ኢ/ር ዘሪሁን ይህን ያሉት በባለስልጣኑ እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና የመጀመሪያ ዙር ማጠቃለያ እና የሁለተኛው ዙር ማስጀመሪያ መረሃ ግብር ላይ ነው።
ባለስልጣኑ በአዋጅ የተሰጠው ንጹህ መጠጥ ውሃ ማቅረብ፣ ፍሳሽ ማሰባሰብ ማጣራት እና ማስወገድ እንዲሁ የውሃ መገኛ አካባቢዎችን የተፋሰስ ልማት ስራ በሚፈለገው ልክ ለመስራት በባለቤትነት ስሜት የሚሰራ ሰራተኛ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በዚህ ረገድ በአይነቱ የተለየ በአስተሳሰብ ላይ የሚያተኩር እና የመጨረሻ ውጤቱ የአገልግሎት አሰጣጥን ማሳደግ ላይ ያተኮረ Field Level Leadership (FLL) ስልጠና ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።
ስልጠናው በአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ፣በቪቴንስ ኢቪደስ ኢንተርናሽናል እና ወርልድ ባንክ ግሩፕ ትብብር የሚሰጥ ነው።
በመረሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የቪቴንስ ኢቪደስ ኢንተርናሽናል ምስራቅ አፍሪካ አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ጥሩነህ በበኩላቸው ስልጠናው እያመጣ ባለው ለውጥ መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ለሚሰጠው ስልጠና ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋልበመረሀ ግብሩ ላይ ስልጠናውን የወሰዱ ሁለት ቅርንጫፎች ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።