በአሁኑ ጊዜ የክረምቱ ዝናብ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የለገዳዲ ግድብ ውሃ መያዝ ከሚችለው በላይ ሞልቷል ፡፡ በዚህም ምክንያት በግድቡ ላይ በተፈጠረው ጫና ትርፍ ውሃ በማስወገድ ላይ እንገኛለን፡፡
በመሆኑም ከግድቡ በታችኛው ተፋሰስ በተለይም በአቃቂ ክፍለ ከተማ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ የምትገኙ ነዋሪዎች ከወቅቱ ዝናብ ጋር ተደምሮ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል በሰው፣ በእንስሳት እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከወዲሁ ቅደመ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች