የረጅም ጊዜ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ችግሩ ሙሉ ለሙሉ ተፈቷል፡፡

ጣፎ አደባባይ አካባቢ የሚገኝ የየካ አባዶ ሳይት የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመር ባልተገባ አጠቃቀም ምክኒያት ተዘግቶ ፍሳሹ እየገነፈለ ለነዋሪዉ ፈተና ፤ለአላፊ አግዳሚው ለመጥፎ ጠረን ዳርጎ ሰነባብቷል፡፡ፍሳሹም በማንሆል ገንፍሎ መንገድ ላይ በመፍሰሱ ምክኒንያት ነዋሪዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ከስፍራው የፍሳሽ ቆሻሻ ሰብስቦ ወደ ኮተቤ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የሚያጓጉዘው ከፍተኛ የፍሳሽ መስመር መዘጋትን ተከትሎ ችግሩን...