ዜና
ባለሥጣኑ ባለፉት 9 ወራት ከ28 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ፍሳሽ ቆሻሻ አጣርቶ አስወግዷል።
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ (በመስመር) እና በተሽከርካሪ በማሰባሰብ ከ28 ሚሊዮን ሜ.ኩብ በላይ ፍሳሽ ቆሻሻ አጣርቶ አስወግዷል ።ባለስልጣኑ በዘመናዊ መንገድ ፍሳሽ የማሰባሰብ ስራን ከፍ ለማድረግም የ134.56 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ መስመር ጥናትና ዲዛይን ስራ ያጠናወቀቀ ሲሆን 82.41 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ መስመር ዝርጋታም አከናውኗል፡፡ ባለሥልጣኑ የፍሳሽ አገልግሎቱን ለማፋጠን...
ባለስልጣኑ ባለፉት 9 ወራት 140.3 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ አምርቶ አሰራጭቷል፡፡
ባለስልጣኑ ከገፀ ምድር እና ከርሰ ምድር የውሃ መገኛዎች አለም አቀፍ ጥራቱን የጠበቀ 140.3 ሚሊዮን ሜ. ኪ ውሃ አምርቶ ማስራጨት መቻሉ ተገልጿል ። ከገጸ ምድር የውሃ መገኛዎች 55.75 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ እንዲሁም ከከርሰ ምድር የውሃ መገኛዎች 84.58 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ በማምረት ለነዋሪዎች ተደራሽ ለማድረግ ተችሏል ፡፡ ይህም ከእቅዱ 85 % ያህል ሲሆን የእቅዱን ያክል ማሳካት ያልተቻለው በኤሌክትሮ ሜካኒካል...
ባለለስልጣኑ የሲቢሉ የውሃ ግድብ ፕሮጀክት ፋይናንስ እንዲያደርግ የአለም ባንክን ጠየቀ፡፡
በአለም ባንክ የውሃ ሲንየር ግሎባል ዳይሬክተር ሳሮጅ ኩማር ጃህ የተመራው ልኡክ ዛሬ የድሬ እና ለገዳዲ ግድብ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የሲቢሉ ግድብ ፕሮጀክት የፋይናንስ ጉዳይ እና በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራውን የግድቡ ውሃ ማስተንፈሻ በሮች ጥገና ስራ ላይ ያተኮረ ውይይትም ተደርጓል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዘሪሁን አባተ የአለም ባንክ ግሩፕ ለባለስልጣኑ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፤...
በባለስልጣኑ ለፍሳሽ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ፡፡
ባለስልጣኑ እውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር ያዘጋጀው ለፍሳሽ ተሽከርካሪ ኦፕሬተሮች እና ረዳቶች እንዲሁም ለሌሎች ባለሙያዎች ነው፡፡ በዕውቅና እና ምስጋና መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ እንደገለጹት፤ ዘርፉ የከተማችን ውበት እና ጽዳት የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ እና አሁን ባለው የከተማችን ነባራዊ ሁኔታ አብዛኛው ፍሳሽ ቆሻሻ በተሸከርካሪ የሚነሳ በመሆኑ...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ የባለስልጣኑን መሰረተ ልማት ጎበኙ፡፡
ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ የለገዳዲ ግድብ ማስተንፈሻ በሮች ጥገና ፕሮጀክት ፣ የተፋሰስ ልማት እና የማሰልጠኛ ተቋም ስራዎች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በስፋራው ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡ አቶ ጃንጥራር በዚሁ ወቅት ከባህዳር የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የመስክ ላይ የአመራርነት ስልጠና (FLL) ለወሰዱ ሰራተኞችም የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል፡፡ በግድቡ አካባቢ የተሰራው የተፋሰስ ልማት ስራ በጥሩ ደረጃ እንደሚገኝ...
ባለሥልጣኑ 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 42ኛው የሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት አድርጓል፡፡
ከፊታችን የካተቲ ስምንት እስከ አስራ ሁለት ድረስ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና የሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት ስብሰባ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡ ይህ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ባለሥልጣኑ በዘጠኙም ቅ/ጽ/ቤቶችና በዋና መ/ቤት 24 ሰዓት በተጠንቀቅ የሚሰራ ኮሚቴ አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ ባለሥልጣኑ ለእንግዶች ማረፊያ ለተዘጋጁ 143 ሆቴሎች፣ የስብሰባ አዳራሽ እና 28 ኤምባሲዎች አስፈላጊዉን አገልግሎት ለመስጠት...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሥራ አስኪያጅ ዘርፍ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የባለሥልጣኑ መሠረተ ልማቶች ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ፣ የለገዳዲ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ እና የባለሥልጣኑን የስልጠና ማዕከል ያካተተ ሲሆን በጉብኝቱ ብዙ ግንዛቤ ማግኘታቸውን አስረድተዋል። ከተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የተውጣጡት ባለሙያዎች በጎበኙት የውሃም ሆነ የፍሳሽ ስራ አድካሚ ከፍተኛ ድካም አንዳለው ተረድተናል ብለዋል። በሁሉም ጉብኝት ጥሩ ግንዛቤ አግኝተናል ያሉት ጉብኚዎቹ ግንዛቤያቸውን...
ባለስልጣኑ ባለፉት 6 ወራት 94.2 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ወሃ አምርቶ አስራጭቷል፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዛሬ የ6 ወራት የመደበኛ እና የፕሮጀክት ስራዎች አፈፃፀም በፕሮሰስ ካውንስል ገምግሟል ። በግምገማው ወቅት ባለስልጣኑ ከገፀ ምድር እና ከርሰ ምድር የወሃ መገኛዎች አለም አቀፍ ጥራቱን የጠበቀ 94.2 ሚሊዮን ሜ. ኪ ወሃ አምርቶ ማስራጨት መቻሉ ተገልጿል ። ይህም ከእቅዱ 82 % ሲሆን የእቅዱን ያክል ማሳካት ያልተቻለው በኤሌክትሮ ሜካኒካል ብልሽት፣ በኤሌትሪክ...
ባለስልጣኑ 90 የፍሳሽ ማንሻ ተሽከርካሪዎች አስገባ፡፡
ባለስልጣኑ የፍሳሽ ቆሻሻ የማንሳት አገልግሎቱን በላቀ ደረጃ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ከአለም ባንክ በተገኘ 15 ሚሊዮን ዶላር ብድር ተሸከርካሪዎችን አስገብቷል፡፡ ባለስልጣኑ ዘመናዊ የፍሳሽ በመስመር ማስወገድ አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የከተማችን ነዋረዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ነው ተሸከርካሪዎችን ያስገባው ፡፡ ተሸከርካሪዎቹን ስራ ለማስጀመር በተዘጋጀ ስልጠና ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራአስኪያጅ...
የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽህፍት ቤት አርሶ አደሮችን የንጹኅ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ቀጥሏል::
የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽህፍት ቤት ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ስሙ ጭላ ፈታ አካባቢ 500 አርሶ አደሮችን የንፁህ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ አድርጓል።1.6 k.m ርዝመት ያለው መስመር ተዘርግቶ ከአካባቢው ነዋሪው በተዋጣ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ፕሮጀክቱ ተገንብቶ ለአገልግሎት በቅቷል።በፕሮጀክት ርክክቡ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ...