፍሳሽ ማስወገጃ መኪኖች

ያለቦትን የውሃ ክፍያ በቀላሉ ይመልከቱ!

የቢል መረጃ
R||divi||400

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም. ተቋማችን በሚሰጠው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች የከተማዋ ህብረተሰብ ረክቶ ማየት እና በዘርፉ የአፍሪካ ከተሞች የልዕቀት ማዕከል ሆኖ መገኘት፡፡
R||divi||400

ተልዕኮ

የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ በማድረግ የውሃ መገኛዎችን በማልማት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓትን በመዘርጋት ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ዕድገት ጋር የሚመጣጠን የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ በበቂና አስተማማኝ ሁኔታ መስጠት፡፡
R||divi||400

እሴቶች

1. አገልጋይነት 2. ቅንነት 3. በጋራ መስራት 4. እውቅና መስጠት 5. ልዕቀት 6. ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ትኩረት የሚሰጥ 7. ፍትሃዊነት 8. እምነት የሚጣልበት
የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው::

የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው::

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ መገኛ ተፋሰሶች እንዳይሸረሸሩና ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ በያዝነው ክረምት 46 ሺህ 500 ችግኞችን ተክሏል፡፡ችግኞቹ የተተከሉት በለገዳዲ፣ ገፈርሳና ድሬ ግድቦች ዙሪያ እንዲሁም በፍሳሽ ማጣሪ ጣቢያዎች ላይ ሲሆን በቀጣይም 800 የሎሚ ችግኞችን በለገዳዲ ግድብ ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በባለስልጣኑ የውሃ መገኛ ተፋሰሶች አስተዳደርና ጥበቃ ዲቪዥን የስራ ሂደት መሪ የሆኑት...

read more
በዓለም ባንክ ግሩፕ የምስራቅ ፣መካከለኛ እና ደቡብ አፍሪካ ወተር ፕራክቲስ ማናጀር ሶማ ጎሽ ሙሊክ እና ልዑካቸው የባለስልጣኑን መሠረተ ልማቶች ጎበኙ።

በዓለም ባንክ ግሩፕ የምስራቅ ፣መካከለኛ እና ደቡብ አፍሪካ ወተር ፕራክቲስ ማናጀር ሶማ ጎሽ ሙሊክ እና ልዑካቸው የባለስልጣኑን መሠረተ ልማቶች ጎበኙ።

ማናጀሯ እና ልኡካቸው የለገዳዲ ግድብ ፣ በግድቦቹ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የተፋሰስ ልማት ስራ ፣ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት እና ማሰልጠኛ ተቋምን ነው የጎበኙት ::ጉብኝቱም በዋናነት አለም ባንክ ድጋፍ የሚያደረትግባቸውን ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ ማጤን እና ተጨማሪ ድጋፍ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡በቅርቡም በዓለም ባንክ ድጋፍ የለገዳዲና ድሬ ግድብ እድሳትና ማሻሻያ ለማከናወን ከዊ ቢውልድ (ሳሊኒ) ከተባለ የጣሊያኑ...

read more
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምእራፍ ሁለት የውሀ ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት በይፋ መርቀዋል።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምእራፍ ሁለት የውሀ ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት በይፋ መርቀዋል።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አስጀምሮ ላስጨረሰን ፈጣሪ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል፡፡ዛሬ የተቀዳጀነው ድል ትርጉሙ ብዙ ነው ያሉት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በአንድ በኩል በመጠጥ ውሃ ችግር ሲሰቃይ የነበረውን የአዲስ አበባ ነዋሪ ችግር የሚያቃልል በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ፕሮጀክቱ የሚለማበት አካባቢ ነዋሪዎችን የጋራ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑ...

read more

ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ዋና ስራ አስኪያጅ

መልእክት

የተቋሙ ተገልጋዮች

||divi||400

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፤

||divi||400

በከተማዋ የሚገኙ የሀገር ውስጥና አለም አቀፋዊ ተቋማት፤

||divi||400

በውሃ መገኛዎች አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች፤

በላይ ደንበኞች

በላይ ሰራተኞች

ቅርንጫፎች

ግድቦች