በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከ90 በላይ የስራ መደቦች የስራ ፈላጊዎች አወዳድሮ ለመቅጥር ይፈልጋል የሚል ከአንድ አመት በፊት የወጣውን ማስታወቂያ አሁን እንደወጣ በማስመሰል የስራ ፈላጊዎች ላላስፈለጊ እንግልት እየተደረጉ መሆኑን ተስተውሏል ፡፡ ስለሆነም በድረ-ገጹ ላይ የተለጠፈው የሥራ ማስታወቂያ የተሳሳተ መሆኑን እየገለጽን ሥራ ፈለጊዎችም ራሳችሁን ላላሰፈላጊ እንግልትና ወጪ እንድትዳረጉ ባለስልጣኑ ያሳስባል፡፡

                   የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን