የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ከቻይና CGGC ኩባንያ ጋር የ6.5 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመ ።

ባለስልጣኑ ከኩባንያው ጋር ስምምነቱን የተፈራረመው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪ ጣቢያ ሙሉ የኦፕርሽን ስራ ( ማጣሪያ ጣቢያው ደረጃውን የጠበቀ ፍሳሽ የማጣራት እና የማወገድ) እንዲሁም ጥገና እና የአቅም ግንባታ ስራን ያካትታል፡፡ የውል ስምምነቱ ለሶስት አመት ከመንፈቅ የሚቆይ ሲሆን ፕሮጀክቱም በአለም ባንክ የሚደገፍ ነው፡፡ የባለስልጣኑ ስራስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ በስምምነቱ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ማጣሪያ ጣቢያ...

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን መካኒሳ ቅርንጫፍ የፎረም አባላት እና የቅርንጫፉ ፕሮሰስ ካውንስል የፍሳሽ መሰረተ ልማችን ጎበኙ ::

የተጎበኙት መሰረተ ልማቶች የመካኒሳ ቁጥር ሁለት የጋራ መኖሪያ ቤት የተገነባው ያተማከለ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ እና የቃሊቲ ማጣሪያ ጣቢያን ናቸው ፡፡ የጉብኝቱ ዋና አላማ አባላቱ በፍሳሽ ዘርፍ የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን በማየት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ በተለይም በቀን መቶ ሺኅ ሜ.ኪዩብ የማጣራት አቅም ያለው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ በከፍተኛ ወጪ ተገንብቶ አገልጎሎት እየሰጠ ቢሆንም እያጣራ ያለው ከግማሽ ያነሰ...

የውሃ ግድቦች ዙሪያ የሚሰራው የተፋሰስ ልማት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

በለገዳዲ ተፋሰስ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በትብብር የሚሰራው የቪተንስ ኢቪደንስ አመራሮች ፣የሰነዳፋ ከተማ አስተዳር ከንቲባ እና የባስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ልማቱም በውሃ ተፋሰሶች ዙሪያ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ወደ ግድብ የሚገባ ጥሬ ውሃ እንዳይበከል መከላከልን አላማ ያደረገ ነው ፡፡ ቪተንስ ኢቪደንስ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ...