አርሶ አደር ሀይሌ ጸጋዬ በመዲናዋ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ 11 ቱሉ ጉዶ አካባቢ ነዋሪ ናቸው፡፡
በደካማ አቅማቸው ያመረቱት ምርት ከጎተራቸው ይገባ ዘንድ ጉዳት ሳይደርስበት መሰብሰብ አለበት ! እርሳቸው ግን ለዚህ የሚሆን አቅም አልነበራቸውም፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የመካኒሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እንደ ሀገር የተላፈውን ጥሪ በመቀበል ሠራተኞቹን ፣ አመራሮችን ፣የቆፋሪ እና አንባቢ ማህበራትን እንዲሁም የውሃ ደንበኞች ፎረም አባላትን በማሳተፍ ዛሬ በአዛንቱ ማሳ በመገኘት ጤፍ አጭደው ከምረዋል፡፡
ሰብል የተሠበሠበላቸው አርሶ አደር ሀይሉ ፀጋዬ “በምን አቅሜ እሰበስባለሁ ብዬ ሳስብ ነበር የተደረገልኝ እገዛ ትልቅ ነው እውነት ፈጣሪ እጃችሁን ይባርክ ! ሀገራችንን ሰላም ያድርጋት ! ” ሲሉ አመስግነዋል ፤ መርቀዋል ፡፡
በአጨዳው ላይ የተሳተፉ አካላትም ከፍተኛ የመንፈስ እርካታ ማግኘታቸውን ገልጸው፤ የመተባበረ ውጤትን በአጭር ጊዜ ያየንበት ፕሮግራም ነው ሲሉም ገልጸዋል ፡፡
በአጨዳ መረሀ-ግብሩ ላይ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቢሊሴ አብሼ እና የአርሶ አድር እና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘሪሁን ደገፋ የተገኙ ሲሆን ለተደረገው እገዛም አመስግነዋል፡፡