የካይዘን ፍልስፍናን ተግባራዊ በማድረግ 1.5 ሚሊዮን ብር ማዳን ተቻለ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የኤሌክትሮ ሜካኒካልና ብየዳ ሥራዎች ንዑስ የስራ ሂደት የካይዘን ፍልስፍናን ወደ ተግባር በመቀየር 1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያስቀረ ውሃ ፓምፕና ሞተሮችን ለመፈተሽ የሚያስችል ቴስት ቤንች የተባለ አንድ መፈተሻ ማሽን ሰራ፡፡ ክፍሉ መፈተሻ ማሽኑን የሰራው  አገልግሎት ላይ የዋሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በማሰባሰብ ነው፡፡ መፈተሻው ጠላቂ የውሃ ፓምፕና ሞተሮች ወደ ውሃ መገኛ ጣቢያ...