በመንገድ ሥራ ምክንያት ከአቃቂ ክፍል 1 ወደ ከተማ ውሃ ይዞ የሚመጣውና 18.94 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ከፍተኛ የውሃ መስመር ማዛወር ስራ ተጠናቆ ለመንገድ ስራው ክፍት ተደርጓል፡፡የመስመር ማዛወር ስራው በ48 ሚሊየን 876 ሺህ 163.72 ብር እና በ7 ሚሊየን 245 ሺህ 883.4 የአሜሪካን ዶላር ወጪ በአሰር ኮንስትክሽን ኃ.ግ.ድ እና በIFH ኮንስትክሽን አማከኝነት ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡የከፍተኛ የውሃ መስመር ማዛወር ስራው ባለ 800፣ ባለ 400 እና ባለ 250 ሚ.ሜ ስፋት ያላቸውን መስመሮች ያካተተ ሲሆን ውሃውን ከነባሩ መስመር በተሳካ ሁኔታ ማዛወር ተችሏል፡፡