ውሃ በተሽከርካሪ ለምትሸጡ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በሙሉ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 10/1987 አንቀፅ 8 መሠረት በባለስልጣኑ የስልጣን እና የአገልግሎት ክልል ውስጥ ካልተፈቀደለት በስተቀር ማንም ሰው ውሃ ማምረት፣ ማከፋፈል፣ ለራሱም ሆነ ለሌላ አካል ማቅረብ እና ባለስልጣኑ የሚያቀርበውን ውሃ መሸጥ እንደማይችል ተደንግጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 25 ንዕስ አንቀፅ 1 ለማንኛውም አገልግሎት የውሃ ጉድጓድ...

የኮዬ ፈቼ ቂሊንጦ ቱሉ ዲምቱ የውሃ ፕሮጀክት በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተመረቀ፡፡

በምርቃት ሥነ-ሥርዐት ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የከተማው መስተዳድር በጅምር ያሉትን የውሃ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት አጠናቆ በመጨረስ የነዋሪውን ፍላጎት ማሟላት እንደሚገባ ገልፀው ይህም ሊሳካ የሚችለው በጋራ የመልማት መርህ ላይ ስንቆም መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የኮዬ ፈቼ ቂሊንጦ ቱሉ ዲምቱ የውሃ ፕሮጀክት በ 2006 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው 1.2 ቢሊዮን ብር ፈጅቷል፡፡ፕሮጀክቱም...

ማስታወቂያ

በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከ90 በላይ የስራ መደቦች የስራ ፈላጊዎች አወዳድሮ ለመቅጥር ይፈልጋል የሚል ከአንድ አመት በፊት የወጣውን ማስታወቂያ አሁን እንደወጣ በማስመሰል የስራ ፈላጊዎች ላላስፈለጊ እንግልት እየተደረጉ መሆኑን ተስተውሏል ፡፡ ስለሆነም በድረ-ገጹ ላይ የተለጠፈው የሥራ ማስታወቂያ የተሳሳተ መሆኑን እየገለጽን ሥራ ፈለጊዎችም ራሳችሁን ላላሰፈላጊ እንግልትና ወጪ...