የዓለም የውሃ ቀን በዓለም ለ27ኛ ጊዜ ‘Leaving no one behind’ በሃገራችን ደግሞ ለ26ኛ ጊዜ “ንፁህ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ”  በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ በዓሉ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በፈረንጆቹ 2030 ሁሉንም ህብረተሰብ የውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የተያዘውን አጀንዳ ታሳቢ በማድረግ ይከበራል፡፡  የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣንም በውሃ አቅርቦት ፣ ተደራሽነት   እና በዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ  እያከናወናቸው በሚገኙ ስራዎች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ያከብራል፡፡

ባለስልጣኑ ባለፉት ዓመታት በሰራቸው በርካታ የውሃ ልማት ኘሮጀክቶች የውሃ ምርቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊያሳድጉ የሚችሉ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ሠዓት ከ550 ሺህ በላይ የውሃ ደንበኞች ያሉት ባለስልጣኑ ከገፀ-ምድር እና ከርሰ-ምድር የውሃ መገኛዎች በየዕለቱ 575 ሺህ ሜት ኪዩብ ውሃ በማምረት ለደንበኞቹ በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ 46 ሺህ ሜ.ኪብ የሚሆነው በያዝነው ዓመት ከኮዬ ፈጬ እና ኪስ ቦታዎች በተሰሩ የውሃ ፕሮጀክቶች የተገኘ ነው፡፡

ይሁንና አዲስ አበባ በማያቋርጥ ፈጣን እድገት ውስጥ የምትገኝ ከተማ መሆኗን ተከትሎ አሁን ያለው የቀን የውሃ ፍላጎትዋ 930 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ እንደሆነ ይገመታል ፡፡ የተፈጠረውን የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም ለማስተካከል ከሁለት አመት በፊት ተጀምረው  በወሰን ማስከበር እና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ችግር የቆሙ  የሳውዝ አያት ኖርዝ ፈንታ፣ የለገዳዲ ክፍል ሁለት ጥልቅ  ጉድጓድ ውሃ  እና ገርቢ ግድብ ፕጀክቶች ችግራቸውን በመፍታት ከቆሙበት እንዲቀጥሉ የማድረግ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታትም በቀን 418ሺ ሜትር ኪዩብ የማምረት አቅም ያለው የሲቪሉ ግድብ ጥናት የማጠናቀቅ እና ገንዘብ የማፈላለግ ስራ እየተሰራ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ባለስልጣኑ የከተማዋን የፍሳሽ አወጋድ ስርአት ለማዘመን ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባስገነባቸው  የፍሳሽ መሰረተ ልማቶች  የማጣራት አቅሙን በቀን 150ሺ ሜትር ኪዩብ አድርሳል፡፡  አሁን   በቀን እያጣራ ያለው ግን 85ሺ 500 ሜትር ኪዩብ ብቻ ነው ፡፡ ባስልጣኑ በአቅሙ ልክ ፍሳሹን በዘመናዊ መንገድ ሰብስቦ ያጣራ ዘንድም  ህብረተሰቡ የተዘረጉ የፍሳሽ መሰረተ ልማቶችን በአግባ  እንዲጠቀም ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ኢሜል አድራሻ፡ aawsainfo@gmail.com

የዘንድሮው የዓለም የውሃ ቀን በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን 500 የደንበኞች ፎረም አባላት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በፖናል ውይይት፣ በፎቶ ኢግዚብሽን ጉብኝት ተከብሮ ይውላል፡፡

ኢሜል አድራሻ፡ aawsainfo@gmail.com
ኢሜል አድራሻ፡ aawsainfo@gmail.com