የመመሪያ አወጣጥ፣ አመዘጋገብ ፣ መረጃ አቀማመጥ እንዲሁም የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ስርዓትን ለመደንገግ በወጣው የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2020 አንቀፅ 7 መሰረት በረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት እንዲቀርብ ጥሪ ማድረግን ይመለከታል ፡፡

የአሰልጣኝ አመራረጥ ሂደትና መስፈርትን ማስፈፀም የወጣው መመሪያ ቁጥር 11/2011 ለአሰልጣኖች ፣ለሰልጣኞች ፣ ለስልጠና አስተባባሪዎች እና ለሌሎችም በስልጠናው ግብዓት ለሰጡ ባለሙያዎች የሚከፈለውን ክፍያ በአግባቡ ያልደነገገ የአከፋፈል ስርዓቱም ወጥና ተጠያቂነት የሰፈነበት የህዝብን ገንዘብ ከብክነትና ከምዝበራ የሚከላከል ባለመሆኑ ባለስልጣኑ ይህንን የስልጠና ሲሰጥም የአሰልጣኞች ምልመላም ሆነ የአሰልጣኞችና የተሳታፊዎች...