የኘሮጀክቱ ሥም፡ ለዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል የውኃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ፕሮጀክት
አስፈፃሚው አካል፡- በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት
ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ በተለያዩ ክ/ከተሞች ውስጥ
ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ዓላማ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የውኃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡
የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- በ10ሩም ክፍለ ከተሞች በተመረጡ ቀበሌዎች የሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የውኃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
- ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ለማወቅ ያስችል ዘንድ የመለያ መስፈርት ጥናት፣
- በዝቅተኛ ገቢ መኖሪያ አካባቢ ያሉትን ሕብረተሰብ በአግባቡ በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት በመለየት የማዋቀር ሥራ፣
- ለተለዩት የህብረተሰብ ክፍሎች የጥናትና ዲዛይን ስራ
- የጋራ ውኃ ቧንቧ ግንባታ ማከናወን፣
- የጋራ እና ተንቀሳቃሽ መፀዳጃ ቤት ግንባታ ማከናወን፣
ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-
- በ 2001 ዓ.ም.
ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-
- በ 2012 ዓ.ም.
የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 300,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡
መግቢያ
አዲስ አበባ ከተማ ካሉት ነዋሪዎች ከ 60% በላይ የሚሆነው በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ መሆኑን የተለያዩ ጥናት ያመለክታል፡፡ ይህ ህብረተሰብም በመጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚነት ወደኋላ መቅረታቸውን በዝቅተኛ ገቢ መኖሪያ አካባቢ በማቴዎስ አማካሪ ድርጅት የተጠናው ጥናትም ያመለክታል፡፡
ይህን የከፋ ችግር መንግሥት በተለይ ከአለም ባንክና ሌሎች አለምአቀፋዊ የገንዘብ ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይነት ያለው መፍትሄ ለማምጣት ጐምበስ ቀና ማለት ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ እስከ 2006 በጀት ዓመት ማብቂያ 5500 ቡድኖችን የውኃና ሳኒቴሽን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡
በቀጣይም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዝቅተኛ ገቢ መኖሪያ አካባቢ የተቀመጠውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ እንዲቻል በ2006 በጀት ዓመት በ8 ክፍለ ከተሞች በተመረጡ ቀበሌዎች ውስጥ 457 የጋራ ቧንቧና 1000 የጋራ፣ የህዝብ እና ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤት፣ሻወርና የጋራ ልብስ ማጠቢያ ለመስራት ታቅዷል
የኘሮጀክቱ ዓላማ፡
በዝግተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የከተማዋ ነዋሪዎችን የውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ነው፣
የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ግብ፡
በ8 ክፍለ ከተሞች በተመረጡ ቀበሌዎች የሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የውኃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣
- የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ቅጥር በመፈጸም 457 የጋራ ውሃ ቧንቧ ግንባታ ማከናወን፣
- ለ1634 ቅጥያዎች የቆጣሪ ቅጥያ ክፍያ መፈጸም
- በ2007 በጀት ዓመት የግዥ ሂደታቸው የተጠናቀቁ የ46 መፀዳጃ ቤቶች ግንባታ ሥራ ማጠናቀቅ፣
- የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ100 መጸዳጃ ቤቶች (80 የጋራ እና 20 የህዝብ) ግንባታ ሥራ ማከናወን
- በመገናኛ አካባቢ በዓይነቱ ለየት ላለ 1 ባለ G+2 መጸዳጃ ቤት ግንባታ የጥናትና ዲዛይን ሥራ ቀሪ 50 በመቶ ማከናወን፣
- የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም በመገናኛ አካባቢ በዓይነቱ ለየት ያለ 1 ባለ G+2 መጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ 23 በመቶ ማከናወን፣
- ከ410 መጸዳጃ ቤቶች ውስጥ የቀሪ 316 መጸዳጃ ቤቶች ተከላ ሥራ ክፍያ መፈጸም፣
- ከ424 ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶች ውስጥ ቀሪ 290 መጸዳጃ ቤቶች ዕቃ አቅርቦትና ተከላ ሥራ ክፍያ መፈጸም፣
- ለ60 ኪ.ሜ. የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ ክፍያ ቀሪ 70 በመቶ ክፍያ መፈጸም
- ለተጠናቀቁ የጋራ እና የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች የመያዥያ ክፍያ መፈጸም
- በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ለሚከናወን የ110 የጋራ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ሥራ ቀሪ 10 በመቶ ክፍያ ማጠናቀቅ፣
- የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን፣
የአፈጻጸም ስልቶች፣
ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በ2001 በጀት ዓመት የተጀመረውን በሎት በመከፋፈል ሥራዎችን የመስጠት ሥራ በቀጣይነት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በ2008 የታቀዱትን ተጨማሪ ሥራዎች በታቀደው መሠረት ሥራ ላይ ለማዋል የተጠቀሰውን የአፈጻጸም ስልቶች መከተል የግድ ይላል፡፡
ለኘሮጀክቱ አስፈላጊ ግብዓቶች
ለ2008 በጀት ዓመት ለታቀዱት ሥራዎች በአብዛኛው ከሀገር ውስጥ በሚመረቱ ዕቃዎች ላይ የመሰረተ ስለሆነ፤
- እስከ 2” እና ከዛ በታች የሆኑትን ቧንቧዎች
- ፊቲንጐች፣
- ተጨማሪ የውሃ ማጠራቀሚያ በሚያስፈልግበት ቦታ አዲስ የውሃ ማጠራቀሚያ፣
- የውሃ ቆጣሪ፣
የአካባቢና የማህበራዊ ትንትኔ
ለሚደረገው የመስመር ዝርጋታና የሳኒቴሽን አገልግሎት በማህበራዊ ጉዳይ የሚኖራቸው አሉታዊ ተጽዕኖ ከቦታ ይገባኛል ጥያቄ እና ከካሣ ክፍያ ጋር በመጠኑ የተያያዘ ስለሆነ በአካባቢያቸው የሚገኘው ቀበሌና ክ/ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ በመስራት መፍትሄ የሚያገኝ ይሆናል፡፡
የተጠናከረ የሱፐርቪዥን ሥራ
- የጋራ መድረክ በማዘጋጀት የሥራ መሻሻሎችና ችግሮች ላይ ውይይት ማካሄድ፣
- ሪፖርቶችን ከ “physical work” ጋር ትክክል መሆኑን መቆጣጠር፣
- ከቅርንጫፍ መ/ቤቶችና ከሌሎች ባለድርሻ መስሪያ ቤቶች ጋር ተጣምሮ መሥራት፣
- የተጠቃሚውን ህብረተሰብ ተሳትፎ ማጠናከር እንዲቻል የተጠበቀ ክትትል ማድረግ፣
ስጋትና ምቹ ሁኔታዎች
የኘሮጀክቱ ሥራ በታሰበበት ፍጥነትና በታሰበበት የጊዜ ገደብ ለመወጣት ስጋት ሆነው የሚቀጥሉት፣
- የአለም ባንክ በወቅቱ ለተጠየቀው ጥያቄ ወቅታዊ ምላሽ ያለመስጠትና የተጠየቀው መስፈርት ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ ያለመሆን፣
- በግዥ በኩል የተፋጠነ ምላሽ ያለማግኘት፣
ምቹ ሁኔታዎች
- ለሥራው አስፈላጊው ባለሙያ የተመደበለት መሆን፣
- ከባለድርሻ መስሪያ ቤቶች ጋር የተቀናጀ ሥራ መስራትና ተናቦ የመሄድ፣
የበጀት ፍላጐት
- በ2008 በጀት ዓመት ውስጥ ለሚደረገው የመጠጥና የሳኒቴሽን አገልግሎት የዝቅተኛ ገቢ መኖሪያ አካባቢ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ብር 107,746,640 የሚያስፈልግ ይሆናል፡፡
ተ.ቁ. | የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት | የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት | ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት | የተያዘ በጀት | ምርመራ | |||
ከመንግስት | ከመ/ቤቱ | ከብድር | ዕርዳታ | |||||
20 | ለዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል የውኃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ፕሮጀክት | 107,746,640 | 100,453,020 | 0 | 0 | 7,293,620 | ||
20.1 | የ1177 የጋራ የውሃ ቧንቧ ግንባታ ሥራ ማከናወን፣ | 5,578,164 | 139,454 | 139,454 | ከ1177 የጋራ ውኃ ቧንቧ ግንባታ ሥራ ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ቀሪ 2.5 በመቶ መያዥያ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
20.2 | የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ቅጥር በመፈጸም 457 የጋራ የውሃ ቧንቧ ግንባታ ማከናወን፣ | 2,382,449 | 2,382,449 | 2,382,449 | በ2008 በጀት ዓመት ከሥራው ጋር በተያያዘ ለሚገባ ውለታ የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
20.3 | ለ56 መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ሥራ የመያዥ ክፍያ መፈጸም | 25,000,110 | 625,000 | 625,000 | በ2007 በጀት ዓመት ከሚጠናቀቅው ሥራ ጋር በተያያዘ ለሚከፈል 2.5 በመቶ የመያዥያ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
20.4 | ከ15 መጸዳጃ ቤቶች ውስጥ ለ2 መጸዳጃ ቤቶች የመያዥያ ክፍያ | 3,681,901 | 46,000 | 46,000 | በ2007 በጀት ዓመት ከሚጠናቀቅው ሥራ ጋር በተያያዘ ለሚከፈል 2.5 በመቶ የመያዥያ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
20.5 | የግንባታ ግዥ በመፈጸም 14 የጋራ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ማከናወን | 7,270,334 | 4,725,717 | 4,725,717 | በ2008 በጀት ዓመት ከሥራው ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ቀሪ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
20.6 | የግንባታ ግዥ በመፈጸም 19 የጋራ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ማከናወን | 9,044,616 | 5,879,000 | 5,879,000 | በ2008 በጀት ዓመት ከሥራው ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ቀሪ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
20.7 | የግንባታ ግዥ በመፈጸም 13 የጋራ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ማከናወን | 6,188,421 | 4,950,737 | 4,950,737 | በ2008 በጀት ዓመት ከሥራው ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ቀሪ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
20.8 | የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም በመገናኛ አካባቢ በዓይነቱ ለየት ያለ 1 ባለ G+2 መጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ማከናወን፣ | 30,000,000 | 8,000,000 | 8,000,000 | በ2008 በጀት ዓመት በሚገባው ውለታ መሠረት ለሚከፈል የቅድመ ክፍያ እና 23 በመቶ ከሚደርሰው ግንባታ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
20.9 | የ410 መጸዳጃ ቤቶች ውስጥ ተከላ ሥራ ክፍያ መፈጸም፣ | 63,078,818 | 24,000,000 | 24,000,000 | ከዋናው መ/ቤት የፍሳሽ ዘርፍ ጋር በመነጋገር ሥራው እስከ ሰኔ 30/2007 በጀት ዓመት ምን ያህል እንደሚደርስ ታሳቢ በማድረግ ለ2008 የሚተላለፈው በጀት ተይዟል፡፡ | |||
20.1 | ከ424 ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶች ውስጥ 134 መጸዳጃ ቤቶች ዕቃ አቅርቦትና ተከላ ሥራ ክፍያ መፈጸም፣ | 109,399,348 | 25,000,000 | 25,000,000 | ||||
20.1 | ለ60 ኪ.ሜ. የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ ክፍያ መፈጸም | 66,000,000 | 20,000,000 | 20,000,000 | ||||
20.1 | ለ1634 ቅጥያዎች የቆጣሪ ቅጥያ ክፍያ መፈጸም | 212,420 | 212,420 | 212,420 | ለአንድ ቅጥያ በ130 ብር ሂሳብ መነሻነት በጀቱ ተይዟል፡፡ | |||
20.1 | የግንባታ ግዥ በመፈጸም 100 መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ማከናወን | 51,930,957 | 11,632,683 | 11,632,683 | በ2008 በጀት ዓመት ከሥራው ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
20.1 | የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን | 459,540 | 153,180 | 153,180 | በውል ስምምነቱ መሠረት በየወሩ ለሚያካሄደው የሱፐርቪዥን ሥራ በየወሩ የሚከፍል ሲሆን በዚህ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለ6 ወር ለሚከፍል ክፍያ የተያዘ በጀት ነው:: |
Recent Comments