በደርቱ አካባቢ  ባጋጠመው ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ምክንያት ባለ 800 ሚሊ ሜትር ከፍተኛ የውሃ መስመር ላይ የስብራት አደጋ አጋጥሟል፡፡በዚህም ምክንያት በተወሰኑ የከተማዋ አካባቢዎች የውሃ ሥርጭት ተቋርጧል፡፡
በጀሞ ፣በላፍቶ፣በለቡ፣በሀና ማርያም፣በጎፋ እና በቄራ አካባቢዎች  በከፊል የውሃ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወደ መደበኛ ስርጭት ለማስገባት የጥገና ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ደንበኞች አስከ ሀሙስ ነሀሴ 24/2010 ዓ.ም ድረስ የጥገናው ስራ ተጠናቆ ወደ መደበኛ ስርጭት እስኪገባ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን እናሳውቃለን ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን